የአንጎል አወቃቀር እንደ ጣት አሻራ የተለያየ ነው

የአንጎል አወቃቀር እንደ ጣት አሻራ የተለያየ መሆኑን ተመራማሪዎች ገለጹ።

በራሂና ሌሎች ጉዳዮች የአንጎልን ተግባር ብቻ ሳይሆን የአንጎል መዋቅር ላይ ተጽህኖ ያላቸው መሆኑንን በጥናቱ ተገልጿል።

በሲውዘር ላንድ የዙሪክ ዩንቨርስቲ የነርብ ፕሮፌሰር የሆኑት ሉትዝ ጃንኬ እንደተናገሩት በጥናቱ የሰው ልጆች አንጎል እንደ ጣት አሻራ የተለያየ መሆኑ ተረጋግጧል።

የተለያዩ ልምዶች በአንጎል አወቃቀር ላይ የራሳቸው አሻራ እንደሚኖራቸው ነው በጥናቱ የተመላከተው።

ታዋቂ የሙዚቃ ሰዎች፣ ጎልፍና ቼዝ ተጫዋቾች የተለየው የዘወትር ልምዳቸው በአንጎላቸው መዋቅራቸው ላይ የራሱ አሻራ እንዳለው ነው ተመራማሪዎች ያመላከቱት።

በእድሜያቸው ከገፉ 200 ፈቃደኛ ተጠኚዎችን በ2ዓመት ለ3 ጊዜ ስካን በማድረግ በተወሰደ የእንጎል መረጃ ጥናቱ መካሄዱም ነው የተገለጸው።

በዚህም ከ450 በላይ የአንጎል መዋቅር፣ ይዘትና የአንጎል ቡናማ እንዲሁም ነጭ ክፍል ይዘት ልዩነት መመዝገባቸው ነው የተገለጸው።

የተለያዩ ሁለት አንጎሎች በበራሂ የተለያዩ ሲሆኑ፥ የተለያዩ ልምዶች በአንጎል አወቃቀር ላይ የራሳቸው አሻራ እንደሚኖራቸውም ነው የተገለጸው።

ከዛሬ 30 ዓመት በፊት የሰው ልጅ የአንጎል አወቃቀር እንደ ጣት አሻራ ልዩነት የኖረዋል ተብሎ የማይታሰብ የነበረ መሆኑን ነው ፕሮፌሰር ጃንኬ የተናገሩት።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.