በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ሰዎች ያለሀኪም ትዕዛዝ የጸረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን ይወስዳሉ – የዓለም ጤና ድርጅት

ዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ሰዎች ያለሀኪም ትዕዛዝ የጸረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን እንደሚወስዱ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

በጥናቱ መሰረት በሀኪም ያልታዘዙ ጸረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን ማዝወተር መድሃኒቶችን የተላመዱ ቫክቴሪያዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል ተብሏል።

መድሃኒቶቹ በሚወሰዱበት ጊዜም ‘‘ከፔኒሲሊዬም’’ ጀምሮ ደረጃ በደረጃ መወሰድ ያለበት መሆኑን በሳለፍነው ዓመት የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ መደረጉንም ዘገባው አስታውሷል።

ይሁን እንጂ አንዳንድ ሀገራት በቀጥታ ከከፍተኛ ምድሀኒቶች የሚጀምሩ መሆኑም ተጠቁሟል።

መድሀኒቶችን ያለሀኪም ትዕዛዝ አወሳሰዱ ተግባር ከቦታ ቦታ የሚለያይ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

በዓለም የጤና ድርጅት በ65 ሀገራት ላይ በተደረገ ክትትል ይፋ የተደረገው ሪፓርት መሰረት በኒዘርላንድ 9ነጥብ 78 በመቶ፣ ብሪታኒያ 38ነጥብ 18 ያህል ሰዎች ያለሀኪም ትዛዝ የጸረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን ተጠቃሚ መሆናቸው ለአብነት ተጠቅሰዋል።

ሞንጎሊያዎች ከላይ የተጠቀሱትን መድሃኒቶችን 64ነጥብ41 በመቶ በመጠቀም በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ ደረጃን ይዘዋል ተብሏል።

ጉዳዩ አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያስፈልገው የተገለጸ ሲሆን፥ በመድሃኒቶቹ አጠቃቀም ዙሪያ ጥብቅ ክትትል ማድረግ የሚጠይቅ መሆኑንም ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

በሪፖርቱ ቡርንዲ በዝቅተኛ ደረጃ 4ነጥብ 44 በመቶ የመድሃኒቶች ተጠቃሚ መሆኗ የተገለጸ ሲሆን፥ የመድሃኒቶቹ አጠቃቀም ዝቅተኛ መሆን ደግሞ በቀላሉ ለመዳን የሚችሉ በሽታዎች እንዲባባሱ ያደርጋል ተብሏል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.