የሀሞት ከረጢት ብግነት ምንድን ነዉ?

የሀሞት ከረጢት መጠኑ ትንሽ የሆነ በቀኝ በኩል ከጉበት በታች የሚገኝ የአካል ክፍል ሲሆን ለምግብ እንሽርሽሪት የሚያግዘዉን ሀሞት ይዞ በመቆየት ወደ ቀጭን አንጀት ይለቃል፡፡የሀሞት ከረጢት በተለያየ ምክንያቶች ሲጎዳ ጤናማ የሆነ ስራዉን መስራት ሳይችል ሲቀር የሀሞት ከረጢት ብግነት ተከሰተ እንላለን፡፡

የሀሞት ከረጢት ብግነት ሊያስከትሉ የሚችሉ መንስኤዎች

  • የሀሞት ጠጠር
  • የሀሞት ከረጢት እጢ
  • በቫይረስ የሚመጡ ህመሞች እንደ ኤች አይቪ
  • የደም ስር ችግር
  • ሆድ አካባቢ አደጋ ወይም ቀዶ ህክምና ከነበረ
  • ለረጅም ጊዜ ምግብ ሳይበሉ መቆየት

ለሀሞት ከረጢት ብግነት አጋላጭ ሁኔታዎች

  • እድሜ ከ50 አመት በላይ መሆን
  • ከልክ በላይ የሆነ የሰዉነት ክብደት
  • የስኳር በሽታ
  • እርግዝና መኖር
  • የልብ ችግር
  • መጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሰ የኩላሊት ህመም
  • በደም ዉስጥ የስብ እና የፕሮቲን መጠን መጨመር
  • ቅባት ያላቸዉ ምግቦችን አዘዉትሮ መመገብ

የሀሞት ከረጢት ብግነት ሲኖር የሚስተዋሉ ምልክቶች

  • በቀኝ የላይኛዉ ክፍል ላይ ህመም በተለይ ቅባት ያላቸዉ ምግቦች ሲመገቡ
  • ከሆድ ወደ ቀኝ ትክሻ እና ጀርባ የሚሔድ ህመም
  • ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
  • ከፍተኛ ትኩሳት እና ላብ
  • የምግብ ፍላጎት መቀነስ
  • የሆድ መነፋት
  • የአይን እና የቆዳ ቢጫ መሆን
  • ጠቆር/ደማቅ ቢጫ ቀለም ያለዉ ሽንት
  • ግራጫ ቀለም ያለዉ ሰገራ

በቀኝ የላይኛዉ ክፍል ላይ ህመም በተለይ ቅባት ያላቸዉ ምግቦች ሲመገቡ፤ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣የአይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን እንዲሁም ሽንት እና ሰገራ ላይ የቀለም መለወጥ ካስተዋሉ በፍጥነት ከባለሙያ ጋር መመካከር ይችላሉ፡፡የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ከሰኞ እስከ ሰኞ ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ሊያማክሩዎት በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!

ምንጭ: ዶክተር አለ

Advertisement