ብቸኝነት የአዕምሮ በሽታን ወደ 40 በመቶ ከፍ ያደርጋል

ብቸኝነት የአዕምሮ በሽታን ወደ 40 በመቶ ከፍ አንደሚያደረግ ተገልጿል።

በፍሎሪዳ ግዛት የጤና ኮሌጅ ተመራማሪዎች ለ10 ዓመታት በ12ሺህ 30 ሰዎች ላይ በአደረጉት ክትትል ብቸኝነት የአዕምሮ በሽታን 40 በመቶ ያህል ከፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋ።

ጥናቱ በየትኛውም ዘር፣ የትምህርት ዘረፍ፣ ፆታ እና የማህበራዊ ግንኙነት ስር የሚገኙ ሰዎች ላይ የተካሄደ ሲሆን፥ ሰፊ የማህብረሰብ አካባቢዎችን ማካተቱንም ነው የጥናቱ ተሳታፊዎች የሚገልጹት።

በጥናቱ የተካተቱ 12ሺህ 30 ሰዎች የብቸኝነት ስሜት እንደሚሰማቸው ሪፖርት ካደረጉ በኋላ በየ2 ዓመቱ በተደረገ ክትትል በ10 ዓመት ውስጥ 1ሺህ 104 ያህሉ ለአዕምሮ በሽታ መጋለጣቸው ነው የተገለጸው።

ሰዎቹ የብቸኝነት ስሜት ሲሰማቸውም ከአዕምሮ በሽታ ጋር ተያያዥነት ላላቸው ስኳር፣ የደም ግፊት፣ እና ድብርት እንደሚጋለጡም ነው በጥናቱ የተመላከተው።

የብቸኝነት ስሜት ለሲጋራ እና ሌሎች ሱስ አስያዥ አነቃቂ ንጥረ ነገሮች ተጠቃሚነት የሚያጋልጥ መሆኑም በጥናቱ ተጠቁሟል።

ከውጭ ሲታዩ በጤናማ የመሀብረሰብ ግንኙነት ተራክቦ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችም ለብቸኝነት ስሜት ተጋልጠው መገኘታቸውን የጥናቱ ተሳታፊዎች የገለጹት።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.