የኢትዮጵያ ተረት ገፀ-ባህሪን በተንቀሳቃሽ ምስሎች የምታቀርበው የ26 ዓመት ወጣት የ DLA ሽልማት አሸናፊዋ ኢትዮጵያዊት ፌበን ኤሊያስ – Meet 26 Years Old Ethiopian Animation Artist DLA Prize Winner Feben Elias

Facebook profile page image

“ተረት ተረት” ሲባል “የላም በረት” ለማለት ከሚፈጥኑ ልጆች አንዷ ነበረች። ከልጅነት ትውስታዎቿ ተረት ትሰማ የነበረበተ ጊዜያት ዋነኞቹ ነበሩ ።

አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው የ26 ዓመቷ ፌበን ኤልያስ በህንጻ ኮሌጅ ኧርባን ዲዛይን ስትማር ከምህንድስና በበለጠ የሶስት አውታር ንድፍና ግራፊክስ ዲዛይን ይስባት ነበር።

የእንጀራ ገመዷን የዘረጋችውም በዚህ ሙያ ነው። በአርማ አድቨርታይዚን ውስጥ ንድፍና አኒሜሽን ትሰራለች።

“ጎረቤቴ ሚጢጢ የአኒሜሽን መነሻዬ”

ያሳደጓት አያቶቿ ናቸው። ሚጢጢ የምትባል የጎረቤት ታዳጊ ነበረች።

ሚጢጢ ለየት ያለ ባህሪ ስለነበራት የሰፈሩ ልጆች ባጠቃላይ ይወዷታል። ፌበን ደግሞ ጎረቤቷን ከመውደድ ባለፈ የህጻናት አኒሜሽን ገጸ ባህሪ መነሻ አደረገቻት።

“ጠያቂነቷ፣ አልበገር ባይነቷ፣ በራስ መተማመኗ፥ ለማወቅ ካላት ጉጉት ጋር ተደማምሮ ተወዳጅ አድርጓታል” ትላለች ጎረቤቷን ስትገልጽ። ልጆች በጣም ስለሚወዷት የሷን የጸጉር አሰራርና አኳኋንም ይከተሉ ነበር።

ፌበን ጎረቤቷን ተመርኩዛ ‘ድንቢጥ’ የተባለች ገጸ ባህሪ ለመፍጠር የወሰነችው በልጆች ዘንድ ተወዳጅ እንደምትሆን በማመን ነው።

ከዪኒቨርስቲ ከተመረቀች በኋላ ለስድስት ወር የሶስት አውታር ንድፍ ስልጠና በድረ ገፅ ተከታታለች። የድንቢጥን ፊልም በቤቷ ኮምፒውተር ትሰራም ጀመር።

‘ድንቢጥና አያቷ’

“አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ልጆች ከገጸ ባህሪዋ ጋር እንዲተሳሰሩ ለማድረግ ሞክሬያለሁ” ትላለች።

ድንቢጥን የምትገልፃት “የልጅነት ተሞክሮዎቼን አንድ ላይ አዋህጄ የፈጠርኳት ገፀ ባህሪ ዘወትር አዳዲስ ነገር ለመሞከር ትነሳሳለች” በማለት ነው።

ፊልሙ ላይ ድብንቢጥ የምትኖረው ከአያቷ ጋር ሲሆን፣ ጸጉሯ እንደ ብዙሀኑ የኢትዮጵያ ልጆች ጥቁርና ከርዳዳ ነው። የምትለብሰውም ጥበብ ቀሚስ ነው።

“ድንቢጥና የፕሪሙ ፍሬ” ከአኒሜሽን ክፍሎቹ አንዱ ነው። በድንቢጥ ቤት አቅራቢያ የፕሪም ዛፍ አለ። የፕሪሙ ፍሬ ሳይበስል እንዳትበላ ቢነገራትም አእምሮዋ ከመጠየቅ የማይቦዝነው ድንቢጥ “ያልበሰለ ፕሪም ጣዕም ምን ይሆን?” ስትል ትጠይቃለች። ጠይቃም አትቀር ትቀምሰዋለች።

“ታሪኩ ጠያቂ መሆንና በራስ መንገድ መሄድን ለልጆች ያስተምራል።” ትላለች ፌበን።

ፌበን የድንቢጥን ታሪክ ዲጂታል ላብ አፍሪካ በተባለ ውድድር ያቀረበችው ከወራት በፊት ነበር።

በውድድሩ ከአፍሪካ ሀገሮች የተውጣጡ 750 ሰዎች ተሳትፈው ነበር። ከነዚህ መሀከል አስሩ በሰምስት ዘርፍ አሸንፈዋል። በአኒሜሽን ዘርፍ ያሸነፈችው ፌበን የ3,000 ዪሮ ተሸላሚ ሆናለች።

በቀጣይ የድንቢጥ ታሪክ ተከታታይ ፊልም ከዛም የህጻናት መጽሐፍ ይሆናል።

 

ኢትጵያዊት ገጸባህሪ

ሲንድሬላ በዋልት ዲዝኒ ከተፈጠሩ ልቦለዳዊ ገጸ ባህሪዎች አንዷ ነች። ከአሜሪካ አልፋ በመላው አለም የብዙ ህጻናትን ልብ ማርካለች።

የሲንድሬላ አይነት አለባበስና ባህሪ ‘ተወዳጅና ተመራጭ’ መሆኑን የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሀን ይሰብካሉ። ሁሉም ሕጻናት የየሀገራቸው እውነታ እንዳላቸው የተዘነጋም ይመስላል።

“የኛን ታሪክ የሚያሳዪ የልጆች ፊልሞች እምብዛም አይደሉም። ይህ የፈጠረው ክፍተት የአፍሪካ ህጻናት ወደ አውሮፓውያን ፊልሞች እንዲያማትሩ አስገድዷል” ስትል ፌበን ትናገራለች።

“ሰውነታቸውን ታጥበው ሲጨርሱ ጸጉሬ ለምን እንደ ሲንድላ አልተኛም የሚሉ ልጆች ገጥመውኛል” ትላለች። የዚህ አመለካከት ለመለወጥ ያስችል ዘንድ ድንቢጥ ከርዳዳ ጸጉርና ወፍራም ከንፈር አላት።

ፌበን “ልጆች የፌበንን ጸባይ እና መልክ ከራሳቸው ጋር አስተሳስረው ደስ እንድትላቸው እፈልጋለሁ። በአስተዳደጓ፣ በባህሪዋና በመልኳ እነሱን የምትመስል ገጸ ባህሪ እያዪ እንዲያድጉ እፈልጋለሁ” ስትል ትገልጻለች።

Facebook profile page image

ከአፋዊ ታሪክ ነገራ ወደ ዲጂታል አኒሜሽን

ታሪክ ነገራ ለኢትዮጵያ እንግዳ አይደለም። ለዘመናት ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል ተሸጋግሯል።

በዲጂታል ዘመን አፋዊ ታሪክ ነገራ ወደ አኒሜሽንና ካርቱን እየተለወጠ ነው። ብዙ ባለሙያዎች የህጻናት አኒሜሽንና ካርቱን ይሰራሉ።

ፌበን ፊልሞቹ በጥራት ረገድ ብዙ ይቀራቸዋል የሚል አቋም ያላት “ይዘታቸው ጥሩ ነው። አሰራሩ ግን ወደኋላ የቀረ ነው። አለም ከሚሰራው አንጻር መወዳደር አልቻልንም” ትላለች።

ትምህርት ቤት አለመኖሩ የእውቀት ክፍተቱን ፈጥሯል። ብቃት ያላቸው ስቱድዮችም ብዙ አይደሉም።

የህጻናት ታሪክ በህጻንት ስነ ልቦናዊ እድገት

ተመራማሪዎች በህጻናት እድገት ሚና አላቸው ከሚሏቸው ልቦለዳዊ ታሪኮች ይገኙበታል። ፌበንም የህጻንት እድገትና የሚነገራቸው ታሪክ ትስስር ጠንካራነቱን ታምናለች።

“ልጆች ከራሳቸው ጋር ማስተሳሰር የሚችሉትና የሚወዱትን ገጸ ባህሪ የማስመሰል ባህሪ ኣላቸው” ትላለች

ልጆች የድንቢጥን ጠንካራ ጎኖች እንዲወስዱ የምትፈልገውም ለዚሁ ነው።

የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መብዛት የአኒሜሽን ፊልሞችን ተደራሽነት ያሰፋዋል ብላም ታምናለች።

“ፊልሙን ቤተሰብና ልጆች በቴሌቭዥን በጋራ እንዲያዪት እፈልጋለሁ” ትላለች።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

15 Comments

  1. What’s Taking place i’m new to this, I stumbled upon this
    I have discovered It positively useful and it has aided me out loads.

    I am hoping to give a contribution & help other users like its aided me.
    Good job. adreamoftrains website host

  2. Hi there just wanted to give you a brief heads up and let you know
    a few of the pictures aren’t loading correctly. I’m not sure why but I think its a linking
    issue. I’ve tried it in two different internet browsers and both show the same results.

  3. Valuable information. Lucky me I discovered your website accidentally, and I
    am shocked why this coincidence didn’t happened in advance!

    I bookmarked it.

  4. Hi there! I could have sworn I’ve been to this site before but after checking through
    some of the post I realized it’s new to me.
    Nonetheless, I’m definitely happy I found it and I’ll be book-marking and checking back often! 2CSYEon cheap flights

  5. I absolutely love your blog and find almost all of your post’s
    to be what precisely I’m looking for. Does one offer guest
    writers to write content to suit your needs? I wouldn’t mind writing a post or elaborating on a lot of the
    subjects you write regarding here. Again,
    awesome site! 31muvXS cheap flights

  6. Have you ever thought about including a little bit more than just your articles?
    I mean, what you say is important and everything. But think about if you added some great images or
    video clips to give your posts more, “pop”! Your content is excellent but with images and clips, this
    site could certainly be one of the best in its niche.
    Terrific blog! y2yxvvfw cheap flights

  7. I just like the valuable information you supply for your articles.
    I will bookmark your weblog and check again right here frequently.
    I’m fairly sure I will be informed a lot of new stuff right here!
    Best of luck for the following! 3gqLYTc cheap flights

  8. It’s the best time to make some plans for the future and it is
    time to be happy. I have read this post and if I could I desire to suggest you some interesting things
    or tips. Perhaps you can write next articles referring to
    this article. I wish to read even more things about it!

  9. At this time it appears like Movable Type is the best blogging platform available right now.
    (from what I’ve read) Is that what you are using on your blog?

  10. Hello exceptional blog! Does running a blog like this take a lot of work?
    I have no knowledge of programming however I had been hoping to start my own blog soon. Anyhow, if you have any ideas or techniques for new blog owners please share.
    I know this is off subject but I simply needed to ask.
    Cheers!

Comments are closed.