ሎሚን ለብ ባለ ውሃ መጠጣት የሚያስገኛቸው የጤና ጥቅሞች

ሎሚ ለብ ባለ ውሃ ውስጥ ጨምሮ መጠቀም በርካታ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ይነገራል።

በተለይም በባዶ ሆድ ለብ ያለ ውሃ ውስጥ ሎሚ ጨምቆ ዘወትር መጠጣት ÷ ጉበትን ከመርዛማ ነገሮች ያፀዳል፣ በውሃው ውስጥ የሎሚውን ልጣጭ በመጨመር የሚጠጡ ከሆነ ደግሞ የደረጃ 2 የጉበት ፀር የሆነውን መርዝ ማስወገድ ያስችላል።

ከዚህ ባለፈም ጉበት ሐሞት እንዲያመነጭ በማበረታታት ቅባት የበዛባቸውን ምግቦችን ሰውነት እንዲፈጭ ይረዳል፣ ሎሚ ከፍተኛ አንቲ ኦክሲደንት ባህሪ ስላለው ሕዋሳት እንዳይጎዱ ይጠብቃቸዋል፣ በሎሚ ውስጥ ያለው አንቲ- ኦክሲደንት እና ፌቶኬሚካልስ የጉበት ሕዋሳት እንዲታደሱ ይረዳል።

በተጨማሪም በሎሚ ውስጥ ያለው ሲትሪክ አሲድ የምግብ ስርዓተ ልመትን ያፋጥናል እንዲሁም የኩላሊት ጠጠርን ያሟሟል።

ሎሚ ከሰውነት ውጭ አሲድ ሲሆን በሰውነት ውስጥ አልካላይን በመሆኑ በሰውነት ውስጥ ያለውን የፒ ኤች ደረጃ ሚዛናዊ እንዲሆን ይረዳል፣ በሽታን ይከላከላል፣ በሎሚ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ጠንካራ የተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅም እንዲኖር ያስችላል።

ሎሚ የደም ቅባትን በመሰባበር በርካታ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን የሀሞት ድንጋይ በሰውነት ውስጥ እንዳይፈጥር ያግዛል፣ የዩሪክ አሲድ መጠንን በመቀነስ ሰዎች በሪህ እና በአጥንት አንጓ ብግነት እንዳይጠቁ ያግዛል።

እንዲሁም ራስን ከአንዳንድ የካንስር በሽታ አይነቶች ለመከላከል እንደሚረዳ የሃኪም ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ምንጭ: ፋና

Advertisement