Kiremt and Reading | ክረምትና መጽሐፍ

መፅሀፍ አዟሪዎች ከተመረጡ መፅሀፍ መካከል ምርጦቹን ነው ይዘው የሚዞሩት ይላል መኮንን። “ቢሸጡ ጥቅም ያላቸው፣ አንባቢም ይፈልጋቸዋል የተባለውን ነው ይዘን የምንዞረው።”

መኮንን ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ መነን አካባቢ ነው፤ መፅሀፍ ማንበብ ይወድ እንደነበር ያስታውሳል። ስራ ሲፈታም ፒያሳ መፅሀፍ ዘርግተው የሚሸጡ ጓደኞቹ ጋር እየሄደ መዋል ጀመረ።

ጓደኞቹ ጋር ሲውል ያስተዋላቸው ነገሮች ግን የስራ በር ከፈተለት። ወደ ጃፋር መፅሐፍት መሸጫና ማከፋፈያ ሄዶ በአዟሪነት ስራ ጀመረ።

በጋሪ አዙሮ መፅሐፍ የሚሸጥ 120 መፃህፍት ብቻ ነው መያዝ የሚችለው የሚለው መኮንን በጀርባው ተሸክሞ ይዞ የሚዞር ደግሞ ከ30 እስከ 50 መፅሐፍት እንደሚይዝ ይናገራል፤ አዲስ መፃህፍትን፣ ‘ኮሚሽን’ በደንብ የሚገኝባቸውን መርጠው ለምን እንደሆነ ሲያስረዳ።

“እጃችን ላይ የማይቆይ መፅሀፍ ነው የምንይዘው።”

“ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ

Getty images

የእለት አንባቢ ፍለጋ

በርካታ አዳዲስም ሆነ የጠፉ መፅሐፎች የሚገኙበት ብሔራዊ የእርሱም ማረፊያ ነው።

የበድሉ ህንፃ ጀርባን ይዞ የብሔራዊ ቲያትር ጀርባን ‘የመፃህፍት ማዕከል’ ይለዋል መኮንን። “እዚህ ተፈልጎ ያልተገኘ መፅሐፍ የትም አይገኝም” ሲልም ይወራረዳል።

ሥራውን ሲጀምር ጀምሮ ስታዲየም ዙሪያ መፅሐፍ እያዞረ የሚሸጠው መኮንን “እኛ ወደ አንባቢው ሄደን ነው እንዲገዙን የምናግባባው” ሲል ያማራል።

“ግሮሰሪ፣ ምግብ ቤት፣ ካፍቴሪያ፣ ስጋ ቤት አንባቢ ፍለጋ ይዞራል። መፅሐፍ ተሸክሞ ከመዞር ይልቅ አንባቢውን መፈለጉ፣ ማስመረጡ ማሳመኑ ከባድ ነው፤ በዚህ ላይ ደግሞ የክረምቱ ዝናብ።”

“ድራፍት ለሚጠጣ ቁርጥ ለሚቆርጥ በላተኛ መፅሐፍ ግዙኝ ማለት ፈታኙ ነገር ነው። ከዛ ይልቅ ቆሎ እና በቆልት የሚያዞሩትን ፈገግ ብለው ይቀበሏቸዋል።”

“ሌላው አንባቢን በጠዋት ፈልጎ ማግኘት ፈተና ነው፤ ትንሽ ረፈድ ማለት አለበት” ይላል መኮንን ከምሳ በኋላ ደግሞ ቢሆን ፍለጋው የተሳካ ይሆናል ሲል ይናገራል።

በደሞዝ ወቅት ገበያው እንደሚደራ የሚናገረው መኮንን ይህንን ስራ ከባድ የሚያደርገው ሌላው ክረምቱ ነው ይላል። ከላይ ሰማዩ እያለቀሰ ከስር ጎርፍ እየወረደ መፅሐፍ ይዞ ከቦታ ቦታ እየዞሩ መሸጡ ፈታኝ መሆኑን በማስታወስ።

ሌላው ይላል መኮንን “ቀኑን ሙሉ ስዞር ስውል መፅሐፍ እንዲገዙኝ ከማሳያቸው 100 ሰዎች መካከል አስሩ ይሆናል መፅሐፉን የሚያይልኝ። ከአስሩ ደግሞ አንዱ ነው ለመግዛት ፍላጎት የሚያሳየኝ፤ እርሱ ደግሞ ቀንስልኝ ብሎ ዋጋ እየቆረጠ የሚከራከር ይሆናል ይህ ደግሞ ከሚያለቅስ ሰማይ ስር ያለ ተከራካሪ ደንበኛ የበለጠ ስራውን ከባድ ያደርገዋል።”

መኮንን በስራው እጅጉን ይተማመናል። “መፅሐፍ አዟሪ እጅ ያልገባ መፅሐፍ አይሸጥም” ሲል ልቡን ሞልቶ ደረቱን ነፍቶ ይናገራል። የእርሱ ስራ በአንባቢ እና በደራሲ መካከል የተዘረጋ የንባብ የሀሳብ መስመር፣ የገበያ መልህቅ እንደሆነ ያምናል።

“አንባቢ ፖለቲካ ነፍሱ ነው” ይላል ደንበኞቹን እያስታወሰ። ልብ ወለድ የስነልቦና መፅህፍት የሕክምና የቢዝነስ የመንጃ ፍቃድ ትምህርት እንዲሁም የታሪክ መፅሐፍት በአይነት ይዞ ይዞራል።

ለምን ክረምት?

ጃፋር መፅሐፍትን በመሸጥ ስራ ላይ ለ15 ዓመታት ያህል ሰርቷል። እንደ እርሱ ከሆነ በየወሩ እቅድ ይዘው ከሚገዙ አንባቢዎች በተጨማሪ ክረምት ላይ አንባቢዎች ይበዛሉ።

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አበረ አዳሙም ማህበሩ በየዓመቱ ሰኔ 30ን የንባብ ቀን አድርጎ አስቦ የሚውልበት ምክንያት ተማሪዎችና መምህራን ከመማር ማስተማሩ ስራ እረፍት የሚያደርጉበት ወቅት በመሆኑና ይህንን የእረፍት ጊዜ ራሳቸውን ከመፅሐፍት ጋር የሚያገናኙበት እንዲሆን በማሰብ እንደሆነ ያስረዳሉ።

በአዲስ አበባ ብቻ 2000 ንቁ አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ሰኔ 30 የንባብ ቀን ተብሎ እንዲታወጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ማቅረቡንም አልሸሸጉም። ይህም ፖለቲከኞችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ መገናኛ ብዙሃን ንባብ ባህል እንዲሆን እንዲሰሩ ያደርጋል ብለው ያምናሉ።

“ንባብ የአንድ ወቅት ብቻ እንዳልሆነ የሚጠቅሱት አቶ አበረ ሰኔ 30ን እንደመነሻ በማድረግ ቀሪውን ጊዜ ሁሉ ስለንባብና መፅሐፍት የምንነጋገርበት እንዲሆን በመፈለግ ቀኑ ተመረጠ።”

ደራሲ ሕይወት እምሻው ‘ፍቅፋቂ’ የተሰኘ ሁለተኛው የወግና የልቦለድ ስራዋ በዚህ ክረምት ለገበያ ውሏል። የ60 ደራሲያን ስራዎች የተካተተበት ደቦ መፅሐፍ ላይም አንድ ስራዋ ተካትቶላታል።

“መፅሐፌ እንዲወጣ የፈለግኩት ግንቦት ላይ ነበር” ትላለች ሕይወት። “በአጋጣሚ ሲገፋ ሲገፋ አሁን ላይ ደርሷል” በማለት ክረምቱን የመረጠችው ግን በክረምት ተማሪዎች ከትምህርታቸው አርፈው ባለስራውም በዝናቡ ምክንያት ከቤቱ የሚወጣበት ጊዜ ስለሚቀንስ ጥሩ ገበያ ይኖራል በሚል እንደሆነ ትናገራለች።

መፅሐፍን ለክረምት ብለው የሚያስቀምጡ አንባቢዎች አውቃለሁ የምትለው ሕይወት ‘ንባብ ለሕይወት’ የተሰኘው የመፅሐፍ አውደርዕይ ላይ ከአንባቢዎቿ ጋር ለመገናኘት እንዳለመችም አልደበቀችንም።

የብራና ሬዲዮ አዘጋጁ በፍቃዱ አባይ በሕይወት ሀሳብ ይስማማል። ክረምት አንባቢን ቤቱ አስሮ ያስቀምጣል ስለዚህ ተመራጭ ነው ይላል። ከመደበኛ ትምህርት መፅሐፍት ውጭ ለማንበብ እድል የሚኖረውም ለዚህ እንደሆነ ይገምታል። ደራሲያንም ይህንን እድል ለመጠቀም በማሰብ ስራዎቻቸውን በዚህ ወቅት እንደሚያሳትሙ ይናገራል።

በክረምት ወቅት በርካታ ታዋቂ ደራሲያን በአንድ ላይ ስራዎቻቸውን ለህትመት ማብቃታቸው የመነበብ እድላቸውን ይቀንሰዋል ሲል ስጋቱን ይገልፃል።

ስም ያላቸው ደራሲያን በሚያወጡበት ጊዜ መፅሐፍን ለገበያ ማቅረብ ጀማሪ ደራሲዎችንና አዳዲስ መንገድን የሚከተሉ ፀሀፍትን እንዳይነበቡ ያደርጋል የሚል ስጋትም አልተለየውም።

በዓመቱ በተለያየ ወቅት መፅሐፍት ቢታተሙ እና ለገበያ ቢቀርቡ ተከታታይነት ላለው የንባብ ባህል ወሳኝ ይሆናል ሲልም ያክላል።

ወቅቱ አንባቢን ብቻ ሳይሆን አውደርዕይ አዘጋጆችንም እንደሚስብ የሚናገረው በፍቃዱ የንባብ ለሕይወትን የመፅሐፍት አውደ ርዕይ እንደምሳሌ ይጠቅሳል።

የንባብ ለህይወት የመፅሀፍት አውደ ርዕይ አስተባባሪ ቢኒያም ከበደ እነዚህ አውደ ርዕዮች በግድ ክረምት ላይ መሆን አለባቸው ብሎ አያምንም። በበጋ ወቅት በተካሄዱ አውደርዕዮች ግን የጎብኚዎች ቁጥር አነስተኛ እንደሆነ ታዝቧል።

መፅሐፍ እና ቴክኖሎጂ

በዚህ በቴክኖሎጂ ዘመን መፅሐፍት ተጠርዘው በእጃችን ሲገቡ ብቻ ማንበባችንን ለበፍቃዱ አባይ የሚደንቅ ነገር ነው። በእጃችን ያለውን ቴክኖሎጂ መጠቀም ጉዳይ ላይ ብዙ እንደሚቀረን ሲያስረዳ “ሞባይል ይዘን እጃችን ላይ ሰዓት ያሰርን፣ ሞባይል ይዘን ሰዓት የምንጠይቅ ሰዎች ብዙ ነን” ሲል ያለውን ክፍተት ያሳያል።

ለበፍቃዱ ደካማ የንባብ ባህል መኖሩ እና ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም ብዙ ገፍቶ አለመኬዱ ስኬታማነቱን ቀንሶታል።

አቶ አበረ አዳሙ በየትኛውም መልኩ ንባብ መዳበሩን ይደግፋሉ።

“ማንኛውም ሰው ሳያነብ እንዳይውል እንዳያድር ነው የምፈልገው። የማንበቢያ መንገዱ በየትኛውም መልኩ ቢሆን ንባብ የህይወታችን የዕለት ተዕለት ዘይቤ አንደኛው መልክ ቢሆን እመርጣለሁ።”

ለሕይወት እምሻው የመፅሐፍ ሽታ፣ ወረቀቱን እየገለጡ እየዳበሱ ማንበብ በእጅ ዳጎስ ያለውን መፅሐፍ ይዞ መጓዝ ምትክ የማይገኝለት ነው። በተንቀሳቃሽ ስልክ፣ በላፕ ቶፕ ወይም በታብሌት ላይ ማንበብ ለእርሷ የማይታሰብ ነው።

“በርግጥ ዘመኑ በአዳዲስ የቴክኖሎጂ መንገዶች ማንበብ የሚቻልበት ቢሆንም የኔ ምርጫ ግን የሚገለጥ መፅሐፍ ነው” ስትል ሀሳቧን ታስረግጣለች።

“መፅሀፍትን እየገለጥኩ ሳነብ ከመፅሐፉ ጋር አንዳች ግንኙነት እንዳለኝ አስባለሁ። በርግጥ አማራጩን ማስፋት ቢቻልና መፅሐፍት በመቀመሪያቸው ላይ ሆነው ማንበብ ለሚፈልጉ መቅረብ ቢችል ጥሩ ነው።”

ቢኒያም በአውደ ርዕዮች ላይ እንደታዘበው የኤሌክትሮኒክስ መፅሐፍት ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው።

“ይህ ነገር ግን በሃገራችን በአግባቡ እንዲሰራ ከኢንፎርሜሽን ዘርፉ ጋር በሚገባ ማስተሳሰር ያስፈልጋል። በመረጃ መረብ ላይ በቀላሉ መፅሐፍቶችን የምናገኝበት በቀላሉ ሰብ ስክራይብ የምናደርግበት መንገድ ቢመቻች ነገሮች አሁን ከምናስባቸው ውጭ ይሆናሉ።”

መፅሐፍ ሻጮችን ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያው ጋር ማስተሳሰር እና እነዚህን ሁለቱን በጋራ የሚመራ አንድ አካል ቢኖር መፅሐፍን ‘ዲጂታላይዝ’ በማድረግ ለአንባቢ ማድረስ ይቻላል ባይ ነው። ይህ ደግሞ ክረምትን ብቻ እየጠበቁ ከማንበብ ያላቅቅ ይሆናል የሚል ግምት አለው።

ጃፋር መፅሀፍትን በእጅ ይዞ መንቀሳቀስ ከራስ ባለፈ ለሚመለከተውም የሚተርፍ ነገር አለው ብሎ ያምናል። “ልጆች እያነበብክ መሆኑን ሲያዩ የማንበብ ፍላጎት ያድርባቸዋል። ከጤናም አንፃር እኔ የምመክረው ጥራዝ መፅሐፍትን ማንበብ ነው።”

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

12 Comments

  1. I am usually to blogging and i really admire your content. The article has actually peaks my interest. I am going to bookmark your website and maintain checking for new information.

  2. I found your blog website on google and check a few of your early posts. Continue to keep up the excellent operate. I simply further up your RSS feed to my MSN News Reader. In search of forward to reading extra from you afterward!?

  3. After study a few of the weblog posts on your website now, and I really like your method of blogging. I bookmarked it to my bookmark website listing and can be checking again soon. Pls take a look at my website online as nicely and let me know what you think.

  4. Can I just say what a relief to search out somebody who really is aware of what theyre speaking about on the internet. You definitely know tips on how to bring an issue to gentle and make it important. Extra people must read this and understand this side of the story. I cant consider youre no more well-liked since you positively have the gift.

  5. I’m typically to blogging and i actually appreciate your content. The article has actually peaks my interest. I’m going to bookmark your website and hold checking for brand new information.

  6. There are definitely lots of details like that to take into consideration. That could be a great level to convey up. I provide the ideas above as basic inspiration however clearly there are questions like the one you bring up where a very powerful thing will likely be working in trustworthy good faith. I don?t know if finest practices have emerged around issues like that, however I am positive that your job is clearly identified as a good game. Each girls and boys really feel the impression of only a moment抯 pleasure, for the remainder of their lives.

Comments are closed.