ቀጣዩ አይፎን ስማርት ስልክ 3D ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ 3 ካሜራዎች ይኖረዋል ተባለ – 2019 iPhones Will Have Triple-Lens Camera Setup, 3D Sensing

በቀጣዮ የፈረንጆቹ 2019 ለገበያ የሚቀርበው አዲስ የአይፎን ስማርት ስልክ 3D ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ሶስት የጀርባ ካሜራ የሚገጠምለት መሆኑ ተሰምቷል።

ካሜራዎቹም ከርቀት ያለ ነገርን በማቅረብ ከፈትኛ ጥራት ፎቶ ግራፍ ማንሳትም ይሆን ቪዲዮ ለመቅረፅ የሚያስችሉ መሆኑም ታውቋል።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ከሶስቱ ካሜራዎች ውስጥ ሁለቱ ካሜራዎች ምስሎችን ከተለያየ አቅጣጫ በአንድ ጊዜ ማንሳት የሚያስችል የ3D ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ ናቸው።

ሶስተኛው ካሜራ ደግሞ ርቀት ላይ ያለን ነገር በማቅረብ በጥራት ለማንሳት የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል።

ይህም አሁን ላይ ያሉት የአይፎን ስማርት ስልክ ከሁለት እጥፍ ርቀት ላይ አቅርበው ከሚያነሱት በተሻለ ከሶስት እጥፍ ርቀት ላይ ያለን ነገር አቅርቦ ለማንሳት ያስችላል።

አሁን በገበያ ላይ ካሉት ስማርት ስልኮች ውስጥ ባለ 3 የካሜራ ስርዓትን ይዞ የቀረበው ህዋዌይ ሲሆን፥ ይህም ሁዋዌይ ፒ 20 በተባለ ስማርት ስልኩ ላይ ነው የተገጠመው።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.