ስቅታን በቀላሉ ለማስቆም

በሆድና በሳምባ መካከል የሚገኝ ጡንቻ ወይም ዲያፍራም ሲሰበሰብ (ሲጨማደድ) ልንቆጣጠረው በማንችለው ሁኔታ ስቅታ ይፈጠራል፡፡ በሚገባ ስንጠግብ (ማለትም ሆዳችን በምግብ ሲወጠር)፣ የጨጓራ የሙቀት መጠን ሲቀየር፣ አልኮል መጠጥና ሲጋራ በዝቶ ሲወሰድ፣ ከመጠን በላይ መዳከም ሲኖር ወይም ከባድ የፍራቻ ስሜት ውስጥ ስንገባ ስቅታ ይፈጠራል፡፡
በቀላሉ ስቅታን ማቆም የምንችልባቸውን መንገዶች በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ፡፡
• የወረቀት ቦርሳ (የካኪ ፖስታ) ውስጥ መተንፈስ፤ ማለትም አፍናን አፍንጫችንን በከረጢቱ ውስጥ አድርገን መተንፈስ፡፡
• በተለምዶ ትንፋሽን ይዞ ከመቆየት ባሻገር ሎሚን መምጠጥም ሌላኛው መፍትሄ ነው፡፡
• ከምላሳችን ስር አንድ ማንኪያ ስኳር ወይም ማር ማድረግና መምጠጥም ስቅታን ሊያስቆም ይችላል ፡፡
• ጆሮን ማሻሸት ሌላኛው መፍትሄ ነው፡፡ ይህን በማድረግዎ የነርቭ ስርአትን በማነቃቃት ሆድ ላይ የሚፈጠር ጫናን መቀነስ ይቻላል።
• ጉሮሮ አካባቢ ላይ አነስ ያለ በረዶን ለተወሰኑ ጊዜያት ማሸትም ስቅታን ለማስቆም ይረዳል።
• አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሀን አጎንብሶ መጠጣት፡፡
• በመምጠጫ ወይም በስትሮ ውሀን መጠጣትና በምንጠጣበት ጊዜ ጆሯችንን በጣታችን ደፍነን መያዝ፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ (Doctor Alle)

Advertisement

8 Comments

Comments are closed.