SPORT NEWS: ኢትዮጵያ በ2020 የቻን ውድድርን ለማስተናገድ አርማ ተረከበች – Ethiopia Has Been Awarded a Logo For Hosting Chan’s Games in 2020

                                                 

ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 2020 የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበትን የአፍሪካ እግር ኳስ ሻምፒዮና/ቻን ውድድርን ለማስተናገድ ትናንት በይፋ የውድድሩን አርማ ተረክባለች።

ሞሮኮ ያስተናገደችው የቻን አፍሪካ 2018 ውድድር ትናንት በአስተናጋጇ ሀገር አሸናፊነት ተጠናቋል።

በፍፃሜው ሞሮኮ እና ናይጄሪያ ተገናኝተው፥ ሞሮኮ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮና ሆናለች።

                                                 

ሞሮኮ የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮናን እራሷ አስተናግዳ ያሸነፈች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡

በውድድሩ ናይጄሪያ 2ኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ፤ ቅዳሜ ሱዳን ከሊብያ ባደረጉት የደረጃ ጨዋታ፤ሱዳን በመለያ ምት በማሸነፍ የሶስተኝነት ደረጃን በማግኘት ውድድሩን አጠናቃለች።

ሞሮኮ ያስተናገደችው የቻን አፍሪካ 2018 ውድድር ትናንት ሲጠናቀቅም ኢትዮጵያ ቀጣዩን ውድድር ለማስተናገድ አርማ ተረክባለች።

በስነ ሰርዓቱ ላይም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ አርማውን ተረክበዋል።

በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 የሚካሄደውን የቻን የፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን የምታስተናግድ ይሆናል።

የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) በሀገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚካፈሉበት ውድድር ሲሆን፤ለአፍሪካ እግር ኳስ እድገት ሲባል በየሁለት አመቱ የሚካሄድ ነው፡፡

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement