ባህላዊዉ የገና በዓል አከባበር

                   

አዜብ ታደሰ ልደት አበበ

በኢትዮጵያዉያን ዘንድ የበዓላት ሁሉ በኩር የሆነዉ የልደት ማለት ገና በዓል ትናንት በደማቅ ተከብሮ ዉሎአል። በኢትዮጵያ የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች አርባ ቀን ፆመዉ የምሥራች የዓለም ቤዛ ክርስቶስ ተወለደ ሲሉ የልደትን በዓል በምሥራች በደስታ ያከብሩታል ተድላዉ ደስታዉም የተጋነነ ነዉ ሲሉ የሃይማኖት አባቶች ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ የገና በዓል ሲከበር ዘመድ አዝማድ አመች በሆነዉ መንገድ ሁሉ እየተገኛኘ እንኳን አደረሰህ እንደምን ከረምክ ልጆች አዝመራዉ እህሉ ጤንነት እንዴት ነዉ የሚባባልበት በተለይ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ወጣቶች እንደያቆብ በትር የተሽለመለመ በንግን እንዲሁም ሩር አዘጋጅተዉ የገና ይጫወታሉ ያሉልንን እንግዶች በዕለቱ ዝግጅታችን ይዘን ቀርበናል ።

የገና በዓል ሲቃረብ ለበዓሉ የሚሆን ጠላ ይጠመቃል በዋዜማዉ ዳቦ ይደፋል፤ አቅምም ያለዉ ጠጅም ይጥላል። አሁን አሁን በከተማዉ በተለይ በገና በዓል ዶሮ ወጥ ማዘጋጀት ተለመደ እንጅ ኢትዮጵያ ዉስጥ በገና እና በስቅለት በዓል በአብዛኛዉ በማህበር ሆኖ እርድን በቅርጫ መከፋፈል የተለመደ ነዉ። ገና የሚለዉ ቃል የተወሰደዉ ከግዕዝ ነዉ ያሉን ሊቀ ኽሩያን በላይ መኮንን ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዉናል።

መምህር ካሳይ ገብረ እግዚአብሄር በበኩላቸዉ ከበዓል አከባበሩ መሰረት ስነነሳ የገና ማለት የልደት በዓል በተለይ ለኢትዮጵያዉያን ብዙ ታሪክ አለዉ ብለዉናል። 

እንደ ሊቀ ኽሩያን በላይ መኮንን የገና በዓል አከባበር የቤት የምግብ አዘገጃጀቱ በከተማዉም ሆነ በገጠሩ የራሱ ባህል አለዉ ፤ ግን በገጠሩ የድሮዉን ዋናዉን ባህሉን ሳይለቅ ይገኛል ያሉት በተለይ በገና ግዜ ለገና በዓል ማድመቅያ ተብሎ የሚቆረጥ የጥድ ዛፍን እንደሚቃወሙ ተናግረዋል። ማሕበረሰባችን የተቸገረን የታመመን የመርዳት ልዩ ባሕል አለዉ ሲሉ የሚናገሩት ሊቀ ኽሩያን በላይ መኮንን በልደት በዓል በተለይ በገጠር የተቸገረን የማብላት የማስጠጋት የመጦር ባህልም አለን ብለዉ በሰፊዉ አጫዉተዉናል። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማOeቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

ምንጭ:- DW

 

Advertisement