በሴኮንዶች ውስጥ ሀይል የሚሞላና ለሳምንት የሚያገለግል ባትሪ እየተሰራ ነው

                                       

ባለፉት አስርት ዓመታት ስማርት ስልኮች አሳማኝ በሆነ መልኩ ለውጥ እየታየባቸው እና ምቹ እየሆኑ መጥተዋል።

የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች በስክሪን ስፋት እና ጥራት፣ በፕሮሰሲንግ አቅም እንዲሁም በካሜራ ጥራት አዳዲስ ለውጦችን ያገኙ ሲሆን፥ የባትሪው ነገር ግን አሁንም የራስ ምታት እንደሆነ ቀጥሏል።

አሁን ላይ ግን የአሜሪካ የተመራማሪዎች ቡድን የናኖ ቴክኖሎጂ ለዚህ ችግር አይነተኛ መፍትሄ ይሆናል የሚል ሀሳባቸውን አቅርበዋል። 

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፥ የናኖ ቴክኖሎጂ በሴኮንዶች ውስጥ ሀይል ለመሙላት እና የተሞላው ሀልይ ለሳምንት እንዲቆይ የሚያስችል አቅም አለው።

እንዲሁም በናኖ ቴክኖሎጂ የሚሰሩ ባትሪዎች እስከ 30 ሺህ ጊዜ በድግግሞሽ ሀይል ለመሙላት ያስችላሉ ተብሏል።

በአሁኑ ጊዜ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት የሊቲየም አየን ባትሪዎች እስከ 1 ሺህ 500 ጊዜ ነው በድግግሞሽ ሀይል መደረግ የሚችሉት ተብሏል።

በናኖ ቴክኖሎጂ የሚሰራው ባትሪው በውስጡ በሚሊየን የሚቆጠሩ የናኖሜትር ቀጭን ሽቦዎች የተሞላ ሲሆን፥ በሁለት አቅጣጫዎች የተሸነፈ ነው።

ይህም በአንደኛው በኩል ሀይል ለመሙላት እና ለማስቆም የሚረዳ ሲሆን፥ በሌላኛው በኩል ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ሀይልም ለማከማቸት የሚያስችል ነው።

ባትሪዎቹን አገልግሎት ላይ ለማዋል ጊዜው ገና ነው የተባለ ሲሆን፥ በቅርቡ ግን የናኖ ቴክኖሎጂ ባትሪው አሁን በጥቅም ላይ የሚገኙትን የኤሌክትሮኒክስ ቁስ እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎችን ይተካል ተብሏል።

ምንጭ :- FBC(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Advertisement