ማይክሮሶፍት ኦፊስ 2019 በዊንዶውስ 10 ላይ ብቻ እንደሚሰራ ተገለፀ – Microsoft Office 2019 Will Only Work on Windows 10

                                                   

አዲሱ የማይክሮሶፍት መገለግለያ የሆነው “ማይክሮሶፍት ኦፊስ 2019” ሶፍትዌር በዊንዶውስ 10 ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ብቻ የሚሰራ መሆኑ ተነገረ።

እንደ ማይክሮሶፍት ኩባንያ ገለጻ፥ በዴስክ ቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ለላይ ለፅሁፍ እና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚያገለግለው “ማይክሮሶፍት ኦፊስ 2019” በያዝነው

የፈረንጆቹ 2018 አጋማሽ ላይ ተጠቃሚዎች ዘንድ መድረስ ይጀምራል።

ሆኖም ግን “ማይክሮሶፍት ኦፊስ 2019” ዊንዶውስ 10 ኦፕሬቲንግ ሲስተም በሚጠቀሙ ኮምፒውተሮች ላይ ብቻ እንደሚሰራ ነው የማይክሮሶፍት ኩባንያ ያስታወቀው።

አዲሱ ማይክሮሶፍት ኦፊስ 2019 ወርድ፣ ኤክሴል፣ ፓወር ፖይንት፣ የቢዝነስ ስካይፒ እና ሼር ፖይንት የተባሉ አገልግሎቶችን ያካተተ ነው።

“ማይክሮሶፍት ኦፊስ 2019” ለ5 ዓመታት ዋና ዋና የሚባሉ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን፥ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ደግሞ የማራዘሚያ ድጋፎች እንደሚደረጉበትን ኩባንያው ገልጿል።

በአሁኑ ጊዜ ለማይክሮሶፍት ኦፊስ 2016 የተሰጠው የማራዘሚያ የድጋፍ ጊዜ በአውሮፓውያኑ 2025 ላይ እንደሚጠናቀቅም ተነግሯል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement