ኤሌፋንታንሲስና ሪቨር ብላይንድነስ ለተባሉት በሽታዎች አዲስ መድሃኒት ተገኘ

ኤሌፋንታንሲስና ሪቨር ብላይንድነስ ለተባሉት በሽታዎች አዲስ መድሃኒት ተገኘ፡፡

ኤሌፋንታንሲስ የተባለው በሽታ የሰወችን እጅ፣ አግርና ጡት የሚያሳብጥ ሲሆን ÷ ሪቨር ብላይንድነስ የተባለው በሽታ ደግሞ ከቆዳ ስር የሚያብጥና የሚያሳክክ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዚኅም በዓለም አቀፍ ደረጃ 157 ሚሊየን ያህል ሰዎች በእነዚህ በሽታዎች መበከላቻን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
የበሽታዎች መንስኤም ጥገኛ ትል ሲሆን÷ ህክምናው ሳምንታትን የሚፈጅና መድሃኒቶቹ ደግሞ የጎንዮሽ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደነበረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በሊበር ፑል ዩኒቨርሲቲ የትሮፒካል መድሃኒት ትምህረት ክፍልና የለንደን ኢምፐሪያል ኮሌጅ ተመራማሪዎቹ ከላይ የተጠቀሱትን በሽዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መፈወስ የሚያሥችልና የጎንዮሽ ጉዳቱ ውስን የሆነ መድሀኒት ይፋ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

መድሀኒቱ በጥገኛ ትሉ ውስጥ የሚገኘውን ውልባቺያ የተባለውን ባክቴሪያ እንደሚያጠፋ ነው ተገለጸው፡፡

ባክቴሪያው ከጥገኛው ትል ወደ ሰዎች ሰውነት ውስጥ ገብቶ በመራባት ለበሽታው እንደሚያጋልጥ ነው ዘገባው የሚያመላክተው፡፡

የአዲሱ መድሀኒት ግኝት ወደ ፊትም የተሻሻሉ መድሀኒቶችንና የክትባት አማራጮችን ለማግኘት መንገድ የሚከፍት ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

6 Comments

Comments are closed.