Goiter | እንቅርት

ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች
-በምግብዎ ዉስጥ የአዮዲን ንጥረነገር
-ሴት መሆን፡- ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ለታይሮይድ እጢ ችግሮች የተጋለጡ ስለሆኑ ከወንዶች ይልቅ ለእንቅርት የመጋለጥ እድላቸዉ የሰፋ ነዉ፡፡
-እድሜ፡- እድሜ እየጨመረ በመጣ ቁጥር እንቅርት የመከሰቱ እድል እየጨመረ ይመጣል፡፡
-መሰል ችግር በቤሰብ ዉስጥ ከነበረ
-እርግዝናና ማረጥ፡- መክንያቱ ምን እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ እንቅርት በነፍሰጡሮችና ባረጡ ሴቶች ላይ በብዛት ይከሰታል፡፡
-አንዳንድ መድሃኒቶች
– ለጨረር መጋለጥ
ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች፡-
የእንቅርት ህክምና እንደ እንቅርቱ መጠን፣የህመም ምልክትና እንቅርቱ እንዲከሰት እንዳደረገዉ መሰረታዊ ችግር ሊለያይ ይችላል፡፡ ስለሆን የህክምና ባለሙያዎች የሚከተሉትን ዘዴዎች ሊከተሉ ይችላሉ፡፡
-በቅርበት መከታተል፡- የእንቅርትዎ መጠን አነስተኛ ከሆነ፣ህመም ከሌለዉና ስራዋን በአግባቡ እየተወጣች ከሆነ የህክምና ባለሙያዎ መከታተሉን ብቻ ሊመርጡ ይችላሉ፡፡
-መድሃኒቶች፡- የታይሮይድ ዕጢዉ የሚያመነጨዉ ሆርሞን መጠን ማነስ/መብዛት ካለዉ መድሃኒቶች ሊጀመርልዎ ይችላል፡፡
-የቀዶ ጥገና

ምንጭ: ዶክተር አለ

Advertisement

5 Comments

  1. እኔ በተደጋጋሚ የገጣጠሚያየ(ጉልበቴ ላይ፣ የእጀ አንገት፣ የጀርባ አጥንቴ) ደርሶ እየወለቀብኝ ከግልና ከመንግስት ሆስፒታሎች የደምና የራጅ ምርመራ ሳደርግ “ሙሉ ጤነኛ ነህ የሰውነት እንቅስቃሴ ስለማትሰራ ነው” የሚሉኝ ዶክተሮች በዙ። ግን እኔ መቀመጥ የማልወድ ዘወትር መንገድ የማበዛ ነኝ። ከዛ ፍል ውሀ ገብቸ የተወሰነ ተሻለኝ። ነገር ግኝ ብርድ ሲሆን በጣም ይበርደኛል፤ ሙቀት ሲሆን በላብ እጠመቃለሁ። እንቅልፌ አልመጣልኝ ስለሚል እስከ 8:00 አመሻለሁ። ከሰው ጋር ተጣላ ተጣላ ይለኛል። ክብደቴ ከ1998 ዐ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ 58 ኪ ግ ነኝ አልጨምር አልቀንስ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ያፍነኛል። በዘህ ስጨናነቅ ቆይቸ ትንሽ አመመኝና ሀምሌ 2010 ዐ.ም ባህር ዳር ከተማ አዲናስ አጠቃላይ ሆስፒታል ለምርመራ ገባሁ። ዶክተሩም ልክ ገና እንደተቀመጥኩ ትኩር ብሎ አየኝና “የእንቅርት በሽታ/Goitor/ እንዳለብህ ታውቃለህ?” ሲሉኝ ኧረ በጭራሽ አልኳቸው። ለማንኛውም የደም ምርመራ አድርግ አሉኝ። በሽታውም በከፍተኛ ሁኔታ ሆርሞን መጨመር ስለነበር መድሀኒት እየወሰድኩ አሁን 7 ወር ሞላኝ። ህመሙም ብዙ ለውጥ አለው አሁን የልብ ትርታየ ተስተካክሏል። ክብደትም ጨምሪያለሁ።መነጫነጨም ቀንሷል። ስለዚህ እንደኔ ባልታወቀ በሽታ የምትሰቃዩ ካላችሁ ፤ የእንቅርት ምርመራ አድርጉ። እኔ ወንድ ልጅ በእንቅርት በሽታ መያዙን ያወቅሁት በእኔ ላይ ሲገኝ ብቻ ነው። ደግሞ አንገቴ ላይ የሚታይ አባጣ ስሌለው የሚታይ አይደለም።

Comments are closed.