በስራ ቦታ ንቁ ለመሆን

 

           
በስራ፣ ስብሰባ እና በሌሎች ጉዳዮች ምክንያት ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ለተለያዩ በሽታዎች አጋላጭ መሆኑ ይነገራል።

ተመራማሪዎችም ለዚህ የሚሆን መፍትሄ አለን ብለዋል።

ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ከልክ ላለፈ ውፍረት፣ ስኳር፣ ከልብ ጋር ተያያዥ ለሆኑ በሽታዎች እና ለካንስር እንደሚያጋልጥ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።

በመሆኑም ለእነዚህ በሽታዎች ያለንን ተጋላጭነት ለመቀነስ አካላዊ እንቅስቃሴ አስፈላጊ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል። 

በአንድ ጥናት እንደተረጋገጠው በአምስት ቀናት ለ30 ደቂቃዎች የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን መቀነስ እንደሚያስችል ጥናቱ አሳይቷል።

በመሆኑም በስራ ቦታ ንቁና ጤናማ መሆን እንዲችሉ የሚከተሉትን አምስት ነገሮች ተግባራዊ ያድርጉ ተብሏል። 

1. ብስክሌት መንዳት

ወደ ስራ ቦታ በሚያመሩበት ወቅት የመኪና ትራንስፖርትን ከመጠቀም ብስክሌት መንዳትን አልያም በእግር መጓዝን ልምድ ማድረግ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ነው የተገለፀው።

በዚህም ብስክሌት በማሽከርከር ወደ ስራ የሚጓዙት የመኪና ትራንስፖርት ከሚጠቀሙት አንፃር ለሞት እና ለካንሰር ያላቸው ተጋላጭነት ዝቅተኛ መሆኑን ነው ጥናቱ ያመለከተው።

ብስክሌት ማሽከርከር አልያም በእግር መጓዝ ከልብ በሸታ እና ደም ስር ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮችን እንደሚቀንስ ተነግሯል። 

ብስክሌት የሚያሽከረክሩት የመኪና ትራንስፖርት ከሚጠቀሙት አንፃርም የተስተካከለ የሰውነት አካል እንዲኖራቸው ይረዳል ሲሉ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

2. ስራን ቆሞ የመስራት ልምድ ማዳበር

በስራ ቦታ ስራን ቆሞ መከወን ቀላል እና ሰዎች ለበሽታ ያላቸውን ተጋላጭነት እንሚቀንስ ተጠቅሷል።

ተመራማሪዎቹ እንዳረጋገጡት በስራ ቦታ ላይ በትንሹ ለሁለት ሰዓት ቆሞ መስራት የሚያስፈልግ ሲሆን፥ ከተቻለ እስከ አራት ሰዓት በማድረስ ጤናን መጠበቅ ያስፈልጋል። 

3. ረጅም እንቅስቃሴ

በስራ ቦታ መቀመጥ የግድ አስፈላጊ ሊሆን የሚችልና የሚጠበቅ ቢሆንም የስራ አካባቢው በሚፈቅደው ደረጃ የምንቀሳቀስበት ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚያስፈልግ ተጠቅሷል።

ለዚህም አንሳንሰርን አለመጠቀም፣ መኪና ከስራ አካባቢ አርቆ ማቅም፣ ከስራ ባልደረቦች ጋር በኢሜል ከመገናኘት በአካል መሄድ፣ እየተንቀሳቀሱ ስልክ መመለስስን መልመድ እና ሌሎች መንገዶች በመጠቀም በስራ አካባቢ መንቀሳቀስ እንዲቻል ማድረግ እስፈላጊ መሆኑን ተመራማሪዎች ገልፀዋል።

4. የስራ ቦታን ለመንቀሳቀስ ምቹ ማድረግ 

በስራ ቦታ እንቅስቃሴ ማድረግ ስራን በጥራት፣ በብቃት፣ ውጤታማ እና መልካም በሆን ስሜት ማከናወን እንዲቻል ጠቀሜታ ስላለው ሀላፊዎች የስራ ቦታን ማቀንቀሳቀስ እንዲቻል በማድረግ ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህም ውስጥ፥ ከስራ አካባቢ ወንበርና ጠረቤዛን ማራቅ፣ በእግር መራማድን ማበረታት፣ እየተንቀሳቀሱ ቁጥጥር ማድረግ እና ሌሎች ተያያዥ ስርዓቶችን በስራ አካባቢ መዘርጋት ያስፈልጋል ተብሏል።

5. በምሳ ሰዓት እንቅስቃሴ ማድረግ

የምሳ ሰዓት የሚሰሩበት ወንበርና ጠረቤዛ ላይ በመሆን የመስመር ስልክ ከመጠቀም እና የኢሜል መልዕክት ከመመለስ መንቀሳቀስ እና የአካል እንቅስቃሰየ ማድረግ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement