በአሜሪካ አዲስ የደም ካንሰር መድሐኒት ይፋ ተደረገ

ምንጭ፦ክዩርቱዴይ

በዩናይትድ ስቴትስ “ዞስፓታ” የተሰኘ አዲስ የደም ካንሰር መድሐኒት ይፋ መደረጉ ተገለጸ።

የዞስፓታ አዲስ የደም ካንሰር መድሐኒት ተጠቃሚ የሚሆኑትም ወጣት የደም ካንሰር ተጠቂ ህመምተኞች ብቻ ናቸው ተብሏል።

ይህ የሆነውም መድሐኒቱ በብዛት ወጣቶችን ለሚያጠቃው “ሜሎይድ ሉኩሚያ” የተሰኘውን የካንሰር ዓይነት ለመከላከል የሚረዳ በመሆኑ ነው።

ሜሎይድ ሉኩሚያ በአብዛኛው በሰውነታችን ውስጥ በሚገኙ ነጭ የደም ሕዋሳት ውስጥ  የሚገኙ መደበኛ የሆኑ የደም ሴሎችን በማጥፋት ይታወቃል፡፡

ይህም ነጭ የደም ህዋሳትን ቁጥር በመቀነስ መደበኛ የስራ ክንዋኔያቸው እንዲስተጓጎል ያደርጋል።

ይህን የደም ካንሰር በሽታ ለመከላከልም የዞስፓታ መድሐኒት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያለው መሆኑ ነው የተነገረው።

እንደ ባለሙያዎች ገለፃ ዞስፓታ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ነጭ የደም ህዋሳትን በማጥቃት ለሉኩሚያ ካንሰር የሚዳርገውን ሁኔታ በእጅጉ ይከላከላል ብለዋል።

የዞስፓታን ውጤታማነት ለማረጋገጥም ኤፍዲኤ በበሽታው ተጠቂ በሆኑ 128 ሰዎች ላይ ሙከራውን አካሂዷል።

በሂደቱም አብዛኞቹ  የበሽታው ተጠቂዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ከበሽታው ነፃ መሆናቸው ነው የተገለፀው።

ይህንንም ተከትሎ ኤፍዲኤ ዞስፓታ የተሰኘው የደም ካንሰር መከላከያ መድሐኒት ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ አገልግሎት ላይ ይውል ዘንድ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

 

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.