የሳንባችን ጤንነት – Lung Health

                                                       

ሳንባችን ጤንነትና በአግባቡ ለመስራት መቻል ለጠቅላላ ደህንነታችም ይጠቅማል፡፡ ሳንባችንን ባላሰብናቸውና ከጥንቃቄ ጉድለት ተግባራዊ በምናደርጋቸው ልማዶች የመጎዳቱን ያህል በአመጋገባችንም ጤናማ ማድረግ እንደሚቻለን ይታመናል፡፡

Health digest በተባለው ድረገፅ ላይም ለዚህ የሚረዳን የአመጋገብ ስርዓት ተጠቁሟል፡፡
የጀመሪያው በቀላሉ ማግኘት የምንችለው ነገር ውሃ ነው፡፡ ሳንባችን ሲደርቅ ሊቃጠል ወይም ሊኮማተር ይችላል፡፡ ስለዚህም በቀን ከ6-8 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ተገቢ ነው፡፡
አሳን መመገብ ደግሞ ሌላኛው የሳንባችንን ጤና የምንጠብቅበት መንገድ ነው፡፡ አሳ በውስጡ በሚይዘው ኦሜጋ 3 አማካኝነት ነፃ የሆነና ጤናማ ሳምባ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከጥራጥሬዎች መካከል ባቄላ ሳንባችንን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን የመከላከል አቅም አለው፡፡
ኮሌስትሮልን ስለሚከላከልና ከተለያዩ ኢንፌክሽኖች እንድንጠበቅ ስለሚረዳን ነጭ ሽንኩርትን ከገበታችን ባንለየው ለአተነፋፈስ ስርዓታችን የተስተካከለ መሆን ጉልህ ሚና አለው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ለውዝ በማግኒዥየም የበለፀገ በመሆኑ ለሳንባችን ስራ የተቃና መሆን ያግዛል ብርቱካን ደግሞ ኦክስጅን በቀላሉ እንዲዘዋወር እንደሚረዳ ተረጋግጧል፡፡
አካላዊ እንቅስቃሴን በመስራት፣ ሲጋራን ባለመጨስ እንዲሁም ከበድ ያለ ቅመም ያላቸውን ምግቦችና ኬሚካላቸው የበዛ መድኃኒቶችን በመቀነስ ጤናማ ሳምባ ሊኖረን ይችላል ሲሉ ባለሞያዎቹ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦Health digest

Advertisement