በረመዳን ፆም ቴምር ለምን ይዘወተራል?

የረመዳን ወር በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ወር ነው። የረመዳን ፆም ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ይፀናል። አማኞቹ ከወትሮው በተለየ ኃይማኖታዊ ሥርዓት በፆምና በዱዓ ፈጣሪያቸውን እየተማፀኑ የሚያሳልፉበትም ቅዱስ ወር ነው። የዘንድሮው 1440ኛው የረመዳን ፆምም ሰኞ ዕለት ተጀምሯል።

ታዲያ በረመዳን ወቅት በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ብቻ ሳይሆን የእምነቱ ተከታይ ወዳጅ ዘመድ ባላቸው የሌላ እምነት ተከታዮች የሚዘወተሩ ምግቦች አሉ።

ሾርባ፣ ሳምቡሳ፣ ጣፋጭ ብስኩቶችና ቴምር የረመዳን ምግባዊ ትዕምርቶች ናቸው ማለት ይቻላል።

በአንድ ጉዳይ ምክንያት ለማፍጠር ቤቱ መድረስ ያልቻለ፤ መንገድ ላይ ቴምር ገዝቶ ፆምን መግደፍ በዚህ ወቅት እንግዳ ነገር አይደለም። በዚህ የረመዳን ወር ማስቲካና ብስኩት ሲሸጡ የነበሩ የጎዳና ላይ ነጋዴዎችም ወሳኝ ቦታዎችን እየመረጡ ቴምርን መሸጣቸው የተለመደ ነው።

ለመሆኑ ቴምር በረመዳን ወር ለምን ይዘወተራል?

ቴምር ኃይማኖታዊም ሆነ የጤና ፋይዳ አለው የሚሉት ኡስታዝ ሀሰን ታጁ ናቸው “በእስልምና ኃይማኖት ግን በቴምር ማፍጠር ሱና ነው” ይላሉ። እርሳቸው እንደገለፁልን ‘ሱና’ ማለት ነብዩ መሐመድ የሰሩት፣ የተገበሩት፣ የተናገሩት አሊያም ሌሎች ሲሰሩት አይተው ያፀደቁት ነው።

ኡስታዝ እንደገለፁልን ነብዩ መሐመድም በሚያፈጥሩበት ጊዜ ቴምርን ይመገቡ ስለነበርና በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ እርሳቸው የተናገሩትን፣ የተገበሩትን አሊያም ያፀደቁትን መከተል ምንዳ ያስገኛል ተብሎ ስለሚታመን ቴምር ለማፍጠሪያ ተመራጭ ሆኗል።

ቴምር መመገብ ብቻ ሳይሆን የቴምር ፍሬዎቹ ቁጥር ሳይቀር ኃይማኖታዊ ይዘት አለው። ኡስታዝ ሀስን ታጁ ምክንያቱን ሲያስረዱም ” ነብዩ መሐመድ ‘አላህ ኢተጋማሽ ቁጥሮችን ይወዳል (3፣ 5፣ 7፣ 9…) የምትመገቧቸው ቴምሮችም ኢተጋማሽ የሆኑ ቁጥሮች መሆን አለበት’ ሲሉ ተናግረዋል፤ ይህም አላህ ኢተጋማሽ መሆኑንና አንድ መሆኑን ያሳዩበት ነው” ይላሉ።

አንድ ሰው የተመገባቸውን የቴምር ቁጥሮች ኢተጋማሽ ማድረጉ ሌላ መንፈሳዊ ምንዳ ያስገኝለታል ሲሉም ያክላሉ።

በመሆኑም በቴምር ማፍጠሩና የፍሬውን ቁጥር ኢተጋማሽ አድርጎ መመገቡ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው ምንዳን ለማብዛት እንደሚረዳ ያስረዳሉ።

የቴምር እርሻ
አጭር የምስል መግለጫየቴምር እርሻ

ነብዩ መሐመድ ቴምር በሌለበት ጊዜም በውሃ ፆማቸውን ይፈቱ ነበር የሚሉት ኡስታዝ ሀሰን በእስልምና እምነት በፍጥሪያ ሰዓት ቴምርን በቅርበት ማግኘት ካልተቻለ በውሃ ፆማቸውን እንዲፈቱ ታዟል ይላሉ። ይህም የእርሳቸውን ድርጊትና ቃል ለማክበር ህዝበ ሙስሊሙ ፆሙን በቴምር አሊያም በውሃ ይገድፋል። እርሳቸው ያንን የሚያደርጉበት ምክንያት ጤንነታዊ አሊያም ማህበራዊ ፋይዳ ሊሆን እንደሚችልም ኡስታዝ ያክላሉ።

ኡስታዝ እንደነገሩን ቴምርን በተመለከተ ብዙ የተነገሩ ሐዲሶች (የነብዩ መሐመድ ንግግሮች) አሉ።

ነብዩ መሐመድ ከአትክልት ውስጥ ሁሉም ነገሩ (ሥሩም፣ ግንዱም፣ ቅጠሉም፣ ፍሬውም )ጥቅም ላይ የሚውለው ቴምር ነው የሚል ተናግረዋል፤ በጎ በጎ ነገሮችንና ባህሪያትንም በቴምር እየመሰሉ የሚናገሩበት ሁኔታም እንዳለ በምሳሌነት ይጠቅሳሉ።

“በቅዱስ ቁርዓን ውስጥ እያንዳንዱ ሕይወት የተመሠረተው በውሃ ላይ ነው ተብሎ በግልፅ ተቀምጧል፤ በዚህም ምክንያት በቴምር አሊያም በውሃ ይፈጠራል።” ይላሉ- ኡስታዝ ሀሰን ታጁ።

ነገር ግን በረመዳን ወቅት የምንመገባቸው ሌሎች ምግቦች እንደየአካባቢው ባህል የሚወሰን ነው። በእኛ አገር ሳምቡሳ፣ ሾርባ እንዲሁም ሌሎች ምግቦች ይዘወተራሉ፤ በሌሎች ሙስሊም አገራትም የተለያየ የአመጋገብ ስርዓትና ምግቦች ቢኖርም ውሃና ቴምር ግን ሁሉንም የሚያመሳስሉ ናቸው ብለውናል።

ቴምር በሥነ ምግብ ባለሙያ

በኢትዮጵያ ሥነ ምግብ ሶሳይቲ የሥነ ምግብ ባለሙያ የሆኑት አቶ አብነት ተክሌ ቴምር ሙቀትን መቋቋም ከሚችሉ ፍራፍሬዎች ውስጥ የሚመደብ ሲሆን ከሚበቅልበት ቦታ አንፃር ታሪካዊ አመጣጦች ሊኖሩት ይችላል ሲሉ ይጀምራሉ።

በአብዛኛው የአረብ አገራት ሞቃት በመሆናቸው ቴምር አብቃይም ናቸው። በመሆኑም እዚያ አካባቢ ከመብቀሉ የተነሳ እንደ ልምድ የሚመገቡት ፍራፍሬ በመሆኑ ሊሆን ይችላል ሲሉ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።

በሥነ ምግብ ሳይንስ ግን ቴምር እንደማንኛውም ፍራፍሬ የቫይታሚን ይዘቱ ጠቃሚ እንደሆነ ይገልፃሉ።

ቴምር

እርሳቸው እንደሚሉት ፍራፍሬዎች በቫይታሚን ይዘታቸው አንዱ ካንዱ ቢበላለጡ እንጂ ይዘታቸው ለጤንነት ጠቃሚ ነው። ጠቃሚ የሆኑበትን ምክንያት ሲያስረዱም ደረቅ የሆነ ካሎሪ ስለማይሰጡ ነው። ለምሳሌ ሙዝ፣ ቴምር ሌሎችም እንደ ስኳር ጣፋጭነታቸውን ብቻ ሳይሆን አብረው ተያይዘው የሚመጡ ንጥረነገሮች በውስጣቸው ይዘዋል።

“እነርሱ ባይኖሩ እንደ የቆዳ በሽታ፣ የደም መርጋት የተለያዩ የጤና ችግሮች የመጋለጥ ዕድላችን ሰፊ ይሆን ነበር” የሚሉት ባለሙያው ጠቃሚ ከሚባሉት ፍራፍሬዎች ውስጥ ደግሞ አንዱ ቴምር መሆኑን ይጠቅሳሉ።

ቴምር እንደ ሌሎች ፍራፍሬዎች በውስጡ ጣፋጭነት ያለው ሲሆን የስኳሩ ዓይነት በተለይ ሰውነታችን በፍጥነት አቃጥሎት ደማችን ውስጥ ያለውን ግሉኮስ የሚጨምር ስለሆነ ተመራጭ ፍሬ ነው ሲሉ ያክላሉ።

በተጨማሪም ቴምር በውስጡ ከፍተኛ አሰር (Fiber) ያለው በመሆኑ በቀጥታ ወደ ሰውነታችን ከመግባቱ በፊት የመፈጨት ሂደት ላይ የመቆየት ባህሪም አለው ይላሉ።

በመሆኑም በረመዳን ወቅት ሰውነታችን ምንም ምግብ ሳያገኝ ስለሚውል ቀኑን ሙሉ የምናደርገው እንቅስቃሴ እንደ ጉልበት የምንጠቀምበት ንጥረ ነገር ከደም ውስጥ ወጥቶ ወደ ሴሎቻችን የሚዘዋወረውን ግሉኮስ ነው።

በመሆኑም ቀኑን ሙሉ ምግብ ሳንመገብ ስለምንቆይ ፆሙን ስንጨርሰ ይህ ንጥረ ነገር አንሶ ይገኛል። ይህንንም ለመመለስ ጣፋጭ ነገሮች ይወሰዳሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ጣፋጭ የሆኑ ምግቦች በቀጥታ ወደ ግሉኮስ ተቀይረው ደማችን ውስጥ ገብተው ለእኛ ጉልበትን እና ማነቃቃትን የሚወስዱት ጊዜ ይለያያል።

“ቴምር አንድም ስኳርነት ያለው ሲሆን ፤መጠናዊ የሆነ የግሉኮስ አጨማመርን ይፈጥራል ፤ ይህም ተመራጭ ፍራፍሬ ያደርገዋል” ሲሉ ያክላሉ።

ከሥነ ምግብ አንፃር የተጠባበሱና ጣፋጭነት ያላቸው ኬኮችና ብስኩቶች ከመውሰድ ቴምር መመገብ ለጤና ጥሩ በመሆኑ በማንኛውም ጊዜ ቢወሰድ ሲሉ ይመክራሉ- ባለሙያው።

አክለውም በማንኛውም ጊዜ የምንመገባቸው ምግቦች ተመጣጣኝ እንዲሆኑ ይመከራሉ። “ለዚህም ደግሞ ትልቁ ግብዓት አትክልትና ፍራፍሬዎች ናቸው” ሲሉም ይገልፃሉ።

በአገር አቀፍ ደረጃ በአውሮፓውያኑ 2013 ሰዎች ምን ይመገባሉ? (Food Consumption Survey) በሚል የተጠና ጥናት እንደሚያመላክተው የኢትዮጵያ ህዝብ አትክልትና ፍራፍሬ አጠቃቀሙ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

አቶ አብነት እንደሚሉት የዓለም ጤና ድርጅት አንድ ሰው በቀን ውስጥ 400 ግራምና ከዚያ በላይ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲመገብ የሚመክር ቢሆንም የኢትዮጵያ ግን ዝቅተኛ ሆኖ ነው የተገኘው። በመሆኑም ቴምርን ጨምሮ ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬዎች የኢትዮጵያ ህዝብ በአግባቡ እየተመገበ አይደለም።

ጥናቱ አቅርቦትን በተመለከተ ያለው ነገር ባይኖርም የተመረተው እየተሸጠ ፤ ምርት የለም ወይም ከምርት በኋላ በአቀማመጥ ችግር እየጠፋ ነው የሚል ሦስት ግምቶችን ያስቀምጣሉ።

በጥናቱ የኢትዮጵያ ህዝብ በአብዛኛው የሚመገበው የእህል ዘሮችን፤ እንደ ስንዴ፣ በቆሎ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ሥራ ሥሮች እንደ ድንችና ካሳቫ የመጠቀም ነገሮች ያሳያል ብለውናል።

ይሁን እንጂ የእንስሳት ተዋፅኦ ፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ የጥራጥሬ አጠቃቀም ዝቅተኛ ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን ትልቅ ለውጥም የሚፈልግ ነው ሲሉ አክለዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

24 Comments

 1. Admiring the hard work you put into your site and detailed information you present.
  It’s great to come across a blog every once in a while that isn’t the
  same out of date rehashed information. Fantastic read!
  I’ve bookmarked your site and I’m including your RSS feeds to my Google account.
  adreamoftrains best web hosting 2020

 2. Have you ever thought about adding a little bit more than just your articles?
  I mean, what you say is fundamental and everything.
  However imagine if you added some great pictures or videos to give your posts more, “pop”!
  Your content is excellent but with pics and video clips, this website could undeniably be
  one of the very best in its niche. Fantastic blog!

 3. Admiring the hard work you put into your site and detailed information you offer.
  It’s good to come across a blog every once
  in a while that isn’t the same outdated rehashed information. Excellent read!
  I’ve bookmarked your site and I’m including your RSS feeds to my Google account.

 4. Appreciating the persistence you put into your website and in depth information you provide.
  It’s awesome to come across a blog every once in a while that isn’t the same outdated rehashed information. Great
  read! I’ve saved your site and I’m adding your RSS feeds to
  my Google account. 3gqLYTc cheap flights

 5. Hello, i think that i saw you visited my site thus i came
  to “return the favor”.I am trying to find things to improve my
  web site!I suppose its ok to use some of your ideas!!

 6. Thanks for your personal marvelous posting!
  I really enjoyed reading it, you’re a great author.
  I will remember to bookmark your blog and may come back very
  soon. I want to encourage you to definitely
  continue your great work, have a nice evening!

 7. Today, while I was at work, my cousin stole my apple ipad and tested to see if it can survive a twenty five foot drop, just
  so she can be a youtube sensation. My apple ipad is now broken and she has 83 views.
  I know this is entirely off topic but I had to share it with
  someone!

 8. Great blog here! Also your website lots up fast!
  What web host are you the usage of? Can I am getting
  your associate hyperlink in your host? I wish my web site loaded up
  as fast as yours lol

 9. Please let me know if you’re looking for a article writer for your
  weblog. You have some really good articles and
  I feel I would be a good asset. If you ever want to take some of the load off,
  I’d love to write some articles for your blog in exchange for a link
  back to mine. Please blast me an email if interested. Thank
  you!

Comments are closed.