በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በከባቢ አየር ላይ የሚኖረው የካርበንዳይ ኦክሳይድ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር እንደሚችል አንድ ጥናት አመላከተ።
ጥናቱን ያካሄዱት የሜት ቢሮ ተመራማሪዎች በያዝነው ዓመት በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ክስተቶች ምክንያት በከባቢ አየር ላይ የሚለቀቀው የካርበንዳይ ኦክሳይድ መጠን በከተፍኛ ሁኔታ ሊጨምር ይችላል ብለዋል ።
በተለይም ሰው ሰራሽ በሆኑ ድርጊቶች ምክንያት በየአመቱ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው የካርበንዳይ ኦክሳይድ መጠን ከፍተኛ መሆኑ ነው የተገለፀው።
ከዚህ ባለፈም በያዝነው ዓመት የፓሲፊክ ሞቃታማ ክልል አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ሙቀትን የሚያስተናግድ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህ ምክንያትም የዕፅዋት እድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከማሳረፉም በላይ፥ የሚጠቀሙት የካርበንዳይ ኦክሳይድ መጠንም ዝቅተኛ ይሆናል ነው የተባለው።
ይህ ሁኔታም በከባቢ አየር ላይ የሚለቀቀውን የካርበንዳይ ኦክሳይድ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምረዋል።
እንደ ተመራማሪዎች ትንበያ በ2019 በከባቢ አየር ላይ የሚኖረው የካርበንዳይ ኦክሳይድ መጠን 441 ፒፒኤም ሊደርስ ይችላል።
ስለሆነም በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በከባቢ አየር ላይ የሚለቀቀው የካርበንዳይ ኦክሳይድ መጠን ከምንጊዜውም የበለጠ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
ይህ ሁኔታም በከባቢ አየር ላይ ያለውን የካርበንዳይ ኦክሳይድ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር ሰደድ እሳትና መሰል ችግሮች እንዲከሰቱ የሚያደርግ መሆኑ በጥናቱ ተመላክቷል።
3,11,13 The FDA us up to 20 reduction between. sildenafil reviews Mwnpew otemiz