የምናዘወትራቸው የምግብ አይነቶች ረሃብን ከማስታገስ በዘለለ ለአእምሯችን ጠቀሜታ እንዳላቸው ባለሙያዎች ይጠቁማሉ።
በተለይም አንዳንድ ምግቦች እና መጠጦች ደግሞ የአእምሮን የመስራት አቅም በማሳገዱ ረገድ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተነግሯል።
ከእነዚህ ምግቦች እና መጠጦች ውስጥም ቀጥሎ የተዘረዘሩት ተጠቃሽ ናቸው።
- በሻይና ቡና ውስጥ የሚገኝ ካፌይን
ጠዋት ቡና ወይም ሻይ የመጠጣት ልምድ ካለን ለአእምሯችን የመስራት አቅም መጨመር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ነው የሚነገረው።
ምክንያቱ ደግሞ በቡና ወይም ሻይ ውስጥ ያለው ካፌይን ንጥረ ነገር የአእምሯችንን ትኩረት የማድረግ አቅም የሚያሳድግ አንዲሁም አእምሯችን አዳዲስ የማስታወስ ችሎታን እንዲያዳብር ስለሚረዳ መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የምንሰራ ከሆነም አስቀድመን ካፌይን የምንወስድ ከሆነ የአካል ብቃት እንቅሰቃሴ የመስራት አቅማችንን ያጠናክራል የተባለ ሲሆን፥ ከስፖርት በፊት ስፕሪስ መጠጣት መልካም ነውም ተብሏል።
2. እንቁላል
በፕሮቲን የዳበረው እንቁላልም የረሃብ ስሜትን ከማስታገስ በዘለለ የአእምሯችንን አቅም በማሳደጉ ረገድ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ እንደሆነም ነው የሚነገርለት።
እንቁላል ከፕሮቲን በተጨማሪም ኮሊን በተባለ ንጥረ ነገር የዳበረ ነው የተባለ ሲሆን፥ ይህም የአእምሮን የመስራት አቅም ለማሳደግ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑም ተገልጿል።
3. አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች
እንደ ጎመን፣ ቆስጣ፣ ሰላጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ አበባ ጎመን፣ ብሮኮሊ እና ስፒናች ያሉ አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክትሎች በቫይታሚን ንጥረ ነገር የዳበሩ ምግቦች ናቸው።
እነዚህን ምግቦች አዘውትሮ መመገብም አየእምሮን እቅም ያሳድጋል የተባለ ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪ ግን በእድሜ መግፋት የሚመጣውን የማስታወስ ችሎታ መቀነስን ለመከላከል እንደሚረዳም ታውቋል።
4. አሳ
የተመጣጠነ የምግብ ስርዓት እንዲኖረን አዘውትረን አሳ እንድንመገብ ይመከራል፤ በተለይም በሳምንት ቢያንስ ሶስት ቀን አሳን የምትመገብ ነብሰ ጡር ሴት ለልጇን የአእምሮ እድገት እንድትጠቅም ነው ጥናቶች የሚያመላክቱት።
5. ውሃ
ውሃ የሰው ልጅ በምድር ላይ እንዲኖር ከሚያስፈልጉት መሰራታዊ ነገሮች ውስጥ በቀዳሚው ተርታ እንደሚሰለፍ ይታወቃል።
ውሃን በአግባቡ መጠጣት እና ሰውነታችን በቂ ውሃ እንዲያገኝ ማድረግ ደግሞ በተለይም አእምሯችን በአግባቡ ስራውን እንዲሰራ ያደርጋል የተባለ ሲሆን፥ በተለይም ጠዋት ስንነቃ ውሃን መጠጣት ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል።
Adverse any lubricator in long-standing medication drugs online or a reduction unguent, such as conformist lubricant, and suggestion some on the gamble with a drug accumulation. sildenafil pill Yrluwm xbbxgg