የጣት ጥፍር መብላት ልምድ እስከሞት ሲያደርስ

በህይወታችን ውስጥ ሳናስተውላቸው ልምድ የሆኑብን በርካታ ጤናችንን የሚጎዱ ባህሪዎች አሉ፡፡

ለብዙዎች ህይወት መበላሸት ብሎም መጥፋት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ምክንያት የሆኑ በርካታ ጥቃቅን ምክንያቶች አሉ፡፡ ቀላልዋ አስተሳሰባችን ፤ ትንሽዋ አመጋገባት ፤ መዝናኛ ቦታችን፤ ጓደኞቻችን ጥቃቅንዋ ሳናስተውል የምናደርጋት ነገር ሁሉ በህይወታችን ውስጥ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ፡፡

አለዚህን ልምዶቻችን በህክምናው አለም ጤነኛ ናቸው አይደሉም የሚለውን ለማወቅና ተገቢውን እርምጃ አስቀድሞ ለመውሰድ በልጅዎና በቤተሰብዎ ዙሪያ የሚያስተዉሏቸውን ያልተገባ የባህሪና የልምድ ለውጦች 8809 ደዉለው ከዶክተር አለ! ሀኪሞች ጋር ይመካከሩ፡፡

ብዙዎቻችን ስንፍራና ስንድንግጥ የምናድርግው ነገር ቢለያይም የአንዳንዶቻችን ግን ተመሳሳይ ነው ፤ጥፍርን መብላት ጆን.ጂ የተባለው አሜሪካዊ የሚያደርገው ይህን ነበር፡፡

በጭንቀት በምንዋጥበት ፤በፍርሀት በምንወጠርበት ሰዓት ወደ አፋችን ልከን በጥርሳችን የምንቆረጥመው ጥፍር ግን እንደምናስበው ቀላል አይደለም ይህን ከ ጆን ጂ ታሪክ መረዳት እንችላለን፡፡

የ40 አመቱ ጆን ጂ ለረጅም አመት በዚህ ጥፍር የመብላት ልምድ እንዲተው በዶክተሮቹ የተነገረው ቢሆንም በቀላሉ ሊተወው ግን አልቻለም ፡፡ ይህ ልምዱ ወደ ኢንፌክሽን ብሎም ወደ ልብ ችግር እንደ ተቀየረ መረጃዎች ይጠቁሙናል፡፡

ዶክተሮቹ ይህ የጥፍር አበላሉ ጣቱ እስኪደማ ድረስ መቀጠሉን ገልጸው ለዚህ ልምድ ያጋለጠውም የነበረበት ጭንቀት እና ከፍተኛ ድብርት ነው ብለዋል በመጀመርያ ጥፍሩን መብላቱ ቀላል መድማትን እንዳስከተለ በኋላም እየባሰ መጥቶ ህመምን እንዳመጣበት ገልጸዋል ፡፡

ጆን ዲ ህመም ቢኖረውም ልምዱን በቀላሉ ማሸነፍ ግን አልቻለም ነበር ፡፡

ቀስ በቀስ ይሄ የጣት መድማት ወደ ኢንፌክሽንነት ቀጥሎም አፉ አከባቢ ያሉትን ባክቴርያዎች ወደ ደም መግባት ምክንያት ሆነ በዚህም ምክንያት ለ septic infection ተጋጧል፡፡ይህንን በማስመልከት መድሀኒቶችን ከመውሰዱ በተጨማሪ ጣቱ እንዲቆረጥ ምክንያት ሆኖል ፡፡

ጆን ጂ ጣቱ ከተቆረጠ በኋላ ከጭንቀቱም ሆነ ከ ህመሙ ያገገመ ቢመስልም የአርባኛ አመቱን ልደቱን ካከበረ በኋላ ግን የቀዶ ህክምና ዶከተሩ drchye እንዳሉት ይህ septic infection ጆን ጀ ለልብ ድካም ብሎም ለሞት እንደዳረገው ገልጸዋል፡፡

ለቤተሰቦቹ ያልታሰበ ድንገተኛ ድንጋጤ ከመፍጠሩ በተጨማሪ በቸልታ ያለፉት ይህ ቀላል ልምድ ልጃቸውን ህይወት መቅጠፉ ጸጸታቸውን አብዝቆታል፡፡

የዶክተር አለ መልዕክት፡-

ስለዚህ፤
1) ቆም ብለን ልምዶቻችንን እናስተውል
2) የልምዶቻችንን ጥቅምና ጉዳት እናመዛዝን
3) አመጋገባችንን ፡ አመለካከታችንን እናስተካክል
4) የሰውነት እንቅስቃሴዎችን እና ዘውትር
5) በርካታ ንፁህ ውሀ እንጠጣ
6) ስለ ራሳችን ምናስብበት ጊዜ ይኑረን

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement