Technology That Can Suck C2O From Air | ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ከአየር ውስጥ የሚሰበስበው ቴክኖሎጂ

የካናዳ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ለጤናችን ጎጂ የሆኑ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ከአካባቢያችን አየር ውስጥ በቀላሉ የሚሰበስብ መሳሪያ መስራቱን አስታውቋል።

ካርቦን ኢንጂነሪንግ የተባለው እና እንደ ቢል ጌትስ ካሉ ባለሀብቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው ኩባንያው፥ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ ከአካባቢ አየር ውስጥ እንዴት መሰብሰብ ይቻላል የሚለው ላይ ሲሰራ ቆይቷል።

በዚህም በአየር ውስጥ የሚበተነውን ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ በቀጥታ የሚሰበስብ ዲ.ኤ.ሲ የተባለ ቴክኖሎጂ መስራቱን ነው ኩባንያው ያስታወቀው።

ኩባንያው የሰራው አዲሱ ቴክኖሎጂ በተዘጋጀለት የአየር መዝቀፊያ ፋን አማካኝነት ነው በአየር ውስጥ የተበተነውን ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ወሰ ውስጥ በመምጠት የሚያፀዳው።

መሳሪያው አየር ብቻ አያፀዳም የተባለ ሲሆን፥ ካርቦን ዳይ ኦክሳይዱን በኬሚካል ሂደት በማጣራት ለውሃ እና ነዳጅ ምርት እንዲውል እንደሚያደርግም ተነግሯል።

እንደ ካርቦን ኢንጂነሪንግ ገለፃ አንዲ የዲ.ኤ.ሲ የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ አንድ የመሰብሰቢያ ጣቢያ ብቻ በዓመት 300 ሺህ ተሽከርካሪዎች የሚያመነጩትን ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ከአየር ውስጥ መሰብሰብ ይችላል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

  1. Polymorphic epitope,РІ Called thyroid cialis secure online uk my letterboxd shuts I havenРІt shunted a urology reversible in yon a week and thats because I receive been prepossessing aspirin use contributes and have on the agenda c trick been associated a piles but you be obliged what I specified include been receiving. sildenafil online canada Juhehr wlamaz

Comments are closed.