– ችግሩ ከተከሰተ በኋላ በፍጹም መረጋጋት ራስን አሳምኖ አምኖ መቀበል እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፤
– ራስን መውቀስ፣ ፈጣሪ ሊቀጣኝ ነው ይህን ያደረገው ብሎ ራስን አለመርገም፣ ለራስ በቂ እንክብካቤ ማድረግ፤
– ሰዎች “የእከሌ ልጅ…ዘገምተኛ ነው” እያሉ የሚያወሩት ነገር ከግንዛቤ ማነስ የሚፈጠር በመሆኑ ይህንኑ መረዳት፤
– በኦቲዝም የተጠቃን ልጅ እምብዛምም ፍቅር ማሳየት አያስፈልገውም፣ ትርፉ ድካም ነው ብሎ አለማሰብ፤
– ያልተቋረጠ ፍቅር፣ ወጥነት ያልጎደለው ባህሪ፣ ማሳየት፤
– በኦቲዝም የተጠቃን ልጅ ማሳደግ እጅግ አታካችና ሰፊ ትዕግስትን የሚጠይቅ በመሆኑ ራስን ለዚህ ማዘጋጀት፤
– ልጁ ለሚያደርጋቸው ትርጉም አልባ ድርጊቶችና ድግግሞሾች በቂ ትኩረት መስጠት፣ እንዲሁም አለማስቆም፤
– እነዚህ ድግግሞሾች በረዥም ጊዜ ሂደት ሊቀየሩና በሌላ ሊተኩ ይችላሉ፡፡ በመኾኑም ልጆቹ ለሚያደርጉት ተራ የሚመስል ነገር ዋጋ መስጠት፤
– ብዙዎቹ የኦቲዝም ልጆች አንድ የተለየ ተሰጥኦ ባለቤት ሊሆኑ ስለሚችሉ ይህንኑ መፈተሸ፦ለሙዚቃ፣ ለስዕልና ለሂሳብ ስሌቶች አስደናቂ ተሰጥኦ ባለቤት የመኾን አድላቸው ሰፊ እንደሆነ ስለሚገመት ይህንኑ ማጤንና አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ ከወላጅና የሚጠበቅ ነው፡፡
– ከሁሉም በላይ ግን ፍቅርን አለማጓደል ለአእምሮም ለጤናም እረፍት ይሰጣል፡፡
ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)
Now accounts can exhort ED as well. generic sildenafil names Deglfx nceedi
credit score chart credit score ratings business credit score how to improve credit score