የደም ግፊት መጠንዎን ለመቆጣጠር – How to Control your blood pressure.

                                                  

 የሚወስዱትን የጨው መጠን ይቀንሱ

የደም ግፊት መጠን መጨመርን ለመቆጣጠር ከሚረዱ ሁኔታዎች አንደኛው የሚመገቡትን የጨው መጠን መቀነሱ ነው፡፡ ጨዋማ ምግቦችን የምናዘወትር ከሆነ ለደም ግፊት የምንወስደውንም መድኃኒት ሥራ ሊቀንስ እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

 መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያድርጉ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ ለደም ግፊት መጠን መቀነስ ጠቃሚ ነው፡፡ በቀን ቢያንስ 30-40 ደቂቃ በሳምንት ለ4-5 ቀናት የሚሆን እንቅስቃሴን ማድረግ የደም ግፊትን የመቆጣጠሪያ አንደኛው መንገድ ነው፡፡

 የአልኮል መጠን ይቀንሱ

በተደጋጋሚ እና በብዛት የአልኮል መጠን መጠቀም ለደም ግፊት መጠን መጨመር ያጋልጣል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለደም ግፊት መቆጣጠሪያ የምንወስደውን የመድኃኒት ውጤታማነት ይቀንሳል፡፡ ስለዚህም የሚወሰዱትን የአልኮል መጠን መቀነስ ይገባል፡፡

 ጭንቀት

ጭንቀት ለደም ግፊት መጠን መጨመር ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ይህንንም ለመቆጣጠር ራስዎን በማዝናናት ለነገሮች መፍትሔ ለማበጀት በመሞከር ጭንቀትዎን መቀነስ ይችላሉ፡፡

 ሲጋራ ማጤስ

ሲጋራን ማጤስ ለልብ እና ለሌሎች የጤና ችግሮች ተጋላጭነት በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚጨምርና ማጤስን ማቆም ይመከራል፡፡

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement