ሳምሰንግ በቀጣይ ገበያ ላይ የሚያው ጋላክሲ S10 ስማርት ስልክ እስካሁን በገበያ ላይ ከዋሉት ምርቶቹ በርካታ ማሻሻያዎች የሚደረጉለት መሆኑ ተነግሯል።
ግዙፉ የኮሪያ የቴክኖሎጂ አምራች ሳምሰንግ 10ኛ ዓመቱን በማስመልከት በሚያመርተው ስማርት ስልኩ ነው ለየት ያለ ነገር ይዞ ለማምጣት ያሰበው ተብሏል።
በዚህም ሳምሰንግ በሚያመርተው አዲሱ ስማርት ስልኩ ላይ ስድስት ካሜራዎችም የሚገጥም መሆኑ ተነግሯል።
ከካሜራዎቹ ውስጥም ሁለቱ ፊት ለፊት ላይ የሚገጠሙ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ አራቱ ደግሞ በስማርት ስልኩ ጀርባ ላይ የሚገጠሙ መሆናቸውም ታውቋል።
በተጨማሪም ስማርት ስልኩ አሁን በተለያዩ ሀገራት እየተሰራ እና የተመኮረ የሚገኘውን አምስተኛ ትውልድ ወይም 5G ኔትዎርክን የማስተናገድ አቅም እንደሚኖረውም ተነግሯል።
ከዚህ በተጨማሪም በተለያየ የስክሪን ስፋት ለገበያ ይቀርባል የተባለ ሲሆን፥ የስክሪን ስፋቱም ከ5 ነጥብ 8 ኢንች እስከ 6 ነጥብ 4 ኢንች ሊሆን እንደሚችል ነው የወጡ መረጃዎች የሚጠቁሙት።
ጋላክሲ S10 ስማርት ስልክ ከወራት በኋላ ማለትም በፈረንጆቹ 2019 የመጀመሪያ ወራት ላይ ለገበያ እንደሚቀርብ ነው የሚጠበቀው።
ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)
Underneath the NHS, more distant symptoms are again nearby dual oral. female sildenafil Proxmi lrdbob