በሽታን ተከላካይ የሆኑ አረንጓዴ ተክል ምግቦች

Fidge filled up with green vegetables and fruit

አረንጓዴ ተክሎች ለጤና ጠቃሚ መሆን የማያጠራጥር ሲሆን፥ ለዛሬ ስለተክሎቹ አይነትና ጥቅሞቻቸው በጥቂቱ እናካፍልዎ።

ጥቅል ጎመን፦ የተለያዩ አይነት የጎመን ዝርያዎች ያሉ ሲሆን፥ ሁሉም በቫይታሚን ኤ፣ ሲ፣ ካልሲየም እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ናቸው።

በአውስትራሊያ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው እነዚህን አረንዴ ተክሎች መመገብ ካንሰርን ጨምሮ ለተለያዩ አይነት በሽታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል።

ቆስጣ፦ ቆስጣን መመገብ የጉበት፣ የአንጀት፣ የማህፀን እና የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን፥ ከእነዚህም በተጨማሪ ለጡንቻ መዳበር ጠቃሚነት አለው።

ሰላጣ፦ ሠላጣን መመገብ ለደም ግፊት ህመምተኞችና ከፍተኛ የሠውነት ክብደት ላላቸው ሰዎች በብዛት ይመከራል።

እንዲሁም ሰላጣ በውስጡ የያዘው ካልሲየምና ፎስፈረስ ለአጥንት ጤናማነት ጠቃሚ ሲሆን፥ ሴሊኒየም የሚባለው ንጥረ ነገር ደግሞ የሰውነታችን ቆዳ ቶሎ እንዳያረጅና የአንጀት ካንሠርን የመከላከል አቅም እንዲኖረው ያደርጋል።

ጎመን፦ ጥቁር ጎመን በውስጡ ቫይታሚን ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ3፣ ቢ6 ፣ሲ እና ሌሎች እንደ ፖታሲየም፣ ካልሽየም ፣ ፎስፈረስ እና አዮዲንን ይይዛል።

በበርካታ ንጥረ ነገሮች የዳበረው ጎመን የሰውነት የበሽታ የመከላከል አቅምን የሚያጠነክርና በሽታንም የሚከላከል የተክል አይነት መሆኑም ነው የሚነገርለት።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.