በእርግዝና ወቅት ከምናደርጋቸው ጥንቃቄዎች Prenatal care

በእርግዝና ወቅት ከምናደርጋቸው በርካታ ጥንቃቄዎች መካከል የአመጋገብ ባህላችንን መቀየር አንዱ እና ዋንኛው ነው ሊባል ይችላል።

በመሆኑም የማርገዝ ዕቅድ ሲኖር አስቀድሞ የአመጋገባችንን ሁኔታ ምን መምሰል ይኖርበታል? የትኞቹን ምግቦች ማዘውተር ይኖርብን ይሆን? የትኞቹንስ ማስቀረት ይጠበቅብናል? ለሚሉት ጥያቄዎች አስቀድሞ ምላሽ ማግኘቱ አስፈላጊ ነው ለማርገዝ ሲወስኑ የአመጋገብ ዘይቤዎን ሊቀይሩ ይገባል
እስኪ በእርግዝና ወቅት ከገበታችን ሊታጡ አይገባም እንዲሁም እነዚህ ምግቦች ደግሞ ፈፅሞ መዘውተር የለባቸውም ያሏቸውን ምግቦች እናካፍላችሁ፡፡
በእርግዝና ወቅት አብዝተን ልንወስዳቸው የሚገባ ምግቦች፦
ጥራጥሬ፦
ለማርገዝ የሚያስቡ እንስቶች እንደ አጃ፣ የስንዴ ዳቦ፣ ምስር እንዲሁም ከፍተኛ የካርቦሃይድሬት መጠን ያዘሉ መሰል ምግቦች ከጓዳቸውና ከገበታቸው ሊታጡ አይገባም ነው የተባለው።
የፕሮቲን ይዘታቸው ከፍ ያለ አትክልቶች፦
እንደ አኩሪ አተር የመሳሰሉትና ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ያላቸውን የአትክልት ዘሮችን መመገብ ይመከራል፡፡
አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች፦
አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች ፎሌት በተሰኘው ንጥረነገር በእጅጉ የበለፀጉ መሆናቸውን ነው ረዳት ፕሮፌሰር ቻቫሮ የሚመክሩት።
ይህ መሆኑም በቀላሉ ለማርገዝ የሚያስችልና ለጤናም ቢሆን በእጅጉ የሚመከር እንደሆነም ጠቅሰዋል።
በብረት ይዘታቸው የበለፀጉ ምግቦች፦
በብረት ማዕድን ይዘታቸው የበለፀጉ ምግቦችን ሁሉ መመገብ ሌላው በእርግዝና ወቅት የሚመከር ጉዳይ ነው።
አተር፣ ባቄላ፣ ምስር፣ ሽንብራ፣ለውዝ እና የመሳሰሉትን ማዘውተር ይገባልም ነው የተባለው።
በእርግዝና ወቅት አይመከሩም የተባሉ ምግብችና መጠጦች፦
ስብ የበዛባቸው ምግቦች፦
የታሸጉ ምግቦች፣ የተጠበሱ አልያም ቅባት የበዛባቸው ምግቦች፣ ከፍተኛ የሆነ የስብ መጠን በውስጣቸው ስለሚገኝ በተቻለ አቅም ከገበታ ልናርቃቸው እንደሚገባ ነው የሚመከረው።
በተጨማሪም እነዚህ ምግቦች የማርገዝ ዕድላችን ዝቅተኛ እንዲሆን ያደርጋሉ ተብሏል።
የለስላሳ መጠጦች፦
የለስላሳ መጠጦች በእርግዝና ወቅት መዘውተር የለባቸውም ከተባሉት መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን፥ የለስላሳ መጠጥን የሚያዘወትሩ ሰዎች ፈፅሞ ከማይጠጡት ጋር ሲነፃፀሩ የማርገዝ ዕድላቸው 52 በመቶ የቀነሰ ነው።
አልኮል፦
የአልኮል መጠጥን ቢቻል ለማርገዝ ከመወሰናችን ከወራት በፊት ማቆም እንደሚኖርብን ነው የሚመከረው።
ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በቀን እስከ 5 ብርጭቆ ድረስ የአልኮል መጠጥ መጎንጨት የማርገዝ ዕድልን ያመናምናል።
ስጋ፦
ስጋን በእርግዝና ወቅት መመገብ ማቆም የብዙዎች ፈተና ሊሆን እንደሚችል ቢነገርም እንደ የዶሮ ስጋ፣ ቀይ ስጋና ሌሎችንም የስጋ አይነቶች መመገብ በ32 በመቶ የመፀነስ ዕድልን ዝቅ እንደሚያደርግ ነው የተነገረው።

ምንጭ:- ዶክተር አለ  (Doctor Alle)

Advertisement