የዓለም ጡት የማጥባት ሳምንት

                                                           

“ጡት የማጥባትን ባሕል በጋራ ዘላቂ እናድርግ!” በሚል መሪ ቃል ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 1 ቀን 2009 ዓ.ም እየተከበረ ነው፡፡

የጡት ማጥባት ቁልፍ መልዕክቶች፡-
1. ልጅዎን እንደ ወለዱ ወዲያውኑ በአንድ ሰዓት ውስጥ ጡትዎን ማጥባትዎ፡-
ጡትዎ በደንብ ወተት እንዲያመነጭ ከወሊድ በኋላ የሚከሰትን የደም መፍሰስ ይቀንሳል፡፡
2. የመጀመሪያውን ቢጫ መሰል የጡትዎን ወተት /እንገር/ ለልጅዎ ማጥባትዎ፡-
እንገሩ ለሕጻኑ የሚያስፈልገውን የበለጸገ ንጥረ-ምግብ በበቂ ሁኔታ የያዘ በመሆኑ የሕጻኑን በተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅሙን ያዳብርለታል፡፡ በተጨማሪም የሕጻኑን አንጀት በማለስልስ የመጀመሪያው አይነ ምድር እንዲወገድ ያደርጋል፡፡ 
3. ልጅዎ መጥባት በፈለገ ጊዜ ሁሉ ያጥቡት፡፡ ቀንና ማታን ጨምሮ ከ10-12 ጊዜ ያጥቡት፡፡
ይህን ማድረግዎ ጡትዎ በቂ ወተት እንዲያመነጭና እንዲያፈስ/እንዲዎጣና በእናትና በልጅ መካከል የሚኖረውን ፍቅር ያደረጃል
4. ልጅዎን በሚያጠቡበት ጊዜ በአግባቡ ማቀፍና ጡትዎን ማጉረስ ያስፈልጋል፡፡
ይህን ማድረገዎ ህጻኑ በደንብ ጡት እንዲስብና ምቾት እንዲሰማው ከማድረጉም በላይ የጡትዎ ጫፍ እንዳይሰነጠቅና እንዳይቆስል ይረዳል፡፡
5. ልጅዎን ጡት ሲያጠቡ አንዱን ጡት ባዶ እስኪሆን ካጠቡ በኋላ ሌላውን ጡትዎን ያጥቡ፡፡
ምክንያቱም ቀድሞ የሚወጣው ቀጭን ወተት የህጻኑን የውሀ ጥም/ ፍላጎት የሚያረካ ሲሆን በኋላ የሚመጣው ወፍራም ወተት ደግሞ የምግብ ፍላጎቱን የሚያሟላ በመሆኑ ነው
6. ልጅዎ ስድስት ወር አስኪሞላው ድረስ ከጡት ወተት ሌላ ምንም ዓይነት ተጨማሪ ነገር አይስጡ፤ ውኃም ቢሆን፡፡
– የጡት ወተት ለሕጻኑ እድገትና ጤንነት የሚያሰፈልገውን በቂ ውሃና ምግብ የያዘ ነው፡፡
– ለሕጻኑ ውሃ ወይም ሌላ ፈሳሽና ምግብ ቢሰጡ ለተቅማጥና መሰል በሽታዎች ያጋልጠዋል፡፡

 

ምንጭ:- ጤናችን

 

 

Advertisement