የሰዎችን ደስታና ሃዘን መካፈል፤ ለሰዎች በችግራቸው ጊዜ ያቅምን ማድረግ አብዛኞቻችን ያስደስተናል፤ እርካታም ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዴ ሰዎች በይሉኝታ ሲታሰሩና ከፍላጎታቸው እና ከአቅማቸው በላይ ጊዜያቸውን፤ ገንዘባቸውን፤ ሃሳባቸውን ለሌሎች ሰዎች ደስታ ሲያውሉ ይታያል፡፡ ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት፡፡

የይሉኝታ መንስኤዎች

– ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት
– በራስ መተማመን ማነስ
– ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ
– የውስጥ መረጋጋት ከሌለን
አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ
ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡-በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ

ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች መገለጫ ባህሪያት

– ከሌሎች ሰዎች ሃሳብ ጋር ሁሌም መስማማት እንዳለብን ሲሰማን
– ሰዎችን ሊያስደስታቸውና ሊያስከፋቸው ይችላሉ ብለን የምናስባቸው ነገሮች ላይ በብዛት መጨነቅ
– ሳናምንበትም እንኳ ቢሆን ስለሌሎች ሰዎች መጥፎ ነገር ሲወራ አብሮ ማማት
– ሰዎች ስለኛ ምን ሊያስቡ እና ምን ሊናገሩ እንደሚችሉ ማሰብና መጨነቅ
– የሃሰብ ልዩነቶችንና ግጭቶችን ተጋፍጦ በሃሳብ ከመርታት ይልቅ መሸሽ፤ ሃሳቦች ሳይብላሉ ማቋረጥ
– ሰዎች በውይይት መሃል የተለየ ሃሳብ ሲያነሱ ከሃሳቡ ይልቅ ሰዎች ላይ ማተኮር
– ሃሳባችን ከማንጸባረቅና ላመንበት ነገር ከመቆም ይልቅ ለቡድን ተጽእኖ እጅ መስጠት
– ከደንብና መመሪያ መከበር ይልቅ በሰዎች ለመሞገስና ለመከበር ትኩረት መስጠት
– የፈለገውን ያህል ዋጋ ቢያስከፍለንም ሌሎችን ላለመሳከፋትና ላለማበሳጨት መጣር
– አይሆንም የማለት ድፍረት ማጣት፤ ለሁሉም ነገር እሺን ማስቀደም
ይሉኝታ የሚያስከትለው ጉዳት
– በራሳችን ህይወት ደስተኞች አንሆነም፤ ስልቹዎች እንሆናለን
– ከሰዎች የምንጠብቀውን ማበረታትና ተቀባይነት ሁሌም ላናገኝ እንችላለን
– ራስ ወዳድና በሌሎች ሰዎች መጠቀም ለሚፈልጉ ሰዎች ተጋላጭ እንሆናለን
– ሁሉም ቦታ ለመገኘት ስንጥር በስራችን ውጤታማ አንሆንም

ይሉኝታን ለመቀነስ የሚረዱ መንገዶች

– ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት
– ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ?
– በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ
– አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ
– በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ
– ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር
– ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር
– ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል ናቸው፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

9 Comments

  1. I used to be very happy to seek out this web-site.I wanted to thanks to your time for this wonderful learn!! I undoubtedly enjoying each little bit of it and I’ve you bookmarked to check out new stuff you blog post.

  2. There are some attention-grabbing closing dates on this article however I don抰 know if I see all of them heart to heart. There is some validity but I will take hold opinion till I look into it further. Good article , thanks and we would like extra! Added to FeedBurner as well

  3. I抦 impressed, I need to say. Really rarely do I encounter a blog that抯 each educative and entertaining, and let me tell you, you have got hit the nail on the head. Your idea is outstanding; the difficulty is one thing that not enough individuals are speaking intelligently about. I am very glad that I stumbled throughout this in my seek for something regarding this.

  4. I found your blog website on google and test just a few of your early posts. Continue to keep up the very good operate. I just further up your RSS feed to my MSN News Reader. Looking for ahead to reading extra from you later on!?

  5. Once I initially commented I clicked the -Notify me when new feedback are added- checkbox and now each time a remark is added I get 4 emails with the identical comment. Is there any manner you’ll be able to take away me from that service? Thanks!

  6. A powerful share, I just given this onto a colleague who was doing a bit of evaluation on this. And he in fact bought me breakfast because I found it for him.. smile. So let me reword that: Thnx for the deal with! However yeah Thnkx for spending the time to debate this, I feel strongly about it and love studying extra on this topic. If attainable, as you turn out to be expertise, would you thoughts updating your blog with more particulars? It’s extremely helpful for me. Massive thumb up for this weblog post!

  7. Once I initially commented I clicked the -Notify me when new comments are added- checkbox and now each time a comment is added I get 4 emails with the same comment. Is there any manner you may remove me from that service? Thanks!

Comments are closed.