በአፍ የሚወሰዱ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን መጠቀም በማህፀን ካንሰር የመጠቃት እድልን ይቀንሳል – ጥናት

                     

ለተወሰነ ጊዜ በአፍ የሚወሰዱ የወሊድ መቆጣጠሪያዎችን የወሰዱ እናቶች በማህጸን ካንሰር የመያዝ እድላቸው ዝቅተኛ ሆኖ እንደተገኘ ተመራማሪዎች ገለጹ። 

የጥናቱ ውጤት እንዳመላከተው እናቶች በአፍ የሚወሰዱ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን ለረጅም ጊዜ በወሰዱ ቁጥር በዚያው ልክ በማህጸን ካንሰር የመጠቃት እድላቸው ቀንሶ እንደተስተዋለ ነው በጥናቱ ተረጋገጠ የተባለው።

በፈረንጆቹ አቆጣጠር ባላፉት 50 ዓመታት ከ1965 እስከ 2014 በታዩ 40 ሺህ የማህጸን ካንሰር ህሙማን መረጃ ላይ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት የተሻለ ገቢ ያላቸው ሀገራት እናቶች የወሊድ መከላከያ እንክብል በመውሰዳቸው በማህጸን ካንሰር የመጠቃት እድላቸው ቀንሶ ታይቷል ነው የተባለው።

ከበሽታዎች ስርጭትና ከማህጸን ካንሰር አጥኚዎች የተውጣጣ የተመራማሪዎች ቡድን የጥናት ውጤት በተለይም ከ2005 እስከ 2014 በነበሩት ተከታታይ ዓመታት በመጨረሻዎቹ አስርት አመታት በ20 ሺህ እናቶች ላይ ይኸው ውጤት እንደታየ ያስረዳሉ።

የጥናቱ አዘጋጅ የሆኑት ፕሮፌሰር ቫለሬ በራል እንደገለጹት፥ በ20 ዓመታቸው አካባቢ ለተከታታይ ጊዚያት የወሊድ መቆጠቀጠሪያ እንክብሎችን የወሰዱ እናቶች 50 ዓመትና ከዚያ በላይ በሆኑ የእድሜ እኩዮቻቸው ላይ የማህጸን ካንሰር እየተስፋፋ ሲመጣ በበሽታው የመጠቃት እድላቸው ውስን ሆኖ ታይቷል።

የወሊድ መቀጠጣጠሪያ እንክብሎች በኦቫሪ ካንሰር የመያዝ እድልምን ዝቅ እንዳደረጉ ተመራማሪዋ ይናገራሉ ።

ይሁን እንጂ ለረጅም ጊዜ የወሊድ መቆጣጠሪ እንክብል የሚወስዱ እናቶች ከዚሁ በተቃራኒው በማህጸን ካንሰር የመጠቃት እድላችን ከፍ ያለ ነው የሚል ስጋት እንዳለባቸው ነው የተገለጸው።

በ27 ሺህ 176 የማህጸን ካንሰር ህሙማን ላይ በሰሜን አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያ፣ አውስትራሊያና ደቡብ አፍሪካ ላይ በተደረጉ 36 ጥናቶች ተመሳሳይ ውጤት እንደታየ በዘገባው ተገልጿል።

በጥናቶችም ለ5 ዓመታት ያህል የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል የወሰዱ እናቶችን በማህፀን ካንስር የመጠቃት እድል በእንድ አራተኛ ያህል እንደሚቀንሰው ነው የተጠቆመው።

ባደጉት ሀገራት ለ10 ዓመታት የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን የወሰዱ እናቶች ከ75 ዓመታቸው በፊት ከ2 ነጥብ 3 እስክ 1 ነጥብ 3 በመቶ በማህፀን ካንሰር የመጠቃት እድላቸው ቀንሷል ተብሏል።

በጥናቱ የታየው በማህፀን ካንስር የመያዝ አደጋ መቀነስ በእናቶች የሰውነት ክብድት፣ የአልኮል መጠጥ ሱስ፣ ሲጋራና የዘርን መሰረት ሳይለይ ተመሳሳይ ውጤቶች እንዳሉትም ነው የተገለጸው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement