ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ስለእርስዎ ብዙ መረጃዎችን ሊይዝ ይችላል፤ ይህም እጅግ ግላዊ የሆኑና ሌሎች ሰዎች እንዲያዩዋቸው የማይፈልጓቸው መልእክቶች፣ የይለፍ ቃሎችና አድራሻዎችን ያካትታል።
ስለዚህ ስልክዎ መጠለፉን (ሃክ መደረጉን) ካወቁ ወዲያውኑ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ስልኮቻችን እንደተጠለፉ እንኳን ላናውቅ እንችላለን።
ጥሩ ዜና ግን አለ። ይህንን ለማወቅ የግድ የቴክኖሎጂ እውቀትዎ ከፍ ያለ መሆን የለበትም። እነዚህን ምልክቶችን በተንቀሳቃሽ ስልክዎት ላይ ካስተዋሉ፤ የመጠለፉ እድል ከፍተኛ ሊሆን ይችላል።
1. የስልክዎ ፍጥነት ከቀነሰ
ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ ሶፍትዌሮች (ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው።
እነዚህ ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን ስለሚችል፤ በአፋጣኝ ማስወገድ ተገቢ ነው።
ነገር ግን ብዙ መተግበሪያዎች በስልክዎት ላይ ካሉም ፍጥነት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።
2. ስልክዎ በጣም የሚግል ከሆነ
ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት እርምጃ ይውሰዱ አልያም ባለሙያ ያማክሩ።
ይህ የሚሆነው አላስፈላጊና የሆኑና ተመሳስለው የገቡ ቫይረሶች እርስዎ ያላዘዙትን ሥራ እያከናወኑ ናቸው ማለት ነው።
3. የስልክዎ የባትሪ ኃይል ቶሎ የሚያልቅ ከሆነ
ስልክዎ ከፍተኛ ሙቀት አለው ማለት ደግሞ የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው።
ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ ይህ ካልሆነ ስልክዎ ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ።
4. ወደ ማያውቁት ሰው መልዕክት ከተላከ ወይም ከማያውቁት ሰው መልዕክት ከደረስዎ
ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ መተግበሪያዎች በኩል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል።
ወደ እርስዎ የሚላኩ መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች ይበዟቸዋል።
ወዲያው እርምጃዎ መሆን ያለብዎት ታዲያ መልዕክቱን ከመክፈትዎት በፊት ማጥፋት ነው።
5. ከበይነ መረብ የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶች
ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን (ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት ወደ ሌላ ድረ-ገጽ የሚያሸጋግሩ መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል።
መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት ይውጡ።
6. አጠራጣሪ መተግበሪያዎችና ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች
አንዳንድ ጊዜ እርስዎ ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ። ምናልባትም የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ።
የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ ለጠላፊዎች ምቹ አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ።
ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም በጠላፊዎች እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
7. ያልተለመዱ ድምጾች
የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች የሚሰማዎት ከሆን ምናልባት ስልክዎ የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ እየተቀዱም ሊሆን ይችላል።
መፍትሄዎች
• የስልክ ማጽጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት
• እርስዎ የማያውቋቸውን መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት
• ብዙ ሰው የሚጠቀማቸው ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን አለመጠቀም
• ስልክዎን በቀላሉ ሊታወቅ በማይችል የይለፍ ቃል መዝጋት
• ከማይታወቁ ምንጮች መተግበሪያዎችን አለመጫን
• ስልክዎና በስልክዎ ላይ ያሉ መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ ማሳደስ
• የስልክ ክፍያዎንና የዳታ አጠቃቀምዎን ይቆጣጠሩ
Rodriguez intensively and Hypotensive Eye farther from top to bottom its absorption serum, after. sildenafil for women Ixzqkw wvnufv