መንቀሳቀስ የማይችሉ የአካል ጉደተኞች በስፓይናል ኮርድ ንቅለ ተከላ እንደገና መንቀሳቀስ መቻላቸው ተገልጿል።
የስፓይናል ኮርድ ንቅለ ተከላውን የሲውዘር ላንድ ሃኪሞች ያካሄዱት ሲሆን፥ 3 የአካል ጉዳተኞች ራሳቸውን ችለው ለመንቀሳቀስ ማስቻሉ ተገልጿል።
በዚህም ቀሪውን ህይወታቸውን ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ሊያሳልፉ የሚችሉ 3 ሰዎች በተደረገላቸው የስፓይናል ኮርድ ንቅለ ተከላ እራሳቸውን ችለው መንቀሳቀሳቸው ታውቋል።
የአካል ጉዳተኞቹ እስከ ሰባት ዓመታት ያህል ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጠው የነበረ መሆኑም ተጠቁሟል።
በቀዶ ህክምናው በኤሌክትሪክ የሚሰራ መሳሪያ የአካል ጉዳተኞች ስፓይናል ኮርድ እንዲገባ በማድረግ ከአዕምሮ መልክት ወደ እግሮቻቸው ለማድረስ መቻሉም ተነግሯል።
በኤለክትሪክ የሚሰራው እና የአካል ጉዳተኞቹ ስፓይናል ኮርድ ውስጥ እንዲገባ የተደረገው መሳሪያ ጉዳት የደረሰባቸው ነርቮች አንደገና እንዲያንሰራሩ ማድረጉንም ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል ተብሏል።
በዚሁ የህክምና ዘዴ ለውጥ ያገኙት የ30 ዓመተቱ ሲዊዘርላንዳዊዩ ደቪድ ሚዚ ስፖርት ሲሰሩ ከደረሰባቸው የስፓይናል ኮርድ ጉዳት በኋላ ከ7 ዓመታት በኋላ መንቀሳቀስ መቻላቸውን ዘገባው አመላክቷል።
ሰባስቲያን ቶብለር የተባሉ የ48 ዓመት ጀርመናዊ እና የ35 ዓመት ኔዘርላዳዊ በተመሳሳይ መልኩ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ፓራላይዝድ ሆነው የነበረ ሲሆን፥ በዚሁ ህክምና ዘዴ እንቅስቃሴ መጀመራቸውም ነው የተገለጸው።
የስፓይናል ኮርድ ንቅለ ተካለው በተለያዩ ጉዳቶች ለአካል ጉዳት የተዳረጉ እና መንቀሳቀስ የማይችሉ ዜጎች እራሳቸውን ችለው ለመንቀሳቀስ የሚያግዝ መሆኑን ተመራማሪዎች ተናግረዋል።
ምንጭ: ቢቢሲ
It should tend you are benefit of a while, in profound. generic for sildenafil Uookxb qbqbds
free annual credit report official site credit score check check your credit score