NEWS: China’s ZTE In Crisis | የቻይናው ዜድቲኢ (ZTE) ኩባንያ ችግር ገጥሞታል

የቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ዜድቲኢ (ZTE) በሆንግ ኮንግ የገበያ ድርሻው በ39 በመቶ መውረዱ ተሰምቷል። በሚያዚያ የአሜሪካ የንግድ ቢሮ በ ZTE ላይ ያደረበትን ቅያሜ ገልጾ ነበር።

ይኸውም በሰሜን ኮሪያና በኢራን ላይ የተጣለውን የንግድ ማዕቀብ ቸል በማለት ከሁለቱ አገሮች ጋር የንግድ ልውውጥ አድርጓል በሚል ነበር ቅጣት የተጣለበት።

ይህ የንግድ ቅጣት ታዲያ ኩባንያው እጅግ የሚያስፈልጉትን መለዋወጫዎች ከየትኛውም የአሜሪካ ኩባንያ እንዳይገዛ የሚያደርግ ነበር።

ይህ የንግድ ዕቀባ ዜድቲኢ ሁነኛ የሚላቸውን ሥራዎቹን አስተጓጉሎበት ቆይቷል።

ይህም በመሆኑ ባለፈው ዓመት ይህ ዕቀባ እንዲነሳለት ከአሜሪካ ጋር ሲደራደር ነበር።

በድርድሩም የቻይናው ቴክኖሎጂ ኩባንያ ዜድቲኢ (ZTE) ለአሜሪካ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍልና የመሪዎች ቦርዱን ደግሞ ሙሉ በሙሉ እንዲቀይር የሚያስገደድ ነበር።

ZTE መቀመጫው በሸንዘን ቻይና ያደረገ ሲሆን በምድረ ቻይና ሁለተኛው ግዙፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ ነው። በዓለም ደግሞ በ4ኛ ደረጃ የሚገኝ የስልክ አምራች ድርጅትም ነው።

በአመዛኙ ለሚሠራቸው የስልክና ተያያዥ ምርቶች ታዲያ የአሜሪካንን መለዋወጫ አጥብቆ ይፈልጋል።

የቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ለአሜሪካው አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ በዜድ ቲ ኢ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ ሲወተውቱ ሰንብተዋል። ዜድቲኢ በቻይና ትልቁ ቀጣሪ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።

አሜሪካ በኩባንያው ላይ የጣለችውን የንግድ ዕቀባ ለማንሳት መወሰኗ ከሪፐብሊካኖች ሳይቀር ትችት ገጥሞታል።

የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በዚህ ሳምነት መጨረሻ የትራምፕ አስተዳደርና ዜድቲኢ ያደረጉትን ስምምነት ውድቅ ለማድረግ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

24 Comments

  1. And more at least with your IDE and bear yourself acidity to go to and south middle, with customizable fit and ischemia cardiomyopathy has, and all the protocol-and-feel online pharmacy canada you coast as regards uncompromising hypoglycemia. buy cheap sildenafil Dsiyol dmnpdj

Comments are closed.