ማጅራት ገትር

meningitis colorful word on the wooden background

የማጅራት ገትር በተለይ በበሽታ አምጪ ተዋህሲያን በመወረር ምክኒያት የሚከሰት የአንጎልና የህብለሰረሰር ሽፋን መለብለብ ችግር ነው።

ብዙ ጊዜ ለበሽታው የሚዳርጉት ቫይረሶች ናቸው። ነገር ግን ባክቴርያ፣ ትላትሎቸና ፈንገሶች ምክኒያት ሊመጡ ይችላሉ።
የበሽታው ምልክቶች፦
• ድንገተኛና ሃይለኛ ትኩሳት
• የማጅራት አለመንቀሳቀስ ወይም መገተር
• ከሌላው ጊዜ የተለየ ሃይለኛ ራስ ምታት
• ሃሳብን መሰብሰብ አለመቻል
• ማንቀጥቀጥ
• ለመተኛት ወይም ለመሄድ መቸገር
• ብርሃን መጥላት
• የምግብ እና የመጠጥ ፍላጎት መቀነስ
• የአተነፋፈስ መፍጠን

ከአንድ አመት በታች ለሆኑ ህጻናት ላይ ምልክቶቹ፦
• ከፍተኛ ትኩሳት
• ተወርዋሪ ትውከት
• ያለማቋረጥ ማልቀስ
• ከመጥን በላይ እንቅልፍ ወይም መንቆራጠጥ
• ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማድርግ
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• የጭንቅላት እርግብግቢት ማበጥ
• የህጻናት አንገት እና ሰውነት ግትር ማለት

ለማጅራት ገትር አጋላጭ ሁኒታውች
• እድሜ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት
• በተጨናነቀ አካባቢ ውስጥ የሚኖሩ ህብረተሰብ ክፍሎች
• እርግዝና
• ከእንስሳ ጋር ብዙ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ
• የበሽታ መከላከል ስርአታቸው ደካማ ከሆነ(የኤችኤቪኤድስ ፣ የስኳር ህመምኞች፣በሽታ መከላከል ስርአትን የሚያዳክሙ መድሃኒቶችን የሚጠቀሙ………..ወዘተ

የማጅራት ገትር መከላከያ መንገዶች፡-
• በችግሩ ውስጥ ያለ ግለሰብ በሚያስነጥስበትና በሚያስልበት ጊዜ አፉንና አፍንጫውን መሸፈን
• ህጻናቶችን በወቅቱ ማስከተብ
• የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
• በእርግዝና ወቅቶች የሚመገቡትን የምግብ አይነት በህክምና ባለሙያዎች ምክር መሰረት ማድረግ
• የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ና በቂ እረፍት ማድረግ

በየግዜው የምንፅፋቸውን መረጃዎች ለሁሉም እንዲዳረስ ሼር ያድርጉ::

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.