ሙዚቃ ማዳመጥ የሚስገኛቸው የጤና ጥቅሞች::

                                        

የሙዚቃ የህክምና ባለሙያው ዶክተር ስቴራ ኮምፕተን ዲክንሰን ሙዚቃ በርካታ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ይናገራሉ፡፡

ከእነዚህም መካከል፦

1. ከፍተኛ የሆነ ጭንቀትን ያስወግዳል

በህክምና ተቋማት፣ በስራ ቦታ እና በሌሎች ስፍራዎች ሙዚቃ መጫወት ወይም ማዳመጥ የራሱ የሆነ ምት፣ ቅላጼ እና ስበት ስላለው ትኩረትን ይሰበስባል፡፡

በመሆኑም ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት ያጋጠማቸው ሰዎች በራሳቸው ሙዚቃ ቢዘፍኑ ወይም ቢያዳምጡ እፎይታን ያገኛሉ ነው የሚሉት ዶክተር ዲክንሰን፡፡

2. የአንጎል ህዋሳት እንዳይዳከሙ ያደርጋል

በርካታ ሰዎች ለአዕምሮ መሳት እና እንዳይንቀሳቀሱ ለሚያደርግ የሰውነት ድካም ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡

እንደዚህ ዓይነት የጤና ጉድለቶች እንዳያጋጥሙ እና የአንጎል ህዋሳት መዳከም ከተፈጠረም ሙዚቃ ለመጫወት መሞከር ወይም ማዳመጥ ወሳኝ መሆኑ ተነግሯል፡፡፡

3. መነቃቃትን ይፈጥራል

ሙዚቃ ለሁሉም ሰው በሚባል ደረጃ ተገቢ የሆነ የጥበብ ዘውግ ነው፡፡

እያንዳንዱ ሰው ካጋጠመው ድብርት ለመነቃቃት ሙዚቃ መጫወትን ወይም የሚወደውን ዘፈን ማዳመጥን በየዕለቱ ተግባራዊ ለማድረግ ይሞክራል፡፡

በአንዳንድ ቦታዎችም በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ ሙዚቃዎችን ለድብርት ማስወገጃ ሲጠቀሙ ይታያል፡፡

4. የማስታወስ ችሎታን ያሳድጋል

በተለያየ ጊዜ በሕይወታችን ውስጥ ያዳመጥናቸውን ሙዚቃዎች በድጋሚ በምንሰማበት ጊዜ ወደ ኋላ መለስ ብለን የተለያዩ አጋጣሚዎችን ለመስማት እንሞክራለን፡፡

ይህ ደግሞ አንጎላችን በአጠቃላይ የማስታወስ አቅሙ እንዲጎለብት እና የመርሳት ችግርን እንዲቀረፍ ያግዛል፡፡

5. የተወሰኑ የአዕምሮ ጤና ችግሮችን ለማከም ያገለግላል

የሙዚቃ ህክምና በተወሰነ መልኩ በአዕምሮ ውስጥ ባለው እሳቤ እና በውጪው ዓለም ባለው እውነታ መጣረስ የሚያጋጥመውን የስኪዞፍሬኒያ ህመምን ለማከም ያገለግላል፡፡

ስሜትን ለማረጋጋት፣ የእሳቤ ሂደትን ለማስተካከልም ሙዚቃዊ ህክምና ወሳኝ ነው፡፡

6. ልጆች በርካታ ነገሮችን እንዲማሩ በር ይከፍታል

በሙዚቃ አጋዥነት ልጆች ፊደላትን፣ ቃላትን እና ዓረፍተ ነገሮችን እንዲገነዘቡ ይደረጋል፡፡

ይህ ኣይነቱ ስራ በአብዛኛው በቅድመ መደበኛ እና በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቢዘወተር መልካም ነው፡፡

ህጻናት አፋቸውን እንዲፈቱ፣ ስለ ቁሳቁስ፣ ስለ አካባቢያቸው እና መሰል ነገሮች ያላቸውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ ሙዚቃ ወሳኝ ነው።

ከዚህም ባሻገር በአዕምሮ ንቃታቸው ዘገምተኛ የሆኑ ልጆች እንዲስተካከሉ እና በትምህርታቸው ጎበዝ እንዲሆኑ ሙዚቃዊ ትምህርቶችን ቢሰጡ ተገቢ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡

7. ማህበራዊ ግንኙነትን ያጠናክራል

ሙዚቃ በብቸኝነት ለማሳለፍ የሚያግዘውን ህል ማህባረዊ ግንኙነትን ለማምጣትም ወሳኝ ነው፤ በተለይም በኮንሰርቶች ላይ ከሰዎች ጋር ተሰባስቦ መታደም፣ በጋራ ምርጫ ሙዚቃን ማዳመጥ ግለኝነትን ወደ ማህበራዊነት ለማሳደግ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡

Advertisement