የጥፍር ፈንገስ ኢንፌክሽን – Nail Fungus Infection

                                                             

የጥፍር ፈንገስ ኢንፌክሽን የምንለው በፈንገስ ምክንያት የሚከሰት ህመም ሲሆን ከአንድ በላይ ጥፍሮችንም ሊያጠቃ ይችላል።የጥፍር ፈንገስ ጥፍራችን እንዲወፍርና የህመም ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል። የጥፍር ፈንገስ ኢንፌክሽኑ በጣቶችዎ መካከል ሊዛመትም ይችላል።

የጥፍር ፈንገስ በአብዛኛው በእግር ጥፍሮች ላይ የሚከሰት ሲሆን አልፎ አልፎ በእጅ ጣት ጥፍሮች ላይም ይከሰታል።

የጥፍር ፈንገስ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
*የጥፍር መወፈር
*የጥፍር ቀለም ወደ ቢጫነት መለወጥ
*የጥፍር ቅርጽ መለወጥ
*መጥፎ ጠረን ማምጣት ናቸው።

ለጥፍር ፈንገስ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
* እድሜ መጨመር
*ከፍተኛ ላቦት መኖር
*በባዶ እግር ውሀ ዋና ቦታ፣ በጂም እና የገላ መታጠቢያ ቦታዎች መራመድ
*የስኳር ወይንም በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳካሙ ህመሞች መኖር ናችው።

የጥፍር ፈንገስ እንዴት መከላከል ይቻላል?
* እጅዎን እና እግርዎን በሚገባ መታጠብ እና ማድረቅ
*በፈንገስ ያልተበከለ የጥፍር መቁረጫን መጠቀም ወይንም በሚገባ አጽድተን መጠቀም
*ላቦትን የሚመጡ ካልሲዎችን መጠቀም
*በየትኛውም ቦታ ጫማ ተጫምተው መንቀሳቀስ
*የአየር ዝውውርን የሚፈቅዱ ጫማዎችን መጠቀም
*ጥፍርዎን ለማስዋብ የሚጠቀሟቸው እቃዎች በሚገባ የጸዱ መሆናቸው ማረጋገጥ
*የጥፍር ማስዋቢያ እቃዎችን ከሌሎች ሰዎች ጋር አለመጋራት ናቸው።

ሀኪምዎን ማማከር የሚገባው መቼ ነው?
የጥፍር ፈንግስ ኢንፌክሽን በከፍተኛ ሁኔታ ከአንድ ጥፍር ወደ ሌላው ሊዛመት ስለሚችልና ተገቢው ጥንቃቄ ካልተወሰደ ደግሞ ሌሎች የቤተሰብ አባሎችንም ሊያጠቃ ስለሚችል ወደሀኪም በመሄድ ተገቢውን መድሀኒት በታዘዘው መሰረት በሚገባ በመጠቀም እንዲለቅ ማድረግ ይቻላል።

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement