ሎሚ የተቀላቀለበት ውሃ ክብደትን ለመቀነስ – Lemon Water Help To Lose Weight

                                                     

ሎሚ የተጨመረበት ውሃ መጠጣት በየቀኑ የካሎሪዎችን መጠን ለመቀነስ ይረዳል።በየቀኑ በቂ ንፁህ ውሃ መጠጣት ክብደት ለመቀነስ እንደሚረዳ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።ሎሚ የተጨመረበት ውሃ መጠጣት ደግሞ የተመገብነው ምግብ ተሎ ለመፍጨት፣ ጉልበት ለመጨመር እና ትኩረትን ለማሻሻል ይጠቅማል።

ስለዚህ ባለሙያዎች ስለ የሎሚ ውሃ እና ጥቅሞቹ የተነገሩት ማወቅ ያለብዎት ነገር እንዲህ ቀርበዋል።

1. የሎሚ ውሃ የካሎሪ መጠን ይቀንሳል
ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ሎሚ የተጨመረበት አንድ ብርጭቆ ውሃ የካሎሪ መጠኑ ከስድስት አይበልጥም። ይህም ክብደት ለመቀነስ በጣም ውጤታማ ነው።በተለይም የፍራፍሬ ጭማቂዎችን እና የሶዳ መጠጦችን በሎሚ ውኃ የምንተካ ከሆነ በየዕለቱ በ200 ካሎሪ የምንወስደውን እንዲቀንስ ይረዳል ተብሏል።

2. የሎሚ ውሃ መጠጣት የምግብ መፍጨት ያፋጥናል
ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በሰውነት ውስጥ ጥሩ የውኃ መጠን መኖር ሚቶኮንድራ( mitochondria) ተብሎ የሚጠራውን ሰውነት ጉልበት እንዲኖረው የሚያስችል ህዋስ እንዲሻሻል ያደርጋል። ይህም የምግብ መፈጨትን በማሻሻል ክብደት ለመቀነስ ይረዳል።

3. የሎሚ ውሃ በሰውነት ውስጥ ያለውን የፈሳሽ መጠን ያሻሽላል
በሰውነታችን ውስጥ የውሃ መጠን መቆየት ከሰውነታችን ቆሻሻን ለማጓጓዝ በጣም አስፈላጊ ነው።በተጨማሪም የአካል እንቅስቃሴዎችን ለማሻሻል እና የሰውነት ሙቀትን ለመቆጣጠር የሚረዳ አንዱ መንገድ ነው።
ከዚህም በላይ በሰውነት ውስጥ ክብደትን ለመቀነስ የሚረዳ የፈሳሽ መጠን እንዲኖር የሚያደወርግ ነው።

4. የሎሚ ውሃን በመጠጣት የበለጠ የደስታ ስሜት ማግኘት ይቻላል
ሎሚ የተጨመረበት ውሃ ወይም ውሃ መጠጣት ካሎሪዎች በመቀነስ የረሃብ ስሜትን ያጠፋል።የረሃብ ስሜት ማጥፋቱም ሰዎች ተጨማሪ ምግብ እንዳይመገቡ እና በዚህም ሊወስዱት የሚችለውን ተጨማሪ ካሎሪያ እንዲቀር የሚያደርግ ነው።

5. የሎሚ ውሃ የሰውነት ክብደት ይቀንሳል
ሎሚ የተጨመረበት ውሃ መጠጣት በሰውነታችን ውስጥ በቂ ፈሳሽ እንዲኖር በማድረግ እና የምግብ መፈጨትን በማፋጠን የሰውነት ክብደት እንዲቀንስ ያስችላል። ጥናቶች እንደሚያመለክቱትም በቂ ውሃ መጠጣት ከስፖርት እና ከአመጋገብ ስርዓት ቁጥጥር ውጪ ብቻውን የሰውነት ክብደት እንዲቀነስ ያደርጋል።

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement