ካናቢስ የዘረመል መዋቅርን ያዛባል

የዱክ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ንጥረ ነገሩ የወንድ የዘር ፍሬ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም ካናቢስ የሚጠቀሙ ሰዎች ልጅ ለመውለድ ከማሰባቸው ስድስት ወራት ቀደም ብለው መጠቀም ቢያቋርጡ እንደሚመረጥ አንስተዋል።

ይህ ተጽዕኖ ያሳድራል የተባለው ንጥረ ነገር በካናቢስ ውስጥ የተለየ ሲሆን፥ “ቴትራሃይድሮካናቢኖል” በመባል ይጠራል፡፡

በሽንት ውስጥ መጠኑ እየጨመረ ሲሄድ የዘረመል መዋቅርን በዚያው መጠን እንደሚያዛባም ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ንጥረ ነገሩ በታዳጊዎች፣ በነፍሰጡር ሴቶች እና በአዋቂዎች ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ለመመርመር ይረዳል ተብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም የተጠኑ ጥናቶች እንደሚያመለክቱትም ሲጋራ ማጤስ፣ ጸረተባዮች፣ ውፍረትና ሌሎች ጉዳዮች በዘር ፍሬ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ይነገራል፡፡

በአሁኑ ወቅት ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ካናቢስ በህጋዊ መንገድ ለመድሐኒትነት እያዋለ ይገኛል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ስካይኒውስ

በአብርሃም ፈቀደ

Advertisement