በረመዳን ፆም ወቅት ሰውነታችን ውስጥ ምን ይካሄዳል?

በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ረመዳንን በጾም ያሳልፋሉ። ጀንበር ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ። ሰውነታችን ከጾም ጋር የሚተዋወቀው ለመጨረሻ ጊዜ ምግብ ከቀመስን ከስምንት ሰዓታት በኋላ ነው። ይህም ማለት አንጀታችን ከተመገብነው ምግብ የሚያገኛቸውን ንጥረ ነገሮች በሙሉ አሟጦ ከጨረሰ በኋላ ነው የሚሆነው።

ከዚህ በኋላ ሰውነታችን ተስፋ ይቆርጥና ፊቱን ጡንቻችንና ጉበታችን ውስጥ ወደተከማቸ ጉሉኮስ ያዞራል። የተቀረው የሰውነታችን አካል ጉልበት የሚያገኘውም ከዚህ የመጠባበቂያ ግምጃ ቤት ይሆናል ማለት ነው።

ከጡንቻና ከጉበት የጉሉኮስ ክምችት ሲያልቅ ሰውነታችን ሌላ አማራጭ ስለማይኖረው ስብን (Fat) ማቃጠል ይጀምራል፡፡ ከዚህ በኋላ ሙቀትና ጉልበትን የሚያገኘውም ከሌላ ሳይሆን ስብን በማቃጠል ነው፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ መልካም ነገሮች ይከሰታሉ፡፡ የሚቃጠለው ስብ በመሆኑ ክብደት መቀነስ፣ የኮሌስትሮል መጠን መውረድ ይኖራል፡፡ የስኳር መጠናችን በዚህ ወቅት ዝቅ ማለቱ አይቀርም።

ሆኖም በደማችን ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ስለሚቀንስ ድካምና መዛልን ያስከትልብናል።

ይህን ተከትሎ መጠነኛ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና መልካም ያልሆነ የአፍ ጠረን ሊከተል ይችላል። ይህ የሚሆነው በረሀብ ምክንያት ሆዳችንን ሲሞረሙረንና ያለ ምግብ መቆየቱ ለሰውነታችን እየከበደው ሲመጣ ነው።

ከ3-7ኛ ቀን፤ ሰውነታችን በፈሳሽ እጥረት የሚጎዳበት ጊዜ

ሰውነታችሁ ጾሙን እየተለማመደ ሲመጣ በውስጣችን የሚገኘው ክምችት ስብ እየተሰባበረ ራሱን ወደ የደም ስኳርነት (Blood sugar) ይለውጣል።

የምንወስደው ፈሳሽ መጠን እየቀነሰ መምጣቱ በሰውነታችን ውስጥ ያለው ፈሳሽ ወደመሟጠጥ (ዲሀይድሬሽን) ስለሚያመራ በ”ማፍጠሪያ” ሰዓትና ከዚያም በኋላ ባለው የሌሊቱ ክፍለ ጊዜ በርከት ያሉ ፈሳሾችን መውሰድ ይመከራል።

በጾም መግደፊያ ሰዓት የምትወስዱት የምግብ መጠን ጉልበት ሰጪ የሆኑ ተመጣጣኝ ምግቦችን ማግኘት ይኖርበታል። በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦች ባሻገር ጨው እና በርከት ያለ ውኃ ከሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦች ጋር ማግኘት ለሰውነታችን መልካም ሁኔታን ይፈጥራል።

ከ8ኛ-15ኛ ቀናት

በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጾሙን ተላምዶታል። በዚህም የተነሳ ድካምና መዛሉ እንደመጀመርያዎቹ ጊዜያት ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም።

ዶክተር ራዚን ማህሩፍ የአኔስቴሺያና የጽኑ ሕሙማን ሕክምና አማካሪ ናቸው። በካምብሪጅ አዴንብሩክ ሆስፒታል ውስጥ ነው የሚሠሩት። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ጊዜ ፆሙ ለሰውነታችን ሌላም በጎ ጎን ይዞ ይመጣል።

ለምሳሌ በሌላው ጊዜ በርከታ ያለ ካሎሪ ያላቸው ምግቦችን የምንወስድ ከነበረ ሰውነታችን ሥራዎችን በአግባቡ ለመፈፀም ፈተና ውስጥ ይወድቅ ነበር። ወይም ደግሞ እክል ይገጥመዋል። በጾም ጊዜ ግን ይህ ሁኔታ ይስተካከላል።

“ምክንያቱም የካሎሪ ክምችት ስለማይበዛበት ሰውነታችን ወደ ሌሎች ሥራዎች ትኩረቱን ያደርጋል” ይላሉ ሐኪሙ፡፡ ለዚህም ነው “ጾም ኢንፌክሽን በመዋጋትና ጤናን በመመለስ አስተዋጽኦ የሚኖረው።”

ከ16ኛ- 30ኛ ያሉ ቀናት

በረመዳን ሁለተኛው ምዕራፍ (ከ15ኛው ቀን ጀምሮ) ሰውነት ሙሉ በሙሉ ጾሙን ይላመዳል። በዚህ ጊዜ እነ ደንዳኔ፣ ጉበት፣ ኩላሊት እንዲሁም ቆዳ ሁሉም ራሳቸውን በማፅዳት ሂደት (ዲቶክሲፊኬሽን) ውስጥ ነው የሚሆኑት።

ዶክተር ማህሩፍ እንደሚሉት በዚህ ወቅት ጤና ተመልሶ፣ ሰውነታችን የቀድሞውን ጉልበቱን የሚያገኝበትና የማስታወስ አቅምና ትኩረት የማድረግ ብቃት ወደ ቀድሞው ሁኔታ የሚመለስበት ጊዜ ነው።

በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጉልበት ለማግኘት ወደ ፕሮቲን መሄድ አይኖርበትም። ይህ የሚሆነው ብዙዉን ጊዜ ረሀብ ሲሰማንና ሰውነታችን ከጡንቻዎቻችን እየቀሰመ የሚወስደውን ምግብ ማደን ሲጀምር ነው። በዚህ መንገድ የሚቀጥለው ግን ለቀናትና ለሳምንታት በተከታታይ ስንጾም ነው።

የረመዳን ጾም የሚጸናው የየዕለቱ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ብቻ ስለሆነ ሰውነታችን ጉልበት ከምግብ እንዲያገኝ የ “ኢፍጣር” ሰዓት ዕድል ይሰጠዋል። ፈሳሽም እንደልብ ያገኛል። ይህ ጡንቻዎቻችን ውስጥ ያለን ክምችት ለመጠባበቂያነት ያቆይልናል። የተወሰነ ኪሎ እንድንቀንስም ይረዳናል። ይህም ለሰውነት መልካም ነገር ነው፡፡

እንዲያው በጥቅሉ፣ ጾም ጤናን ይጎዳል?

የካምብሪጁ አዲንብሩክ ሆስፒታል ሐኪም ዶክተር ማሕሩፍ ምላሻቸው “እንደሁኔታው” የሚል ነው። እንደርሳቸው አመለካከት በርከት ያሉ ሁኔታዎች ፆምን ለሰውነታችን ጎጂም ጠቃሚም ሊያደርጉት ይችላሉ።

ጾም ለሰውነታችን አሪፍ የሚሆንበት አንዱ ምክንያት መቼ ምን መብላት እንዳለብን ትኩረት እንድናደርግ ስለሚያስችለን ነው። ሁለተኛው ክብደታችንን መቆጣጠርና፣ የካሎሪ መጠን መወሰን ስለሚያስችል ነው፡፡

ለወር ያህል መጾም እምብዛምም የሚያመጣው የጤና እክል ባይኖርም ከዚያ በኋላ ግን ለተከታታይ ጊዜ ያለማቋረጥ መጾም ግን አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ሐኪሙ ሳይጠቁሙ አያልፉም፡፡

እንደ ሐኪሙ ማብራሪያ ያለማቋረጥ መጾም በቋሚነት ኪሎ ለመቀነስ አይረዳም። ምክንያቱም ከሆነ ጊዜ በኋላ ሰውነታችን ስብን ወደ ጉልበት መቀየር ያቆምል። ከዚያ ይልቅ ፊቱን ወደ ጡንቻዎቸቻችን ነው የሚያዞረው። ይህ ጤናማ አይደለም። ምክንያቱም ሰውነታችን ከሆነ ወቅት በኋላ “በመራብ ስሜት” ላይ ስለሚቆይ ነው።

ሐኪሙ እንደሚሉት ከረመዳን ውጭ መጾም ቢያስፈልግ እንኳ በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እያፈራረቁ መጾም በመደዳ ለተከታታይ ቀናት ከመጾም እጅግ የተሻለ ጤናማ ተግባር ነው።

“ረመዳን በአግባቡ ከተጾመና በቂ ፈሳሽ በቀን ውስጥ ማግኘት ከተቻለ፣ ጠቃሚ የጡንቻ ክምችቶች ሳይቃጠል ኪሎ መቀነስ ስለሚያስችል የጤና በረከትም ያስገኛል” ይላሉ እኚሁ ሐኪም።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

23 Comments

  1. Thank you, I’ve recently been looking for info approximately this topic
    for a while and yours is the best I’ve discovered
    till now. But, what concerning the bottom line? Are you certain in regards to
    the source?

  2. Simply desire to say your article is as amazing.
    The clarity in your post is just excellent and i could assume you’re an expert on this subject.
    Fine with your permission let me to grab your feed to keep up to date with forthcoming post.

    Thanks a million and please continue the gratifying work.
    cheap flights 3gqLYTc

  3. Undeniably believe that which you stated. Your favorite reason seemed to be on the web the easiest thing to be aware of.
    I say to you, I certainly get annoyed while people think about worries that they just don’t know about.
    You managed to hit the nail upon the top and defined
    out the whole thing without having side effect , people could
    take a signal. Will likely be back to get more.
    Thanks cheap flights y2yxvvfw

  4. I’m not sure why but this website is loading incredibly slow for me.
    Is anyone else having this issue or is it a issue on my end?
    I’ll check back later on and see if the problem still exists.
    yynxznuh cheap flights

  5. Good day! Do you know if they make any plugins to assist with Search Engine Optimization? I’m trying to get my blog to rank for some targeted keywords but I’m not seeing very
    good results. If you know of any please share.
    Thanks! 31muvXS cheap flights

  6. Hi, Neat post. There’s an issue with your web site in internet explorer, would test
    this? IE still is the marketplace chief and a huge section of folks will omit your
    wonderful writing due to this problem.

  7. Thank you for every other informative web site.

    Where else may I am getting that kind of information written in such a perfect approach?

    I have a mission that I’m just now operating on,
    and I’ve been on the glance out for such information.

  8. Simply desire to say your article is as astonishing.
    The clarity in your post is simply nice and i can assume you are an expert on this subject.
    Fine with your permission let me to grab your RSS feed to keep updated with forthcoming post.
    Thanks a million and please keep up the gratifying work.

  9. I’ll immediately seize your rss feed as I can not in finding your email subscription link or newsletter service.
    Do you’ve any? Kindly allow me understand so that I may
    just subscribe. Thanks.

Comments are closed.