ውሃ ውስጥ የገባን የሞባይል ስልክ ማከሚያ መንገዶች (Techtalk Ethiopia/ቴክ ቶክ ኢትዮጵያ)

                                  

    በአጋጣሚ የሚጠቀሙበት ተንቀሳቃሽ ስልክ ውሃ ውስጥ ሊወድቅ እና ሊበላሽ ይችላል። አንዳንድ ስልኮች ውሃን በቀላሉ እንዳያሰርጉ ተደርገው የተዘጋጁ ቢሆንም፥ ውሃ ወደ ውስጠኛ ክፍላቸው የሚገባባቸው ሁኔታዎችን ግን ሙሉ በሙሉ የዘጉ አይደሉም።በየትኛውም አጋጣሚ የሞባይል ስልክዎ ውሃ ውስጥ ቢወድቅብዎ

• ፈጥኖ ከውሃው ውስጥ ማውጣት፦ ስልኩ በውሃ ውስጥ በቆየ ቁጥር የሚደርስበት ጉዳት እየከፋ ይመጣል።

• ስልኩን ፈጥኖ መዝጋት

• ከስልኩ መለየት የሚችሉ ለምሳሌ ባትሪውን እና ሲም ካርዱን ፈጥኖ ማውጣት

በሞባይል ስልኩ ውስጥ እርጥበት ስለሚኖር ይህ ካልተወገደ ስልኩ መስራት አይችልምና፥ እርጥበቱን ለማጥፋት፦

• በደረቅ እና ነፋስ ሊያገኝ በሚችል ስፍራ ማስቀመጥ፣
• ከ100 እስከ 110 ዲግሪ ፋራናይት ሙቀት እንዲያገኝ በሚችል ስፍራ ማስቀመጥ።

ስልኩ የአፕል ምርት ከሆነ ደግሞ፥ ኩባንያው እስከ 115 ዲግሪ ፋራናይት ሙቀት ሰጥቶ እርጥበቱን ማስወገድ እንደሚቻል ይመክራል።

• የሞባይል ስልኩ እስከሚደርቅ ድረስ ጥቂት ቀናት ማቆየት፣

ስልኩን በሩዝ ማከምም ሌላኛው አማራጭ ነው።

ለዚህም ውሃ ውስጥ የወደቀውን የሞባይል ስልክ በጥሬ ሩዝ ውስጥ በመክተት ማቆየት።

ይህ ደግሞ ሩዝ በተፈጥሮው እርጥበት የመሳብ ባህሪ ስላለው በስልኩ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመምጠጥ እንዲደርቅ ያደርገዋል።

ምንጭ :-Techtalk Ethiopia/ቴክ ቶክ ኢትዮጵያ

Advertisement