የአንገት ህመምን የምናስታግስባቸው ቀላል መንገዶች?

                

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በዓለም አቀፍ ደረጃ 10 በመቶ ያህል አዋቂ ሰዎች በአንገት ህመም ይሰቃያሉ። 

ከህሙማኑ መካከል 65 በመቶ በላይ ያህሉ በሽታው በህይወታቸው አንድ ጊዜ የሚጎበኛቸው ናቸው።

 ከአካል እንቅስቃሴ ማብዛት፣ ምቾት የሌለው መኝታና አቀማመጥ፣ ለረጅም ሰዓት በተመሳሳይ የሰውነት አቋም መቀመጥና ከፍተኛ ውጥረት የበሽታው መንስኤዎች እንደሆኑ ይገለፃል።

አንድን ተግባር ረጅም ጊዜ ማከናዎን ለውጥረት የሚዳርግ ሲሆን፥ በተለይም ረጅም ጊዜ ኮምፒዩተር ላይ መቆየት ችግሩን ሊያበብሰው እንደሚችል ነው የተገለጸው።

ይሁን እንጂ ችግሩን በቀላሉ በተፈጥሮአዊ መንገድ በቤታችን ውስጥ ማከም የምንችልባቸውን መንገዶች ብራይት ሳይድ ሚ አስቀምጧል።

በጀርባና በጎን በመተኛት እረፍት ማድረግም የአንገት ህመምን ለማስታገስ የተሻሉ የመኝታ አማራጮች ናቸው ተብሏል።

በረዶ የተሞላ የፕላስቲክ ከረጠት ህመሙ የሚሰማን የሰውነት ክፍል ላይ ለ15 ደቂቃዎች ያህል መያዝ ችግሩ በተከሰተበት የሰውነት ክፍል ላይ የደም ዝውወርን በማስተካክል የአንገት ህመምን የሚቀንስ እንደሆነ ታውቋል።                   

               

ነገር ግን በረዶውን በቀጥታ ከቆዳችን ጋር ንክኪ ካላው ቆዳችንን ሊጎዳው ስለሚችል ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም መረጃው ያመለክታል። 

በተመሳሳይ መልኩ ሩዝ ወይንም ስንዴ የተሞላ የሞቀ ቀረጢት ለ15 ደቂቃ ያህል ህመም የሚሰማን ቦታ ላይ ማስቀመጥ ሌላው የህመም መቀነሻ ዘዴ ሲሆን፥ በተለይም ጧት

ከእንቅልፋችን እንደተነሳንና እንቅስቃሴ ከማድረጋችን በፊት ይህን ማድረጉ ጥሩ ውጤት እንዳለው በዘገባው ተግልጿል።

ጨው ባለው ለብ ያለ ውሀ መታጠብ፣ ‘‘ቱርመሪክ’’ ሻይ በማር መጠጣት ለአንገት ህመም ማስታገሻ እንደሆኑም ተመላክቷል።

ከላይ ከተዘረዘሩ መፍትሄዎች በተጨማሪ የአንገት አካባቢ ጡንቻዎችን በማንቀሳቀስ የአንገት ጡንቻዎችን በማጠንከር የአንገት ህመምን ለመቀነስ እንደሚቻልም ተጠቁሟል።

የአቀማመጥ ስርዓትን አለማስተካከልና ለረጅም ጊዜ ስልክ ላይ መቀመጥ ለአንገት ህመም መሰረታዊ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል።

                   

በነዚህ ጉዳዮች የሚከሰቱ የአንገት ህመሞችን ለመቀነስ ፎጣ መጥቅለልና በአንገታችን ላይ በማስቀመጥ ጫፎቹን በእጅ በመያዝ ማጅራታችን ላይ እድርገን ወደ ፊታችን ትይዩ በጥንቃቄ በመሳብ የአንገት ጡንቻዎች ዘና እንዲሉ በማድረግ ህመሙን መቀነስ ይቻላል ተብሏል።

የሁለት እጆቻችን መገጣጠሚያ ዙሪያ የአንገታችንና የአከርካሪ አካባቢዎችን በአውራ ጣቶቻችና በጠቋሚ ጣቶቻችን እየተጫን ከ4 እስከ 5 ሰከንዶች በመዳፋችንና በአውራ ጣታችን ጫፎች መጫንና ማሸት ተጨማሪው በቤት ውስጥ የአንገት ህመምን ለማከም የሚያስችል አማራጭ ነው።

እነዚህን የአንገት ህመም ማስታገሻ መንገዶች ስንጠቀም በባለሙያ ምክር ብንታገዝ የበለጠ ውጤታማ እንደምንሆንም ዘገባው ያስረዳል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement