ምግብ በምንበላበት ወቅት ውሃ አለመጠጣት የጤና ችግር ያስከትላል

በአንዳንድ የማህበራዊ የትስስር ድረ ገፆች የሚሰራጩ የተሳሳቱ የአመጋገብ ስርዓትን መሞከር በጤና ላይ አደገኛ ሁኔታ ሊያስከትል ይችላል ተብሏል። ለምሳሌ አወዛጋቢ በሆነ መልኩ ውሃን በምግብ ወቅት አለመጠጣት የሚመለከቱ መረጃዎች የሚሰራጩባቸው ድረ ገፆች አሉ።
ይህ ያልተለመደ አመጋገብ ከየት እንደሚመጣ ወይም ለምን ያህል ጊዜ እንደሚሠራ ግልፅ ባልሆነ መልኩ ከዚህ ቀደም 17 ሺህ 600 ፅሁፎች በኢንስታግራም የማህበራዊ የትስስር ገፅ ላይ መጋራታቸውን ባለሙያዎች ያወሳሉ።

ይሁን እንጂ አዲሱ የአመጋገብ ስርዓት በጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ነው ባለሙያዎቹ የሚመክሩት። የማህበራዊ ጤና ባለሙያ የሆነው ጆኔ ላቢነር እንደሚለው፥ ውሃ መፆም ወይም አለመጠጣት የሚል ሀሳብ ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ልማድ ነው። ውሃ አለመጠጣት ማለት ምንም ቫይታሚኖች እና ማዕድናት አለማግኘት ማለት መሆኑንም ገልጿል። ምክንያቱም አብዛኞቹ ቫይታሚኖች ውሃ ውስጥ ሊሟሙ የሚችሉ በመሆናቸው በየቀኑ ውሃ ያስፈልጋቸዋል።
በተጨማሪም ውሃ ካልጠጣን ፕሮቲን አይኖርም ማለት ነው፤ ይህም በሆርሞኖች እና ኢንዛይሞች ውስጥ አሚኖ አሲዶችን እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ ጡንቻችን ለአላስለፋጊ ድካም ይዳረጋል ማለት ነው።

ይህ ደግሞ በመሰረቱ በራሳችን ላይ ከፍተኛ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል። በዚህም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለ ውሃ አለመጠጣት አስመልክቶ የሚገለጹ ነጥቦች ግልፅነት የሌላቸው እና የተሳሳቱ ናቸው ተብሏል።

የምግብ ባለሙያ የሆኑት ርሂያኖን ላምበርት፥ ውሃ መፆም ማለት በመነሻነት ከረሀብ ጋር እንደሚመሳሰል ጠቁመዋል። ይህ የሆነበት ምክንያት ለሰውነት የሚያስፈልገውን ካሎሪ በሚከለክሉበት ጊዜ የጤና ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ነው የተናገሩት። በአጠቃላይ እንደዚህ አይነት የተሳሳቱ መረጃዎች ወደ አስጊ የአመጋገብ እጥረቶች ሊወስዱ እና የአጥንትን ጡንቻ ማጣት ሊያስከትሉ ይችላሉ ብለዋል።

ምንጭ: ማኅደረ ጤና

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.