አባይ ፀሐዬ፡ መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው

ከህወሓት መስራቾች አንዱና የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት እንዲሁም በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሠሩት አቶ አባይ ፀሐዬ ከወራት በፊት ተጀምሮ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ፖለቲካዊ ለውጥና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ቢቢሲ አሁን በኢትዮጵያ ባለው ለውጥ ላይ ህወሓት እንደ እንቅፋት ተደርጎ ይቀርባል። ለውጡን እንዴት ያዩታል ?

አቶ አባይ ፀሐዬ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ለውጥ ኢህአዴግ ‘ብዙ በድያለሁ፤ አጥፍቻለሁ’ ብለው አራቱ አባል ድርጅቶች ገምግመው ሕዝብን ይቅርታ ጠይቀው የተጀመረ ነው። ኢህአዴግ በዚህ ደረጃ እራሱን እንዲፈትሽ፣ መፈትሄ እንዲያሰቀምጥና ሕዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅ ህወሓት የጎላ ድርሻ ተጫውቷል።

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ግምገማ በጣም ጥልቀትና ስፋት ነበረው። ሌሎችም እንደ ፈር ቀዳጅና እንደ ማሳያ ነው የወሰዱት። ስለዚህ ህወሓት የለውጥ ጀማሪ፣ በለውጡ የነቃ ተሳትፎና አብነታዊ ሚና ተጫውቷል። ከዚያ በፊት ህወሓት በትግራይ ሕዝብ ተዓማኒነት እስኪያጣ ድረስ የከፋ ችግር ነበረበት፤ በአገር ደረጃም የኢህአዴግ አካል ሆኖ ብዙ ስህተት የፈፀመ ድርጅት ነው። ስለዚህ ስህተት አልፈፀምኩም፣ ጉድለት የለኝም፣ ያልተገባ ነገር አልሠራሁም አላለም። ይሄን ሁሉ ዘርዝሮ ለኢህአዴግ አቅርቧል፤ ለሕዝቡም ይፋ አድርጓል።

ከዚያ በኋላም ህወሓት የኢህአዴግ አካል ሆኖ ለተሠሩ ስህተቶችም ከግምገማና ከሂስ አልፎ ዶክተር ዐብይ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ሲመረጥ፤ በጋራ የመረጥነውን መሪ በፀጋ ተቀብሎ ደግፏል። በፓርላማም ድምፁን ሰጥቶ ‘የጋራ መሪያችን ነው፤ የጋራ ለውጥ ነው’ ብሎ በቅንነት በሕግ አክባሪነት ለውጡን ደግፏል።

በተሠሩ መልካም ሥራዎች ላይም ህወሓት ጉልህ ሚና ነበረው። ለምሳሌ ከኤርተራ ጋር የተደረገው የሰላም ስምምነት፣ በውጭ የነበሩ ተቃዋሚዎች እንዲመጡ፣ በነፍጥ ሲፋለሙ የነበሩ ወደ ሰላም እንዲመጡ የተደረገው ጥረት መነሻው የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚና የኢህኣዴግ ምክር-ቤት ውሳኔ ነው።

አፈፃፀሙ ላይ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶክተር ዐብይ ላቅ ያለ ጥረት አድርገው ውጤታማ እንዲሆን ሠርተዋል። ይህንንም ህወሓት አድንቆና አመስግኖ ተቀብሎታል። ከዚያም አልፎ የእሰረኞችን መፍታት አድንቆና ተቀብሎ ነው የሄደው።

እንዲሁም የባለስልጣናት ሽግሽግ ሲደረግ፤ በርካታ ከስልጣንና ከሚኒስትርነትም የተነሱ ሰዎች ፣ ከዚያ በታች ባሉ የሲቪል ኃላፊነት ቦታዎችም፣ ከሠራዊትም በርካቶች ከህወሓት ነው የተነሱት። ይሄንንም በፀጋ ነው የተቀበለው። ዲሞክራሲያዊ ነን በሚሉ ሃገራት አንድ ፓርቲና አንድ ግለሰብ ከሠራዊት ወይም ከድህንነት ኃላፊነት ሲነሳ ስንት ኩርፍያና ግርግር ይፈጠራል። ህወሓት ግን አካሄዱ ላይ ይስተካከል ብሎ አስተያየት ሰጥቷል፤ ነገር ግን ተግባራዊ አድርጎታል። የቱ ጋር ነው ለውጡን የተቃወመው?

አፈፃፀም ላይ የታዩ ጉድለቶች ነበሩ እነርሱም ደግሞ ይታረሙ ብሏል። ያለፉትን 27 ዓመታት ምንም እንዳልተሠራ ይነገራል “ይሄ ትክክል አይደለም፤ አብረን ነው የሠራነው” በሎ ሃሳብ አቅረቧል። እንዴ ህወሓት ነው እንዴ የሰራው? ህወሓት ብቻ ነው እንዴ የሚከፋው? ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብም’ኮ የለፋበት ነው። ይሄ ሲነቋሸሽ ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ ልዩ ቅሬታ፣ ልዩ መከፋት የሚሰማቸው መስሎ የሚታያቸው ካሉ ትክክል አይደሉም። ይሄ ሚዛኑን ይጠብቅ ማለት ለውጥ መቃወም አይደለም።

ቢቢሲ፡ ለምሳሌ የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ላይ ህወሓት ተቃውሞ አሰምቶ ነበር …

አቶ አባይ ፀሐዬ የኢትዮ-ኤርትራ ሰላም አፈፃፀሙ ላይ የተወሰኑ ጉድለቶች ነበሩ። ሕዝብን ብናማክር ይጠቅም ነበር። በትግራይ በኩል ያለው በር ይከፈት፤ ግንኙነቱ ከአዲስ አበባ ብቻ አይሁን፤ አሰብ ብቻ ሳይሆን ምፅዋም ይከፈት። የትግራይ ድንበሮች ክፍት ይሁኑ የሚል ነው። ይህንን ሃሳብ ማቅረብ ለውጡን መቃወም አይደለም።

ቢቢሲ፡ በውጭ የነበሩ የታጠቁ ኃይሎች ሃገር ቤት ሲገቡስ ደስተኞች ነበራችሁ?

አቶ አባይ ፀሐዬ ውጭ የነበሩት ተቃዋሚ ኃይሎች በአጭር ጊዜ እንዲገቡ መደረጉ ህወሓትም የትግራይ ሕዝብም አድንቋል። አብዛኛው በይቅርታና በፍቅር መንፈስ፤ አንድነትን በመፍጠርና ዲሞክራሲን በማስፋት መንፈስ ነው የመጣው። ጥቂቶቹ ግን ከእነ ቂም በቀላቸው ነው ያሉት። ኢህአዴግ ላይ በጠቅላላ ቂምና በቀል ሊወጡ የሚፈልጉ አሉ። ይሄ ደግሞ የለውጡ መፈክር በፍቅርና በይቅርታ እንዲሄድ የሚለውን ሃሳብ ይፃረራል። ስለዚህ ይሄም ትክክል አይደለም ‘ተው’ መባል አለባቸው። ጥቂቶች ናቸው። ስለዚህ ይሄ ይታረም ማለቱ ምንድን ነው ክፋቱ?

ቢቢሲ፡ ህወሓት ለውጡን እንዴት ነው የሚረዳው? በተደጋገሚ የሕግ የበላይነት ይከበር ስትሉስ ምን ለማለት ነው?

አቶ አባይ ፀሐዬ ለውጥ ሲባል እናጨብጭብ ማለት አይደለም። ጥሩ ፈር ይዞ የሄደውን እናጨብጭብለት። ዳር እናድርሰው። በስመ ለውጥ ያልሆነ ነገር ተደባልቆ የሚደረግ ከሆነ፤ ተቀላቅሎ የሚፈፀም ሌላ ጤነኛ ያልሆነ ነገር ካለ ደግሞ “ይሄ እንከን አለው፤ ይሄ ለውጡን ያኮላሸዋል። ይሄ አይደለም የለውጡ መንፈስና ይዘት” ብሎ ማረም ለውጡን ከጉድለት የፀዳ እንዲሆን ማድረግና ይሄን በይፋ እንዲታረም መጠየቅ ለውጡን ያጎለብታል እንጂ ለውጡን የሚያደናቀፍ አይደለም።

ስለዚህ ላለፈውም ዋነኛው ተጠያቂ ህወሓት፤ የሕግ የበላይነት ሲባልም የትግራይ ተወላጆች ላይ የሚያነጣጥር ከሆነ የትም አያደርሰንም። የሕግ የበላይነት በሁሉም ክልል፣ በሁሉም ድርጅቶች፣ በሁሉም ፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ በእኩል ዓይን በሕግና በጠራ መረጃ ብቻ ፖለቲካዊ ዓላማ በሌለው፤ አድልዎ በሌለው መንገድ ይፈፀም ነው እያለ ያለው የትግራይ ሕዝብና መስተዳደር።

ይሄ ለውጡን መቃወም ነው? አይደለም። ህወሓት ላይና የትግራይ ተወላጆች ላይ አነጣጥሮ ሌላውን ነፃ አድርጎ ሸፍኖና ከልሎ ከሆነ ይሄ የሕግ የበላይነት አይደለም። ሕግ የማስፈን ጉዳይ አይደለም። ሕዝብ እንዲያኮርፍና እንዲያገል የሚያደርግ ካልሆነ የትም አያደርስም።

አንድን ሕዝብ ማግለልና ማስከፋት የጀመረ መንግሥት ሌላውንም ማስከፋቱና ማግለሉ አይቀርም። የጊዜ ጉዳይ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ እንዲከፋ እንዲተራመስ ማንም አይፈልግም። ያን ሁላ መስዋዕትነት የከፈለው የትግራይ ሕዝብ፤ ያን ሁላ ትግል ያካሄደው ህወሓት፤ ለኦሮሞ ሕዝብ ለአማራ ሕዝብ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት ነበር።

በምን ተዓምር ነው አሁን በየቦታው ለሚፈጠረው ችግር ወያኔ/ህወሓት ምክንያት ተደርጎ የሚነሳው? እንደዚህ ዓይነት አንድ ብሔር የሁሉም ችግር ምክንያት አድርጎ መመልከት አደገኛ ነው፤ ሃገርም ያፈርሳል።

ጣት የምንቀስርበት ብሔር ወይም ደግሞ የሕብረተሰብ ክፍል መኖር የለበትም። እንቀፈው፣ እናድምጠው፤ ምን አጎደልን ብለን እንጠይቀው። እንመካከርና እናርም። አለበለዝያ በየቦታው ግጭት፣ በየቦታው ጥርጣሬና ስጋት እየሰፋ የሚሄድበት ሁኔታ በጣም ያሰጋል።

ቢቢሲ፡ ትግሉን በመምራት፣ ፌደራላዊ ሥርዓቱን ተግባራዊ በማድረግና አጠቃላይ ሥረዓቱን (በኢህአዴግም ቢሆን) በበላይነት ይመራ የነበረው ህወሓት ነው። በተሰሠራው ስህተት ላይ ተጠያቂነቱ ከፍ ቢል የሚጠበቅ ነገር አይደለም ይላሉ?

አቶ አባይ ፀሐዬ ፈረንጆች ‘ዳብል ስታንዳርድ’ የሚሉት አለ። አንደኛ አረመኔው የደርግ መንግሥት ተወግዷል፣ ልማት መጥቷል፣ ሰላም መጥቷል፣ ሃገራችን አንገቷን ቀና አድርጋ በዓለም እውቅና አግኝታ አካባቢዋን አረጋግታ እራሷን ማልማትና ማረጋጋት ጀምራለች ይላል ብዙ ሰው። በዚህ መንግሥት ውስጥ ህወሓት ከሆነ የአንበሳው ድረሻ የነበረው መመስገን አለበት። ጉድለት ላይ ሲሆን ህወሓት ነው ዋናው ተጠያቂ፤ ስኬቱ ላይ ደግሞ ‘እኛ’ኮ ነን የሠራነው፤ አለንበት’ የሚል ይመጣል።

የህወሓት መዳከምና ወደ ብልሽት መግባቱ፤ እንደ ትጥቅ ትግሉ ጊዜ፣ እንደ ሽግግሩ ጊዜ ሕዝብ አመኔታ የሚያሳድርበት መሆኑ እየቀረና እያሽቆለቆለ መሄዱ ትግራይን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን በአጠቃላይ ደግሞ ሥርዓቱንም መጉዳቱን ገምግሞታል። የእኛ መዳከም ለሥርዓቱ መዳከም ትልቅ ድርሻ አለው ብሎ ነው የገመገመው።

ይሄ ማለት ግን ህወሓት አድራጊ ፈጣሪ ነበረ ማለት አይደለም። ስልጣንን ሰብስቦ የያዘው ህወሓት ነው ማለት አይደለም። በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውስጥ ሦስት አራት ሚኒስትሮች፣ ፓርላማ ውስጥ ስድስት ወይም ሰባት በመቶ ናቸው። እኚህ አካላት ናቸው ፖሊሲ የሚያፀድቁት ሕግም የሚያወጡት። እዚያ ላይ ደግሞ አብላጫ ድምፅ ያላቸው ብዙ ወንበር፣ ብዙ ሚኒስትር ያላቸው ትልቁ ድርሻ አላቸው። ፍትህ አካላት ላይም ደግሞ እንደዚሁ። ብዙም የትግራይ ሰዎች አልነበሩበትም።

በፖሊስና በሠራዊት አመራር ላይ አዎ ነበሩ። ደህንነትም ላይ እንደዚሁ። ባለፉት ሰባት ስምንት ዓመታት ግን በአበዛኛው የሌላ ብሔር ተወላጆች ናቸው ያሉት። ኤታማዦር ሹምና የደህንነት ኃላፊ የትግራይ ሰው ከሆነ በቃ! ሁሉም ነገር በዚያ ይመዘናል።

ስለዚህ ሃገሪቱ ለገባችበት ችግር፣ ኢህአዴግ ላጋጠመው ቀውስ፣ የህወሓት አስተዋፀዖ ትልቅ ነበረ፤ ትክክል። ነገር ግን ለሁሉም ነገር ህወሓት ተጠያቂ መሆን ነበረበት የሚል ትክክል አይደለም። ምክንያቱም ህወሓት አናሳ ነው ድምፁ። የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲወስኑ አንድ አራተኛው ነው ድምፁ። ፓርላማም ውስጥ ከአስር በታች ነው ድምፁ። የሚኒስትሮች ምክር-ቤት ውስጥም እንደዚሁ።

ስለዚህ ዋናው ተጠያቂ ኢህአዴግ የእራሱ ሥራ አስፈፃሚ ነው ብሎ ነው የገመገመው። ህወሓት ነው ብሎ አልገመገመም። ምክንያቱም ፌዴራል መንግሥቱን ሲመራ የነበረው፤ ሠራዊቱንም ደህንነቱንም ሲመራ የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚያ ቀጥሎ መከላከያ ሚኒስትሩና ኤታማዦር ሹሙ ናቸው። ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው ከህወሓት ከሆነ፡ እሱ በነበረበት ጊዜ ተጠያቂ ይሆናል። ሌላው በነበረበት ጊዜ ድግሞ ሌላው ይጠየቃል።

ቀደም ብለን ማድረግ ይገቡን የነበሩብን አሁን የተደረጉ ለውጦች አሉ፤ የሚል ከሆነ እቀበላለሁ። ለምሳሌ እስረኞችን መፍታት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጥ እስኪደረግ ድረስ ለምን አላደረግነውም? እዚህ ላይ ሁላችንም ድርሻ አለን እቀበላለሁ። ህወሓት ብቻ ለሁሉም ነገር ተጠያቂ ነው የሚል፣ መነሻው የህወሓትና የትግራይ የበላይነት ነበረ ከሚል ነው የሚነሳው። ነገር ግን ከመረጃና ከሃቅ አይደለም የሚነሳው።

እንደርሱ ቢሆን ለምን የትግራይ ሕዝብ የተለየ ነገር አላገኘም? አንድ ሚሊዮን ሕዝብ በየዓመቱ በረሃብ የሚጠቃ ነው። ህወሓት እራሱን በማያዳግምና ያለምህረት ሂስ አድርጓል። ለማስተካከል ልባዊ ጥረት አድርጓል። አሁንም ለውጡን ደግፎ በሙሉ ልብ እየሄደ ነው። አንዳንድ ጉድለቶችና ዝንፈቶች ደግሞ እንዲስተካከሉ በይፋ በኢህአዴግ መድረክ ላይ እያረመ ነው እየሄደ ያለው።

ከዚያ በተረፈ ስለግለሰቦች ከሆነ የሚነገረው ስለሌሎች ግለሰቦችም ይነሳ። እያንዳንዱ ክልሉን ሲያስተዳደር የነበረ ይጠየቅ። ክልሉን ካላለማ፣ ካተራመሰ ህወሓት ነው የሚጠየቅለት? ለምን? ህወሓት ሲያስተዳድረው የነበረው ክልል አለ ከትግራይ ውጭ?

ስለዚህ ‘የጎደለ ነገር ካለ በዋናነት የሚጠየቀው እዚያ ያለው ፓርቲ ነው’ ብለን ነው በኢህአዴግ ውስጥ የገመገምነው። ለምንድነው ወደ ህወሓት ጣት የሚቀሰረው? አንቀበልም፤ ድርጅቱም እንደዚያ ብሎ አልገመገመም።

በፌደራል ደረጃ ላለው ችግር ደግሞ የምንጠየቀው በጋራ ነው። ለዚያውም ዋናው ተጠያቂ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ነው። ከዚያ በመቀጠል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ብለን ነው የገመገምነው።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

95 Comments

  1. [url=https://viagragm.com/]viagra for men for sale[/url] [url=https://hydroxychloroquine360.com/]generic plaquenil price[/url] [url=https://hloroquine.com/]chloroquine tablets buy[/url] [url=https://seroqueltb.com/]seroquel 300 mg for sleep[/url] [url=https://buyviagaonline.com/]pharmacy rx viagra[/url] [url=https://proscar365.com/]proscar 5mg price[/url] [url=https://celexamed.com/]citalopram for ibs[/url]

  2. [url=https://stromectoliv.com/]how much does ivermectin cost[/url] [url=https://hydroxychloroquinerem.com/]where to buy plaquenil[/url] [url=https://viagrazbs.com/]sildenafil 100mg tablets[/url] [url=https://trentalgen.com/]trental 400 online india[/url] [url=https://bupropionb.com/]bupropion generic price[/url]

Comments are closed.