ለ47 ዓመታት ያህል ያልተከፈተው የገና ስጦታ – Christmas Present Which Hasn’t Been Opened for 47 Years

                                                               

ብዙዎቻቸን የተሰጠንን ስጦታ ከፍተን ውስጡ ያለውን ለማየት እጅግ ጉጉ ነን።

ከወደ ካናዳ የተሰማው ግን ከዚህ ለየት ያለ መሆኑን ነው የተነገረው።

ይህም አንድ ካናዳዊው ከ47 ዓመት በፊት ከሴት ጓደኛው ያገኘው የገና ስጦታ እስከ አሁን አልከፈተውም።

አድሪያን ፔርስ በአውሮፓውያን 1970 በ17 ዓመት እድሜው በቶሮንቶ ግዛት በሚገኘው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ነበር ጓደኛው የተለየችው። 

በዚያን ወቅት የነበረችው የመጀመሪያዋ የሴት ጓደኛው፥ በፖስታ መልክ በማሸግ የገና ስጦታ ካበረከተችለት በኋላ ግንኙነታቸውን ወድያውኑ ማቋረጡ ተነግሯል። 

በዚህም አድሪያን ፔርስ በጣም አዝኖ እንደነበር እና በመለያየታቸው ምክንያት ለ47 ዓመታት በብስጭት እንደነበረ ነው የተጠቆመው።

ስለሆነም ስጦታው በቀላሉ በገና ዛፍ ሥር ከጣለው በኋላ ያልተከፈተ መሆኑን የሚያስታውሰው በገና በዓል ቀን ብቻ ነበር።

ለቤተሰቦቹም ፈፅሞ እንደማይከፍተው በየጊዜው ይናገራቸው እንደነበር ተጠቁሟል።

በዚህም የገና ስጦታው ሳይከፈት 47 ዓመታት አልፎታል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement