በባዶ ሆድ የሚጠጣ የማር ብጥብጥ እና የጤና ትሩፋቶቹ

ሰዎች በጤና በመሰንበት ረዘም ያለ ጊዜ ለመኖር እና ያሰቡትን ለማሳካት ከተመረጠ አመጋገብ ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶችን ያደርጋሉ።

አለፍ ሲልም ወደ ሃኪም ቤት በማቅናትና ባለሙያዎችን በማማከር የተሰጡ መመሪያዎችን በመተግበር በጤና በመቆየት ያሰቡትን ለማሳካት ሲጥሩ ይስተዋላል።

በእነዚህ ሂደቶች ውስጥ ግን ሁል ጊዜም ቢሆን ባለሙያዎች ያሉትን ከመተግበር ባለፈ በቀላሉና በቤት ውስጥ በሚገኙ ውህዶች ታሞ አልጋ ላይ ከመዋል መዳን የሚቻልባቸው በርካታ አማራጮች አሉ።

ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ለዛሬ፥ በብዛት በልጅነት በቁርስ ሰአት የሚመገቡት የታታሪዋ ንብ ውጤት የሆነውን ንጹህ ማር በውሃ በጥብጦ በባዶ ሆድ መጠጣት ያለውን ጠቀሜታ እንመልከት።

ማር ከጣፋጭነቱ ባለፈ ለበርካታ የጤና ጠንቆች መፍትሄ እንደሆነም ይነገርለታል፤ ነገር ግን ማርን በውሃ በጥብጦ እና አዋህዶ መጠጣት ያለውን አስገራሚ የጤና ጠቀሜታ ብዙ አልተነገረለትም።

እናም በአንድ ብርጭቆ ውሃ የተበጠበጠ ንጹህ ማር በመጠጣትዎ የሚያገኘኟቸው የጤና ጠቀሜታዎች ዘርፈ ብዙ ናቸውና ልብ ብለው ያንበቧቸው፥

እንዴት ይዘጋጃል

አንድ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሃ እና
አንድ የሾርባ ማንኪያ ንጹህ ማር ማዘጋጀት።
በመቀጠልም ማሩን ውሃው ውስጥ በመጨመር ሁለቱ ተዋህደው የሚያስገኙት የቀለም አይነት እስኪመጣ ድረስ በደንብ ማማሰል እና በአግባቡ መቀላቀል፤ በጣም ያልቀላ የቀለም አይነት እስኪያመጣ ድረስ።
ከዛም ያዘጋጁትን የማር እና የውሃ ቅልቅል ምንም አይነት ምግብ ሳይቀምሱ በባዶ ሆድ ከቁርስ በፊት መጠጣት፥ ከቻሉም ይህን ውህድ ማታ ላይ ከእራት በፊት ቢደግሙት እና ቢጠጡት መልካም ነው።

ይህን ውህድ በመጠጣትዎ ምን ይጠቀማሉ?

ሳንባ ላይ የሚከማችን አክታ ያስወግዳል፤
የጉሮሮ ቁስለትንና አደገኛ ጉንፋንን በመከላከል እና በማስወገድ የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ያዳብራል፤

የሆድ እቃ እና የውስጥ ቁስለትን በማስወገድ ለበሽታ የሚያጋልጡ ጥገኛ ህዋሳት እንዳይራቡ ያደርጋል፤

የሆድ ድርቀትን በመከላከልና በማለስለስ ለተስተካከለ የሰውነት ሽግግር ይረዳል። ከዚህ ባለፈም መፀዳጃ አካባቢ የሚፈጠር ድርቀትንም መከላከል ያስችላል፤

አጠቃላይ ሰውነትንና አንጀትን ንጹህ እና ፅዱ በማድረግ መርዘኛ ነገሮችን ከሰውነት ለማስወገድ ይረዳል፤

ፈንገስን እና ባክቴሪያን በመከላከል ቫይረስ በሰውነት ውስጥ እንዳይከሰትና እንዳይከማች ያደርጋል፤

የሚከሰትን የሽንት አለመቆጣጠር ስርአትን ማስተካከልም የዚሁ ውህድ ሌላው ጠቀሜታ ነው።

ማር የኩላሊትን የማጣራት ተግባር በእጅጉ በማገዝ እና ስራውን ቀልጣፋ በማድረግ የሚፈጠረውን የጤና ጠንቅ የማስወገድ አቅም አለው።

በዚህ ተግባሩም ኩላሊት መደበኛ እና የተስተካከለ ስራውን እንዲሰራ በማድረግ ጤናማ እንቅስቃሴን ይፈቅድልዎታል።

ከዚህ ባለፈ ደግሞ ይህን የማር ብጥብጥ በመጠጣት እጅግ ማራኪና ፅዱ የቆዳ ገጽታንም ያላብስዎታል።

ይህ ዘመናትን ያስቆጠረው የቤት ውስጥ ወጌሻ ታዲያ ለስላሳ፣ ጤናማ እና ማራኪ የፊት ገጽታንም ያላብሳልና እስኪ ይሞክሩት።

ጠዋት በባዶ ሆድዎት ይህን ውህድ ፉት ብለው የሚከሰቱ የጤና እክሎችን ከመሰረታቸው በማድረቅ ማራኪና ውብ ገጽታን መላበስ ይችላሉና ይጠቀሙበት።

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.