ጣዕማቸው ምን ሊመስል ይችላል? ጥሩ ሊሆን ይችላል?
ከአካባቢ ደህንነት አንፃር እንዲሁም ለእንስሳት ሥጋ እንደ አማራጭ ከመሆን አንፃር የነፍሳት ምግብ ተመራጭ ነው።
ግን ማን ነው ነፍሳትን በምግብነት እየተጠቀመ ያለው?
ዓለም በበርካታ ነፍሳት የተሞላች ነች። ብዙዎችም እነዚህን ነፍሳት ምግባቸው ያደርጋሉ። ይህን የሚያደርጉት ምግብ ተቸግረው ሳይሆን በጣዕሙ መርጠውት ነው።
በሜክሲኮ በጣዕማቸው ተወዳጅ የሆኑ የነፍሳት አይነቶች አሉ። በተለይም ቀይ ትሎች ዋጋቸውም ውድ ነው። እነዚህ ቀይ ትሎች በጥሬ ሁሉ ለምግብነት ይውላሉ።
የተለያዩ ነፍሳትን ለምግብነት ለማግኘት ነፍሳቱ ወደ ሚገኙበት የተለዩ ገበያዎች መሄድ ሊያስፈልግ ይችላል።
አንዳንድ ነፍሳት በጣም ተፈላጊ ከመሆናቸው የተነሳ ነፍሳቱን ለማራባት የመሞከር ነገርም አለ። በሌላ በኩል ደግሞ ነፍሳት ማራባት በጥብቅ የሚከለከልበት ሁኔታ አለ።
ለምግብነት የሚውሉ አብዛኞቹ ነፍሳት እንዲሁ በቀላሉ የሚገኙ ናቸው። ከሰሃራ በታች በሚገኙ አገራት ለምግብነት የሚውሉ ነፍሳትን በምሳሌነት ማንሳት ይቻላል።
አብዛኛውን ጊዜ በዝናብ ወቅት የመጀመሪያው ዝናብ እንደጣለ ነፍሳት በብዛት ካሉበት ይወጣሉ ወይም ይፈለፈላሉ።
በቀጣዩ ቀን መሬት ያለብሳሉ በሚባል ደረጃ ይበዛሉ።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ነፍሳት በብዛት የሚበሉት በገጠራማ አካባቢዎች ሲሆን በከተማ ደግሞ ገቢያ ላይ ይገኛሉ።
ሳይንስ እንደሚለው አብዛኞቹ ነፍሳት ሙሉ በሙሉ ለምግብነት መዋል ይችላሉ። በዚህ ንፅፅር 40 በመቶ የሚሆኑ የከብቶች ሥጋ ግን ለምግብነት መዋል አይችልም።
ለምግብነት መዋል የሚችሉ ሌሎች ነፍሳት ደግሞ በብዛት ዛፍ ላይ ይገኛሉ። ለምሳሌ በዝናብ ወቅት ወደ ቡርኪና ፋሶ ቢኬድ የዛፎች ስር በአባጨጓሬ ተሸፍኖ ይገኛል።
በዚህ ወቅት ኗሪዎችም ንጋት ላይ ተነስተው ነፍሳቱን ይለቅማሉ። ነፍሳቱ የፍራፍሬ ያህል ጣም ያላቸው መሆናቸውንም ይናገራሉ።
በዛፎች ግንድ ውስጥ የሚፈጠሩ ነፍሳትም አሉ። በዚህ መልኩ ከሚፈጠሩት የተወሰኑት በዲሞክራቲክ ኮንጎ በጣም የተለመዱ ናቸው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዛት ለምግብነት የሚውሉት ፌንጣና አምበጣና ናቸው።
በእስያ ገበሬዎች የሩዝ እርሻ ላይ መረብ ወጥረው ለምግብነት የሚውሉ ነፍሳትን ይይዛሉ። በሜክሲኮም ከበቆሎ እርሻ በተመሳሳይ መልኩ ነፍሳትን ለመያዝ ይሞከራል።
እንደ ሰብል ሁሉ ለምግብነት የሚውሉ ብዙ ነፍሳት የሚገኙት ወይም የሚፈጠሩት በተለያየ ወቅት ነው። ነፍሳቱ የሚገኙባቸውን ወቅት ተከትሎም የተለያዩ በአላት በተለያዩ አገራት ይካሄዳሉ።
ለምሳሌ የጃፓኑን የተርብ፤ በቡርኪና ፋሶና በዲሞክራቲክ ኮንጎ የሚካሄደውን የአባጨጓሬ በአል መጥቀስ ይቻላል።
በአሁኑ ወቅት ነፍሳትን በብዛት አምርቶ ለምግብነት የማዋል ፍላጎት ቢኖርም እዚያ ደረጃ ላይ አልተደረሰም።
ነፍሳትን ለምግብነት የማዋሉ ነገር በብዛት እየታየ ያለው የምግብ አማራጭን ከማስፋት እንዲሁም ይዘትን ከማሻሻል አንፃር ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ አካባቢን ከብክለት ከመጠበቅ አንፃር ነው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ