SORT NEWS: ክለባቸውን ሊለቁ የሚችሉ ዘጠኝ የፕሪምየር ሊጉ ተጫዋቾች

የዘንድሮው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት የፊታችን ሃሙስ በይፋ ይዘጋል። ብዙ የእንግሊዝ ክለቦች የመጨረሻው ቀን ከመድረሱ በፊት ይጠቅሙኛል ያሏቸውን ተጨዋቾችን ለማስፈረም እየተሯሯጡ ነው።

ቶተንሃም በመጨረሻም ተጫዋች ያስፈርም ይሆን? የማንቸስተሩ አንቶኒ ማርሻል ወደ ሌላ ክለብ ይዘዋወር ይሆን?

በዚህኛው የዝውውር መስኮት ክለቦቻቸውን ሊለቁ የሚችሉ ዘጠኝ የፕሪምየር ሊጉ ተጫዋቾችን እንመልከት።

ቶቢ አልደርዌረልድ (ቶተንሃም)

ቶቢ አልደርዌረልድImage copyrightGETTY IMAGES
ቦታ: ተከላካይ እድሜ: 29
2017-18 ፕሪምር ሊግ: 15 ጨዋታ አድርጓል ሊሄድ የሚችለው: ማንቸስተር ይናይትድ

ቤልጂየማዊው ተከላካይ ባለፈው ዓመት ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በቶተንሃም የቋሚ አሰላለፍ ቦታ ለማግኘት ተቸግሮ ነበር። ኮንትራቱ በዚህ ዓመት የሚጠናቀቀው አልደርዌረልድ፤ ስሙ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር እየተያያዘ ነው። ለተጫዋቹ የቀረበው የመግዣ ዋጋ ደግሞ 75 ሚሊዮን ፓውንድ ነው።

• ጅማ አባጅፋር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆነ

• ኢትዮጵያዊው ጀማል ይመር በአስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ

• አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ

ጃክ ግሬሊሽ (አስቶን ቪላ)

ጃክ ግሬሊሽImage copyrightGETTY IMAGES
ቦታ: አማካይ እድሜ: 22
2017-18 ቻምፒየንሺፕ: 30 ጨዋታ, 3 ግቦች ስሙ የተያያዘው: ቶተንሃም, ቼልሲ

የ21 ዓመቱ እንግሊዛዊ ግሬሊሽ በቻምፒዮንሺፑ አስቶን ቪላ ላደረገው ግስጋሴ ከፍተኛ አስተዋጸኦ አድርጓል። ክለቡ በአሁኑ ሰአት የገንዘብ እጥረት ያጋጠመው ሲሆን፤ በተለይ ደግሞ ቶተንሃሞች ተጫዋቹን የግላቸው ለማድረግ እስከ 20 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ተዘጋጅተዋል። አስቶን ቪላ ግን ቶተንሃሞች ያቀረቡትን ዋጋ እጥፍ እየጠየቁ ነው።

ዳኒ ኢንግስ (ሊቨርፑል)

ዳኒ ኢንግስImage copyrightGETTY IMAGES
ቦታ: አጥቂ እድሜ: 26
2017-18 ፕሪምየር ሊግ: 8 ተጫውቶ, 1 ግብ ስሙ የተያያዘው: ክሪስታል ፓላስ, ሳውዝሃምፕተን, ሌስተር, ኒውካስል

በአንድ ወቅት እንግሊዝ ካፈራቻቸው ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ ተብሎ ሲወደስ ነበረው ዳኒ ኢንግስ ሊቨርፑል ባሳለፋቸው ሶስት ዓመታት እጅግ አስቸጋሪ ጊዜ አሳልፏል። በባለፈው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግም አንድ ጊዜ ብቻ ነው ግብ ማስቆጠር የቻለው።

ሊቨርፑሎችም ለተጫዋቹ የ20 ሚሊዮን ፓውንድ መሸጫ ዋጋ ለጥፈውበታል። ተጫዋቹን በጥብቅ ከሚፈልጉት ክለቦች መካከል ደግሞ ክሪስታል ፓላስ የመጀመሪያውን ስፍራ ይዟል።

ሃሪ መጓየር (ሌስተር ሲቲ)

ሃሪ መጓየርImage copyrightGETTY IMAGES
ቦታ: ተከላካይ እድሜ: 25
2017-18 ፕሪምር ሊግ: 38 ተጫውቶ, 2 ግቦች ስሙ የተያየዘው: ማንቸስተር ይናይትድ

በተለይ በአለም ዋንጫው ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ያሳየው ወጥና አስገራሚ አቋም በአሁኑ ሰአት ይህን ተከላካይ ተፈላጊ እንዲሆን አድርጎታል።

የሃሪ መጓየር ዋነኛ ፈላጊ ደግሞ የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሆሴ ሞሪንሆ ናቸው። ለተጫዋቹም እስከ 56 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የተጫዋቹ ባለቤት ሌስተር ሲቲ ደግሞ ለተከላካዮች ሪከርድ የሆነ 80 ሚሊዮን ፓውንድ ጠይቀዋል።

አንቶኒ ማርሻል (ማንቸስተር ዩናይትድ)

አንቶኒ ማርሻልImage copyrightGETTY IMAGES
ቦታ: ክንፍ እድሜ: 22
2017-18 ፕሪምየር ሊግ: 30 ተጫውቶ, 9 ግቦች ስሙ የተያያዘው: ቶተንሃም, ቼልሲ, ፒ ኤስ ጂ

ከአሌክሲስ ሳንቼዝ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ መምጣት በኋላ አንቶኒ ማርሻል የቋሚ አሰላፍ ቦታ ለማግነት ተቸግሮ የቆየ ሲሆን፤ ለአለም ዋንጫው በብሄራዊ ቡድኑ አለመካተቱ ደግሞ ክለቡን እንዲለቅ ምክንያት ሊሆነው እንደሚችል ተገልጿል።

በሌላ በኩል ተጫዋቹ ሁለተኛ ልጅ ሲወለድለት የቅድመ ውድድር ጨዋታውን ጥሎ ወደ ፈረንሳይ መመለሱ የማንቸስተሩ አሰልጣን ሆዜ ሞሪንሆን ያስደሰታቸው አይመስልም። መሸጫ ዋጋውም እስከ 80 ሚሊዮን ፓውንድ ይደርሳል ተብሏል።

ሲሞን ሚኞሌ (ሊቨርፑል)

ሲሞን ሚኞሌImage copyrightGETTY IMAGES
ቦታ: ግብ ጠባቂ እድሜ: 30
2017-18 ፕሪምየር ሊግ : 10 ጨዋታ ስሙ የተያያዘው: ባርሴሎና, ቤሺክታሽ

ቤልጂየማዊው ግብ ጠባቂ በሊቨርፑል ቤት የቋሚ አሰላለፍ ቦታውን በካሪየስ ተነጥቆ ነው የቆየው። አሁን ደግሞ ብራዚላዊውን ግብ ጠባቂ አሊሰን ከሮማ ማስፈረማቸው ደግሞ የተጠባባቂውን ቦታ እንኳን እንዳያገኝ ሊያደርገው ይችላል።

በአስገራሚ ሁኔታ የላሊጋው አሸናፊ ባርሴሎናዎች በግብ ጠባቂው ላይ ፍላጎት አሳይተዋል።

አሮን ራምሴ (አርሰናል)

አሮን ራምሴImage copyrightGETTY IMAGES
ቦታ: አማካይ እድሜ: 27
2017-18 ፕሪምየር ሊግ: 24 ተጫውቶ, 7 ግቦች ስሙ የተያያዘው: ቼልሲ, ሊቨርፑል

ዌልሳዊው አማካይ ራምሴ በአርሰናል ቤት 10 ዓመት የቆየ ሲሆን፤ 300 ጨዋታዎችን ደግሞ ለክለቡ አድርጓል። አዲሱ የአርሰናል አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ ራምሴን ጠቃሚ ተጫዋች ነው ብለው ቢገልጹትም፤ ከቼልሲ የቀረበላቸው የ35 ሚሊዮን ፓውንድ መገዣ ዋጋ እና የሊቨርፑል ፍላጎት ሃሳባቸውን ሊያስቀይራቸው እንደሚችል ይገመታል።

ዊሊያን (ቼልሲ)

ዊሊያንImage copyrightGETTY IMAGES
ቦታ: ክንፍ እድሜ: 29
2017-18 ፕሪምየር ሊግ: 36 ተጫውቶ, 6 ግቦች ስሙ የተያያዘው: ባርሴሎና, ሪያል ማድሪድ, ማንቸስተር ዩናይትድ

ይህ የማይደክመው የሚባልለት የክንፍ ተጫዋች በአለም ዋንጫው ለሃገሩ ብራዚል በአምስቱም ጨዋታዎች በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ መግባት ችሏል። ባለፈው ዓመት ቼልሲ በኤፍ ኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ከማንቸስተር ይናይትድ ጋር ሲጫወቱ በቀድሞው አሰላጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ተጠባባቂ ቦታ ላይ መቀመጡ ደግሞ ልቡን እንዳስሸፈተው ይገመታል።

የተጫዋቹ ዋነኛ ፈላጊ ሆነው እየተፎካከሩ ያሉት ደግሞ ሪያል ማድሪድ፤ ባርሴሎና እና ማንቸስተር ዩናይትድ ሲሆኑ፤ 65 ሚሊዮን እንዲፍሉ ተጠይቀዋል።

ዊልፍሬድ ዛሃ (ክሪስታል ፓላስ)

ዊልፍሬድ ዛሃImage copyrightGETTY IMAGES
ቦታ: ክንፍ እድሜ: 25
2017-18 ፕሪምየር ሊግ: 29 ተጫውቶ, 9 ግቦች ስሙ የተያያዘው: ቦርሺያ ዶርትመንድ, ቼልሲ, ቶተንሃም

ምንም እንኳን የባለፈው ዓመት የውድድር ዘመን የመጀመሪያዎቹን ስድስት ጨዋታዎች ለቡድኑ መሰለፍ ባይችልም፤ ከዚያ በኋላ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ግን ዘጠኝ ግቦችን አስቆጥሮ ሶስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አቀብሏል።

አሰልጣኝ ሮይ ሆድሰን ኮትዲቯራዊውን ተጫዋች በቡድናቸው ለማስቀረት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፤ ከተለያዩ ክለቦች እየቀረበላቸው ያለው ከፍተኛ ገንዘብ ሃሳባቸውን ሊያስቀይራቸው እንደሚችል ይገመታል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.