የድመት ጢም

                                         ድመቶች አብዛኛውን ጊዜ በጨለማ ንቁ ናቸው። ከጨለመ በኋላ በአቅራቢያቸው ያሉ ነገሮችን ለይተው ለማወቅና አድነው የሚበሉትን እንስሳ ለመያዝየሚረዷቸው ጢሞቻቸው እንደሆኑ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል የሚለው ጄደብሊው ዶትኦርግ ነው።

የድመት ጢሞች የሚበቅሉት ብዙ የነርቭ ጫፎች ባሏቸው ሕብረ ሕዋሳት ላይ ነው። እነዚህ ነርቮች በአየሩ ላይ የሚፈጠረው በጣም ትንሽ እንቅስቃሴ እንኳይሰማቸዋል። በዚህም የተነሳ ድመቶች በአቅራቢያቸው ያሉ ነገሮችን ባያዩአቸውም እንኳ መኖራቸውን ማወቅ ይችላሉ፤ ይህ ደግሞ በጨለማእንደሚጠቅማቸው ግልጽ ነው።

የድመት ጢሞች ትንሹም እንቅስቃሴ ቶሎ የሚሰማቸው መሆኑ አንድ ነገር ወይም አድነው የሚበሉት አንድ እንስሳ ያለበትን ቦታና የሚያደርገውን እንቅስቃሴለይተው እንዲያውቁ ያስችላቸዋል። በተጨማሪም ድመቶች በአንድ ክፍተት በኩል ለማለፍ ሲሞክሩ ጢሞቻቸው የክፍተቱን ስፋት ለመለካት ይረዷቸዋል።

ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንደገለጸው ከሆነ፣ የድመት ጢም ያለውን ጥቅም በተመለከተ ማወቅ የተቻለው ከፊሉን ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ድመቱ ጢሙከተቆረጠበት ለጊዜውም ቢሆን እክል እንደሚገጥመው ታውቋል።

የሳይንስ ሊቃውንት፣ የድመት ጢሞችን ንድፍ በመኮረጅ በእንቅፋቶች መሃል እየተሹለከለኩ ለመሄድ የሚያስችሉ ጠቋሚ መሣሪያዎች ያሏቸው ሮቦቶችለመሥራት ጥረት እያደረጉ ነው። ኢዊስከርስ ተብለው የተጠሩት እነዚህ ጠቋሚ መሣሪያዎች ‹‹ለተራቀቀ የሮቦት ቴክኖሎጂ፣ የተለያዩ መሣሪያዎችንለአጠቃቀም ምቹ ለማድረግ እንዲሁም በባዮሎጂ መስክ የተለያየ አገልግሎት›› እንደሚኖራቸው በካሊፎርኒያ የሚገኘው የበርክሊ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ሊቅየሆኑት አሊ ጃቪ ተናግረዋል።

ምንጭ:- ሪፖርተር

Advertisement