የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለእርግዝና!

ለእርግዝና የሚረዱ ጥሩ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ልምዶች

1. ስፐርም (የወንድ የዘር ፍሬ)!

እርግዝናን በሚያስቡበት ወቅት ሰው ሰራሽ ማለስለሻዎችን መጠቀም በፍጹም አይመከርም የዚህም ምክንያት ለወንድ የዘር ፈሳሽ ጎጂ ስለሆነ ነው፡፡ አንዳንድ ሴቶች የጥሬ ዕንቁላል ነጭ ክፍሉን እንደ ማለስለሻ ይጠቀሙበታል በዚህ አጋጣሚ እንቁላሉ የተበላሸ ከሆነ ኢንፌክሽን ሊከሰት ይችላል፡፡ የምህጸን በር ፈሳሽ ንፍጥን ለመጨመር ውሃ በብዛት መጠጣት፣ ሮቢቲሱን እና/ወይም ኢፖ መውሰድ ይመከራል፡፡

2. አቅጣጫ (ፖዚሽን)!

በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ወንድ ከላይ ሆኖ በሚያደርግበት ወቅት ለማህፀን በር ቅርብ ከመሆኑ አንፃር በጣም ተመራጭ አቅጣጫ ነው፡፡ በመሬት ስበት አማካይነት ሴቶች ከላይ የሚሆኑበት የግብረ ስጋ ግንኙነት አቅጣጫ በጣም ጎጂና ተመራጭ ያልሆነ ነው፡፡

3. በጀርባ መንጋለል (መተኛት)!

አንዳንድ ሴቶች እንደሚሰጡት አስተያየት በዳሌያቸው ስር ትራስ አስገብቶ አልጋ ላይ በጀርባ ተንቶ እግርን ልክ ብስክሌት እንደሚነዱ ከፍ በማድረግ ቢይንስ ለ 20 ደቂቃ መቆየት ጠቃሚ ነው ይላሉ፡፡ ሌሎች ሴቶች ደግሞ ቢያደርጉም ባያደርጉም ለውጥ እንደሌለው ይናገራሉ ምርጫው የእርስዎ ነው ዋናው ቁምነገር ግን ለ 20 ደቂቃ በጀርባዎ ተጋድመው የሚቆዩ ከሆነ ሊወጣ ወይም ሊወገድ የሚችለው ጤናማ ያልሆነ ስፐርምና የሴመን ፈሳሽ ነው፡፡ ጤናማ የስፐርም (የወንድ የዘር ፈሳሽ) ወደ ሴት ሃፍረተ ስጋ ውስጥ ከተረጨ በኋላ ወዲያው ወደ ማህጸን ይጓዛል ስለዚህ ከሴት ሃፍረተ ስጋ መርዛማ አካባቢ ይርቃል፡፡

4. የጡንቻዎች ጥንካሬ!

የሴት ሃፍረተ ስጋ ጡንቻዎችን ከመጨመር ባሻገር ኬግልስ የሚባለው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ በሴት ሃፍረተ ስጋ ውስጥ የቀረውን የወንድ የዘር ፍሬ ወደ ውስጥ ለማስገባት መሥራት ጠቃሚ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ ሽንትዎን መሽናት የለንዎትም፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.